No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 17 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ኤስ ኦ-ኤስ የህፃናት መንደር - ጠበቃ አቶ አይሸሽም መድፍ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ለጉዲዩ መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሾች ሲሆኑ አመልካች ተከሣሽ ነበር። ከሳሾች ያቀረቡት ክስ በድርጅቱ በጥበቃ ሰራተኛነት ለበርካታ አመታት ስናገለግል የቆየን ሲሆን ስራውን በልላ ድርጅት ላሰራ ወስኛለሁ በሚል ሰበብ ያለአግባብ ከስራ ውጪ የሥራ ውላችንን ያቋረጠ በመሆኑ ወደ ሥራችን እንድንመለስ፣ የማይመልሰን ከሆነ ካሳና ጥቅማጥቅም እንዱከፈል ይወሰንልን የሚል ነው።
አመልካችም መጋቢት 5 ቀን 1999 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልሱ የድርጅቱን አሰራር ለማሻሻል ከሳሾች ይሰሩበት የነበረውን የጥበቃ ሥራ የጥበቃ አገልግልት ለሚሰጥ “ትረስት የጥበቃና የሰው ኃይል አገልግልት ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” ከተሰኘው ድርጅት ጋር ውል በማድረግ ሥራውን ያስተላለፈ መሆኑን በመግለጽ የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው በማለት ተከራክሯል። ግራ ቀኙን ያከራከረው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ13/9/2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው የ6 ወር ደመወዝ ካሳ እና የእረፍት ጊዜ ክፍያ ተከፍልአቸው ይሰናበቱ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም በዚህ በፍ/ ሰኔ 9 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የ6 ወር ደመወዝ ካሳ ተከፍልአቸው ይሰናበቱ ተብል የተሰጠውን ውሳኔ ለማጣራት ያስቀርባል እንደገና ተመልሶ እና ትዔዛዙ የ6 ወር ካሳ ክፍያን አይመለከትም ላልች ውሳኔዎችን አጽንቼአለሁ ሲል ትዕዛዝ በመስጠቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው ዋና ቅሬታ ስንብቱ የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሰራር ዘዳ ለመለወጥ የተደረገ በመሆኑ ከሕግ ውጪ ነው መባለና የ6 ወር ደመወዝ ካሳ እንዱከፈል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዱሻርልን የሚል ነው።
ቀረቡ በዚህ ፍ/ቤትም የተጠሪዎች ስንብት ያለአግባብ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ በአግባቡ መሆኑ አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ ታዞ ተጠሪዎች ሐምል 22 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ መልስ በማቅረብ ውሳኔው እንዱፀና ተከራክረዋል።እኛም የግራ ቀኙን ክርክር በሕግ ረገድ እንደሚከተለው መርምረናል።
የሥራ ውል ሉቋረጥ የቻለው ተጠሪዎች ይሰሩብት የነበረው የጥበቃ ሥራ ለላላ የጥበቃ አገልግልት ለሚሰጠው ድርጅት በመተላለፍ ምክንያት እንደሆነ በተጠሪዎችም አልተካደም ። ይህ ከታመነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28 መሰረት አሰሪው አዱስ አሰራርን ለመከተል የድርጅቱን ምርታማነት ለማሻሻልና የአሰራር ዘዳዎች በመለወጡ ምክንያት ሰራተኞቹ ይሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ ቢሰረዝ አሰሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውል ለማቋረጥ እንደሚችል በግልጽ ተደንግጓል። የበታች ፍ/ቤት ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው ለማለት መሰረት ያደረገው አመልካች የጥበቃ ሥራ በልላ ሦስተኛ ወገን እንዱከናወን ተደርጓል ከሚል በስተቀር የሥራ መደቡ ተሰርዟል የሚል ባለመሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 28 ትርጉም ሉሰጠው የሚችል አይደለም የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት ነው። በመሰረቱ አመልካች የሥራ መደቡን ለላላ ድርጅት ሲሰጥ የጥበቃዎቹ ቅጥር፣ዔድገት፣ዝውውር፣ስንብትና ክፍያ የሚፈፀመው በዚያው ድርጅት ነው ። አመልካች የሥራ መደቡን ሰርዞ ያስተላለፈ በመሆኑ በቃል የክፍያ ስምምነት በማድረግ ለድርጅቱ የሚከፍል ስለሆነ ሥራው የሚያከናውነው በልላ ድርጅት ነው። ያም ሆነ ይህ በተያዘው ጉዲይ ለውሳኔው መሰረት መሆን የሚገባው የሥራ መደቡ መሰረዝ ወይም አለመሰረዝ ብቻ ሳይሆን ስንብቱ ሕጋዊ ነው ወይንስ ከሕግ ውጪ ነው የሚለው ጭብጥ ሆኖ አመልካች የመልስ ሰጭዎችን/የተጠሪዎችን/ የሥራ ውል ለማቋረጥ ሕጋዊና በቂ ምክንያት መኖሩን ማስረዲት ነው። አመልካች አከራካሪ የሆነውን የሥራ መደብ ለላላ አካል ማስተላለፍን ተጠሪዎች በክስ ማመልከቻቸውም ላይ የጠቀሱትና ያልተካደ በመሆኑ ሥራን ለላላ ማስተላለፍ /0ut sourcing/ ሕጋዊ ነው። ይህ ከሕግ ወጪ ነው የሚል ወገን አለመተላለፍን ማስረዲት ብቻ ነው። ይህ ክርክር የለም ምናልባት አመልካች ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው ማሰናበቱ የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደ ሚለው መደምደሚያ የሚያደርስ ሳይሆን ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጥ ውጤቱ ለሰራተኛው ሉከፈለው የሚገባውን የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እንዱከፈላቸው ሕጉ ከሚያስገድድ በስተቀር የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ወደ ሚለው የተለጠጠ የሕግ ትርጉም ላይ የሚያደርስ አይሆንም።
ለማጠቃለል የሥራ መደብ በልላ ሦስተኛ ወገን እንዱከናውን አሳልፍ መስጠት/0ut sourcing/ በውጫዊ እይታ ሲታይ የሰራተኛውን መብት የሚነካ ቢመስልም በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ ረገድ ሕጋዊ አሰራር ነው። በመሆኑም የተጠሪዎች የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት የ6 ወር ደመወዝ ካሳ ተከፍልአቸው ይሰናበቱ በማለት የተሰጠው ውሳኔ ከላይ በተመለከቱ ምክንያቶች መሰረታዊ የሕግ ትርጉም ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ 13/9/2000 ዓ.ም ስንብቱ ከሕግ ውጪ ነው በማለት የ6 ወር ደመወዝ ካሳ ተከፍልአቸው ይሰናበቱ ሲል የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።ይፃፍ።
ስንብቱ በሕግ አግባብ ነው ብለናል።
በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 35 መሰረት የማስጠንቀቂያ ሉከፈላቸው ይገባ የነበረውን እንደየአገልግልት ዘመናቸው አንፃር ሉከፈላቸው ይገባል ብለናል።
ተጠሪዎች ከ9/12/98/ እስከ ጥር 25 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ያለው የእረፍት ቅጣት ክፍያ እንዱከፈል በተሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበ አቤቱታ ስለላለ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ የዚህ ፍ/ቤትን ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለን መዝገቡን ዘግተናል።
No topics extracted.