No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 17 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ርሆቦት ሆሉሴቪየር ኃ/የተ/የግ/ማ ጠ/ተስፊዬ ክትላ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አማረ አድማሱ ቀረቡ።
ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ጉዲይ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሥራ ክርክር ችልት የጀመረ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በዚሁ ፍ/ቤት በቀረቡት ክስ አመልካች በህገ-ወጥ መንገድ የሥራ ውላቸውን ስላቋረጠው ወደ ስራ እንዱመልሣቸው የማይመልሳቸው ከሆነ ግን የተያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸውና የስራ ም/ወረቀት እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪ ላቀረበበት ክስ የስራ መሪ በመሆናቸው ክሱ በዚህ ፍ/ቤት ላቀርብ አይገባም በማለት ከተቃወሙ በኋላ በድርጅቱ በደተረገው የመዋቅር በውስጥ የተጠሪ የስራ መደብ በመሰረዙና ተጠሪን ወደ ላላ የስራ መደብ አዛውሮ ማሰራት ባለመቻለ ማሰናበቱንና ይህም ስንብት ህጋዊ እርምጃ በመሆን የተጠሪ ክስ ተቀባይነት የለውም አመልካች የማስጠንቀቂያና የስራ ስንብት ክፍያ ለተጠሪ ፈጽሟል የም/ወረቅትም ሰጥቷል በማለት ለፍሬ ጉዲዩ መልስ ሰጥቷል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ የሥራ መሪ የሚያከናውነው ተግባር ላይ የተሰማሩ ስለመሆናቸው ማስረጃ ስላላቀረበ መቃወሚያው ተቀባይነት የለውም የድርጅቱን ወጪ በመቀነስ የአመልካች የመደበኛ ት/ቤቶች ሀላፉነት የስራ መደብ መሰረዙን ያስረዲ ቢሆንም ተጠሪን ወደ ላላ ቦታ አዛውሮ ማስረዲት አለመቻለን የሚያስረዲ ማስረጃ ስላላቀረበ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ስለሆነም የ2 ወር ደመወዝ ከፍል ተጠሪን ወደ ስራቸው ይመልሣቸው በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይርባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ የ2 ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ ይመለሱ የሚለውን ውሣኔ ያፀና ሲሆን ነገር ግን አመልካች ለተጠሪ የ2 ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና የስንብት ክፍያ የከፈለ ለመሆኑ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ተጠሪ ወደ ስራ ከተመለሱ የተቀበለትን ክፍያ ለአመልካች ሉመልሱ ይገባል በማለት ወስኗል።
የአሁኑ የአመልካች አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን ተጠሪ የስራ መሪ ናቸው በተደረገው የመዋቅር መሻሻያ የተጠሪ የስራ መደብ የተሰረዘና ወደ ላላ የስራ መደብ አዛወሮ ማሰራት ባለመቻለ የስራ ውለ መቋረጡ በአግባቡ ነው በማለት ቅሬታውን አቅርቧል።
ይህ የአመልካች አቤቱታ ለሰበር ችልት ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ጥቅምት 18/2001 የተፃፈ መልስ አቅርበዋል ችልቱም የአመልካችን አቤቱታ የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና ከህጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል።
በመጀመሪያ አመልካች ተጠሪ የሥራ መሪ ናቸው በማለት ያቀረበውን ቅሬታ ስንመለከት የተጠሪ የስራ ኃላፉነት የስራ መሪ የሚሰኛቸው ነው ወይስ አይደለም የሚለው በማስረጃ የሚረጋገጥ የፍሬ ነገር ጉዲይ እንደመሆኑ አመልካች ይህንኑ የማስረዲት ሸክም አለበት ነገር ግን ከመዝገቡ እንደተረዲነው በስር ፍ/ቤት አመልካች ይህንን ለማስረዲት ያቀረበው ማስረጃ የለም በመሆኑም በዚህ በኩል ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
ወደ ፍሬ ጉዲዩ ስንገባ አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን እንመለከታለን ተጠሪ ከስራ የተሰናበትኩት በህገ-ወጥ መንገድ ነው ሲለ አመልካች ደግሞ በተደረገው የመዋቅር ማሻሻያ የተጠሪ የስራ መደብ በመሰረዙ በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። ከመዝገቡ እንደተረዲነው አመልካች የድርጅቱን ወጪ ለመቀነስ ባደረገው የመዋቅር ማሻሻያ የተጠሪ የስራ መደብ መሰረዙን አመልካች አስረድቷል የሥር ፍ/ቤቶች ይህንን ካረጋገጡ በኋላ የሥራ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ያለት አመልካች ተጠሪን ወደ ላላ ሥራ ማዛወር የማይችል መሆኑን አላስረዲም በማለት ነው። በእርግጥ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 28/1/መ/ መሰረት አንድ ሰራተኛ በማስጠንቀቂያ ከስራ የሚሰናበተው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲሰረዝና ሰራተኛውን ወደ ላላ ሥራ ማዛወር የማይችል ሆኖ ሲገኝ ነው በተያዘው ጉዲይ የተጠሪ የሥራ መደብ በመዋቅር ማሻሻል ምክንያት የተሰረዘ መሆኑ ተረጋግጧል። ስለዚህ የሥራ መደብ የተሰረዘው በበቂ ምክንያት ነው በልላ በኩል ግን አመልካች ተጠሪን ወደ ላላ የሥራ መደብ መዛወር አለመቻለን የገለፁ ሲሆን ተጠሪ በቃራኒው አመልካች ወደ ላላ የሥራ መደብ አዛውሮ ሉያሰራቸው የሚችል መሆኑን ገልፀው አልተከራከሩም በዚህ በሰበር ችልት በሰጡት መልካም ቢሆን በአንቀፅ 28/1/መ/ መሰረት የሥራ ውለ ሲቋረጥ ማስጠንቀቂያ ሉሰጣቸው ሲገባ አመልካች ማስጠንቀቂያ አለመሰጠቱ ስንብቱን ህገ-ወጥ ያደረገዋል በማለት ከሚከራከሩ በቀር በአመልካች ድርጅት ውስጥ ተዛውረው ሉሰሩበት የሚችለበት የሥራ መደብ እያለ የሥራ ውላቸው ሉቋረጥ እንደማይገባ ገልፀው አልተከራከሩም በመሆኑም ተጠሪው ይህንን ክርክር አንስተው ሣይከራከሩ የሥር ፍ/ቤት አመልካች ተጠሪን ወደ ላላ ቦታ ማዛወር አለመቻለን አላስረዲም በሚል ምክንያት ስንብቱ ህገወጥ ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ26/05/2000 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
2/ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ4/10/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
3/ የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 28/1/ መሰረት በመሆኑ ህጋዊ ነው 4/ ተጠሪ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት ከአመልካች የተቀበለትን የማስጠንቀኪያ ጊዜ ክፍያ እና የሥራ ስንብት ክፍያ መልሰው ከሆነ አመልካቹ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና የሥራ ስንብት ክፍያ መልሰው ከሆነ አመልዛቹ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና የሥራ ስንብት ክፍያ ይከፈላቸው የሥራ ምስክር ወረቀት ያልሰጣቸው ከሆነም እንዱሰጣቸው ተወስኗል።
5/ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።