No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 28 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው ዓሉ መሐመድ አልማው ወላ አመልካች፡- ዶ/ር ማንደፍሮ እሸቴ በራሳቸው እና ሞግዚት ለሆኑላት ለህፃን ጀሲካ ማንደፍሮ ጠበቃ አዲሙ ሽፈራው ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- ፍሬድረክ ኤቨርት ሲቲፍቱንግ- ጠበቃ መሐሪ ዓለማየሁ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ፡ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሆኖ የጉዲት ካሣንና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ክፍያዎችን የሚመለከት ነው ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች የካቲት 02 ቀን 1998 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ የአመልካች ህጋዊ ባለቤት እና የህፃን ጀሲካ ማንደፍሮ ወላጅ እናት የሆኑት ሟች ዶ/ር ሰብለ ደምሰው በተጠሪ መ/ቤት ከሚያዝያ 25 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክት ስራ አስተባባሪነት የሥራ መደብ በወር ደመወዝ ብር 4500.00/አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በሰራተኛነት ተቀጥረውና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ከደመወዛቸው በተጨማሪ እየተከፈላቸው በማገልግል ላይ እያለ ተጠሪ ለመስክ ስራ ወደ አዋሣ ልኳቸው ወደ አዱስ አበባ በመመለስ ላይ እንዲለ ተጠሪ ለመስክ ስራ በግልፅ የመደበው መኪና ነሐሴ 09 ቀን 1997 ዓ.ም ተገልብጦ ዶ/ር ሰብለ ደምሰው ህይወታቸው በአደጋው ወዱያውኑ ማለፍን በመጥቀስ የጉዲት ካሣ፣ የቀብር ማስፈፀሚያ፣ የስንበት ክፍያ እንዱሁም የዓመት ፈቃድ ክፍያ እና ክፍያው ለዘገየበት ከበቂ ኪሣራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው ። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነት ቀርቦ የሟች የስራ ቅጥር ውል ባለመሆኑ በስራ ክርክር ችልት ላታይ እንደማይገባውና ሟች የአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ሆነው በተከሣሽ ድርጅት የነበራቸው የአገልግልት ውል መሆኑን በመግለፅ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ሟች ህይወታቸው ባለ ጊዜ ከተከሣሽ ጋራ ውል ያልነበራቸው መሆኑን ፣ ህይወታቸው ባለፈበት ጊዜም ወደ መስክ የሄደት ከተከሣሽ ድርጅት ጋራ ለስራ ውል ግንኙነት ሣይኖራቸው አንደኛ አመልካች ባለቤታቸው በመሆናቸው አንድ ላይ ለመሄድ ፈልገው መሆኑን፣ የመኪና መገልበጥ አደጋው የደረሰውም በተከሣሽ ድርጅት የተመደበ ሹፋር እያለ የስር አንደኛ ከሣሽ አላግባብ መኪናውን ከሹፋሩ በመቀበል በማሽከርከራቸው በመሆኑ ተከሣሽ ድርጅት ለአደጋው ኃላፉ ልባል እንደማይገባና የተጠየቁትን ክፍያዎችም የስራ ውል ግንኙነት ሣይኖር የሚከፍለበት ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ሚያዝያ 04 ቀን 1998 ዓ.ም በፃፈው የመከላከያ መልስ ማመልከቻ ዘርዝሮ ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር እና ማስረጃዎችን ከሰማ በኋላ በተጠሪ በኩል በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የቀረቡትን የክርክር ነጥቦች ውድቅ በማድረግ በሟችና በተጠሪ መካከል የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የነበረ መሆኑን ተረጋግጧል በማለት ድምዲሜ ከደረሰ በኋላ የጉዲት ካሣውን በተመለከተ አደጋው በደረሰ ጊዜ መኪናውን የሟች ባለቤት የሆኑት አንደኛ አመልካች ሲያሽከረክሩ ስለነበር በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ነው ልባል አይችልም በማለት በዚህ ረገድ የቀረውን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ አድርጏ ተከሣሽ ድርጅት የስንብት ክፍያ ብቻ ሉከፈል እንደሚገባ በመግለፅ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ መጋቢት 02 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 4/አራት/ ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የጉዲት ካሣውም ሆነ የቀብር ማስፈፀሚያ ክፍያ እንዲይከፈል የተባለው በጉዲዩ ላይ የቀረበውን ክርክርና ማስረጃ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 96(1) ስርና ተከታዩቹ ድንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ መሆኑን አንደኛ የሰበር አመልካች ጥፊት የለባቸውም አለባቸው ቢባል እንኳ የሁለተኛ አመልካች የካሣ ጥያቄ ውድቅ የሚሆንበት አግባብ አለመኖሩን፣ የሟች የቀብር ማስፈፀሚያ የተከላከለውም ህጋዊ መሰረት ሣይጠቀስ መሆኑንና ፣ ሟች ያልወሰደት የዓመት እረፍት ክፍያ ውድቅ የተደረገውም የሰበር ተጠሪ ባልተከራከርንበትና ባላስረዲ ሁኔታ መሆኑን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ተሽሮ የሞት ጉዲት ካሣ ብር 270,000.00(ሁለት መቶ ሰባ ሺህ) ፣ የቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ የሟችን የሁለት ወር ደመወዝ፣ ያልተወሰደ የዓመት እረፍት የሟች የሁለት ወር ደመወዝ እና ተጠሪው ክፍያ ላዘገየበት የሟች የሶስት ወር ደመወዝ ለሰበር አመልካቾች ተከፍል እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፈል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል ተብል በመታዘዙም፤ የተጠሪ ጠበቃ ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን አቅርበዋል። በመልሣቸውም የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ማየቱ ተገቢ ያልነበረ ስለመሆኑና ሟች የተጠሪ መደበኛ የቅጥር ሰራተኛ ያልነበሩ ስለመሆናቸው፣ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ካየም ሟች ዶ/ር ሰብለ ደምሰው ከተጠሪ ጋር ባደረጉት የአገልግልት ውልም መሰረት መወሰን የነበረበት ስለመሆኑ፣ የሟች የአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ መደበኛ ተቀጣሪ ሆነው ከተጠሪ ዘንድ በተወሰነ ጊዜ በተደራቢነት አገልግልት መስጠታቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ከተጠሪ ጋር የቅጥር ውል ነበራቸው ልባል የማይገባ ስለመሆኑ፣ ሟች የአገልግልት ውልም ቢሆን ሟች በ09/12/1997 ከመሞታቸው አንድ ወር ተኩል ቀደም ብል በ23/10/97 ያበቃ ስለመሆኑ፣ ሟች የሞቱት በስራ ላይ ባልነበሩበትና መኪናውን ለማሽከርከር ከተጠሪ ፈቃድ ባልተሰጣቸው በአንደኛ አመልካች አላግባብ ሲሽከረከር ስለመሆኑ ተጠያቂነትም ቢኖር ክስ አልቀረበበትም እንጂ ከውል ውጪ ባለ ኃላፉነት ስለመሆኑ ይህንን ዓይነት አደጋ ሲያደርስ ሟች ሉካሱ እንዱችለ ተጠሪ በአገልግልት ውለ መሰረት በየወሩ ለሟች ብር 200 የመድን ሂሣብ ለራሣቸው ይከፈል የነበረ ስለመሆኑ፣ የቀረቡት የክፍያ ጥያቄዎች የህግ መሰረት የላላቸው ስለመሆኑ በመዘርዘር የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ሆኖ በቂ ወጪና ኪሣራ እንዱከፈል ይወሰን ዘንድ ተከራክረዋል። የአመልካቾች የተጠሪ ጠበቃ መከራከሪያ ነጥቦች ሥነ ሥርዓቱን ጠበቃው ያልቀረቡ መሆኑን በመለየትና ተቀባይነት የላላቸው መሆኑን በመዘርዘር የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል። ከዚህም በኋላ ግራ ቀኙ የቃል ክርክር እንዱያደርጉ ታዝዞ ክርክራቸው ታህሣሥ 16 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ተደምጧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ እና የቃል ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ከላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አደጋው የደረሰው አንደኛ የሰበር አመልካች ያላግባብ መኪናውን ከሾፋሩ በመቀበል ሲያከራክሩ ነው ተብል ተጠሪ የጉዲት ካሣ የመክፈል አላፉነት የለበትም መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ? በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ህይወታቸው ያለፈው የተጠሪ መስሪያ ቤት ንብረት የሆነው መኪና ለመስክ ስራ ከሄደበት ቦታ በመመለስና በአንደኛ የሰበር አመልካች በመሽከርከር እያለ በመገልበጡ ምክንያት መሆኑን፣ በሟችና በተጠሪ መካከልም የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙት መኖሩ ተረጋግጧል ተብል በስር ፍ/ቤት መወሰኑን፣ አንደኛ አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤት የስራ ግንኙነት ያላቸው መሆኑንና ሁለተኛ ተጠሪ አካለ መጠን ያላደረሰች የሟች ተወላጅ መሆናቸውን ነው የስር ፍ/ቤት የሟችና የተጠሪ ግንኙነት በአሰሪና ሰራተኛ የሚፈረጅ መሆኑን በመደምደምም ተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፍል እንደሚገባ በውሣኔው ላይ መግለፁን ከመዝገቡ ተመልክተናል። ላላው ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የሟችና የተጠሪ ግንኙነት በሚያዝያ 25 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ ውል መቋቋሙን፣ በዚህ ውል መሰረት ግንኙነታቸው እስከ ጥቅምት 21 ቀን 1997 ዓ.ም ቆይቶ ከጥቅምት 22 ቀን 1997 ዓ.ም በኋላ ግን የስራ ቅጥር ስምምነት ለመዋዋል እንደሚያቅደ መስማማታቸውን፣ ከዚህ በኋላ ተደረገ በተባለ ማሻሻያም የውል ግንኙነት እስከ ሰኔ 23 ቀን 1997 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን እንዱሁም ከሚያዝያ - ነሐሴ ወር 1997 ዓ.ም ላለት ጊዜያት በውለ ላይ የተመለከቱት ክፍያዎች በሟች ስም ተሰርተው ለአንደኛ አመልካች መከፈላቸው በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮችም ሟች ለመስክ ስራ የሚያስፈልጋቸው የውል አበል ክፍያ ተከፍሎቸው ለስራው የሄደ መሆኑ መመስከራቸውን ነው።
በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ጉዲዬች እነዚህ ሆነው የሰበር ተጠሪ ሟች ጋር የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት የለንም በማለት ለሰበር ችልቱ በሰጠው የጽሁፍና የቃል ክርክር ያቀረበውን ክርክር ሥነ-ሥርዓታዊ መሆን ያለመሆኑን መመልከቱ አስፈላጊ ነው።
የተጠሪ ጠበቃ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሟችንና የተጠሪን ግንኙነት አስመልክቶ በቀረበው ክርክር የተጠሪን ክርክር ባለመቀበል በመካከላቸው የነበረው ውል ከአሰሪና ሰራተኛ የሚመነጭ ዓይነት ውል ስለመሆኑ በመጥቀስ ውሣኔ መስጠቱን አምነው በዚህ ነጥብ ላይ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያላቀረቡት ለሟቹ ይከፈል የተባለው የስራ ስንብት አነስተኛና የተጠሪን መብት የማይጏዲ ስለሆነ ነው በማለት ተከራክረዋል።
በመሰረቱ በአንድ የፍ/ቤት ውሣኔ ይግባኝ ለበላይ ፍ/ቤት የሚቀርበው ውሣኔው ወይም ትዔዛዙ የይግባኝ አቅራቢውን መብት ወይም ጥቅም የነካ ፣ አሉያም ግዳታው ከፍ እንዱል ያደረገ ሆኖ ሲገኝ ስለመሆኑ ስለ ይግባኝ አቀራረብ የተደነገጉት የፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎች የሚያስገነዝቡት ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይ የስር ፍርድ ቤት የሟችንና የተጠሪ ግንኙነት የስራ ቅጥር ግንኙነት ስለመሆኑ በመቀበል የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፍል መወሰኑ የተጠሪን መብት ወይም ጥቅም የነካ አይደለም ልባል የማይችልበት ህጋዊ ምክንያት ስለላለ የተጠሪ ጠበቃ በሥርዓቱ መሰረት በጉዲዩ ላይ ቅሬታ ሣያቀርቡ በተጠሪና በሟች መካከል የስራ ቅጥር ግንኙነት የለም በማለት በሰበር ደረጃ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። በዚህ ረገድ የቀረበው ክርክር ሥነ-ሥርዓታዊ ካለመሆኑም በላይ ሟች አደጋው በደረሰባቸው ወቅት ለመስክ ስራ የሄደት ከተጠሪ መስሪያ ቤት አበል ተከፍሎቸው ነው ተብል ከተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ አኳያ ተቀባይነት የለውም ሟች በአዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋሚ ሰራተኛ መሆናቸውም ከተጠሪ ጋር የስራ ቅጥር ግንኙነት ለማድረግ የሚከለክላቸው አለመሆኑን የአዋጅ ቁጥር 351/1995 አንቀጽ 24 ድንጋጌ በግልፅ ያሣያል።
በመሆኑም በሟችና በተጠሪ መካከል ነበረ የተባለውን ግንኙነት በተመለከተ የተጠሪ ጠበቃ ያነሡት መከራከሪያ ሥነሥርዓቱን ያልጠበቀና የግራ ቀኙን የማስረጃዎች ይዘት እንዱሁም ስለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጣውን አዋጅ ያላገናዘበ በመሆኑ አልፈነዋል።
ወደ ዋናው ጭብጥ ስንመለስም ሟች ህይወታቸው ያለፈው ተጠሪ ለመስክ ስራ የመደበውን መኪና ከተጠሪ ሹፋር አንደኛ አመልካች በመቀበል ሲያሽከረክሩ መሆኑ በግራ ቀኙ ያልተካደ ጉዲይ ነው። አንደኛ አመልካች በወቅቱ ወደ መስክ የሄደት ከተጠሪ ፍላጏት ውጪ ነው ከመባለ በስተቀር የተጠሪ ሰራተኛ መሆናቸው አልተካደም።
እንግዱህ ሟች የሞቱት 1ኛ አመልካች መኪናውን ሲያሽከረክሩ መሆኑ አሰሪ የሆነውን ተጠሪ ከአላፉነት ያድንዋል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሉመረመር የሚገባው ነው።
በመሰረቱ በስራ ምክንያት ለሚመጡ ጉዲቶች አሰሪው አላፉነት አለበት። ስለዚህ በስራ ምክንያት የሚመጣ ጉዲት ከሆነ አሰሪው አላፉነቱን እንዱወስድ የተደረገ ሲሆን በአዋጁም በስራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ማለት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ መሆኑን በቁጥር 95(2) ደንግጓል በአዋጅ አንቀጽ 96(1) ”አሰሪው ጥፊት ባይኖረውም…..” ተብል መመልከቱ የአሰሪው የአላፉነት ዓይነት ጥፊት ሣይኖር አላፉነት /Strict Liability or Liability in the absence of Fault/ መሆኑን የሚያሣይ ነው። አሰሪው ከዚህ ዓይነት አላፉነት የሚድነው ጉዲት የደረሰበት ሰራተኛ ሆነ ብል በራሡ ላይ ያደረሰው ጉዲት መሆኑን ማስረዲት ሲችል ስለመሆኑ አንቀጽ 98(2) ያስገነዝባል።ሆነ ብል ያደረሰው ጉዲት የሚባለት ሁኔታዎችም ሰራተኛው አስቀድሞ በግል የተሰጡትን የደህንነት መጠበቂያ መመሪያዎችን መጣስ ወይም የአደጋ መከላከያ ደንቦችን መተላለፍ ወይም አካለን ወይም አእምሮውን በሚገባ ለመቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ በመጠጥ ወይም በአደንዛዥ እፅ ሰክሮ በሥራ ላይ መገኘት መሆናቸውን ህጉ በቁጥር 96(2(ሀ እና ለ)) ስር አመላክቷል።
የአዋጁ አንቀጽ 97(1) ድንጋጌ ሲታይም አንድን አደጋ በስራ ላይ የደረሰ ነው ለማለት ሰራተኛው ስራውን በማከናወን ላይ እያለ ወይም ከስራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሡ ውጭ በሆነ ምክንያት ወይም ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካለ ወይም በአካለ በማንኛውም ክፍል ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት የደረሰበት ጉዲት ስለመሆኑ መርሁን ያስቀመጠ ሲሆን ይኸው ድንጋጌ ከፉደል (ሀ) እስከ ፉደል (መ) በተመለከቱት ንዐስ ድንጋጌዎች የተመለከቱት ምክንያቶች በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ተብለው የሚጨመሩ ስለመሆኑ ያሣያል። ስለሆነም በመርሁ መሰረት ሰራተኛው የጉዲት ካሣ ለማግኘት ማሣየት የሚጠበቅበት አደጋው ስራውን በማከናወን ላይ እያለ የደረሰ መሆኑን፣ ወይም ደግሞ በራሡ ባልሆነ ምክንያት ግን ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው መልኩ የደረሰበት አደጋ መሆኑን ነው ።ከላይ እንደተገለፀው ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ህጉ አስቀምጧል። ለዚህ ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው ድንጋጌ በአንቀጽ 97(1(ሐ)) ስር የተመለከተው ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት አሰሪው በመደበው የመጓጓዝ አገልግልት ሰራተኛው ሲጠቀም ጉዲት ከደረሰ አደጋው በስራ ላይ እንደደረሰ ተቆጥሮ አላፉነቱን ከአሰሪው ሲወሰድ የሚገባ መሆኑ ተመልክቷል። ይኸው ድንጋጌ አሰሪው የመደበው የመጓጓዝ አገልግልት አደጋው ከደረሰበት በአሰሪው ስር ባለው ላላ ሰራተኛ ወይም 3ኛ ወገን ከሆነ አሰሪው ለተጏጂው ሰራተኛ የጉዲት ካሣ አላፉነት የላለበት ስለመሆኑ አያሣይም ይልቁንም ድንጋጌው በአዋጁ አንቀጽ 96(1) ስር ከተመለከተው የአሰሪ አላፉነት ዓይነት ጋር ተዲምሮ ሲታይ አሰሪው አላፉነት ያለበት መሆኑን የሚያጠናክር ነው በልላ አገላለፅ በሰራተኛው ላይ ጉዲት ያደረሰው ሰራተኛው ወደ ስራ ሲሄድና ከስራ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ አሰሪው በመደበው የመጓጓዠ አገልግልት ሲጠቀም አደጋ የደረሰበት መሆኑ ከተረጋገጠ 3ኛ ወገኖች ለአደጋው ያደረጉት አስተዋጽኦ ለአሰሪው መከላከያ ላሆን አይችልም። በመሆኑም አንደኛ አመልካች የተጠሪን መኪና በወቅቱ ሲያሽከረክሩ የነበሩ መሆኑ መረጋገጡ ተጠሪን ነፃ ሉያደርገው የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት ስለላለ በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች አደጋው የደረሰው በስራ ምክንያት አይደለም ሲለ የደረሰበት ድምዲሜ ከላይ የተመለከተቱን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ድንጋጌዎችን ያላገናዘበ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ተጠሪ ለጉዲቱ አላፉነት አለበት ከተባለ የጉዲት ካሣ መክፈል ያለበት ለየትኞቹ የተጏጂ ጥገኞች? የሚለው ጥያቄም በህጉ አግባብ መታየት ያለበት ነው። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ድንጋጌም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 107(1(ሐ) ስር ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ማንኛውም በስራ ላይ የሚመጣ ጉዲት የደረሰበት ሰራተኛ የሞተ እንደሆነ ለጥገኞች የጡረታ አበል ወይም ዲረጏት ወይም ካሣ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ ተመልክቷል።የአዋጁ አንቀጽ 110 ድንጋጌ ሲታይም ለሟች ሰራተኛ ጥገኞች የሚከፍለትን የክፍያ ዓይነቶንና ጥገኛ የሚባለትን ወገኖች በንዐስ ቁጥር አንድና ሁለት በግልፅ ዘርዝሯል። በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰራተኛ ወይም ለማጅ ሰራተኛ በስራ ምክንያት በደረሰበት ጉዲት የተነሣ የሞተ እንደሆነ የጉዲት ካሣ ለጥገኞች፣ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወጪ እንደሚከፈልና ጥገኞች የሚባለትም የሟች ህጋዊ ባል ወይም ሚስት፣ ዔድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ የሟች ልጆችና በሟች ሰራተኛ ድጋፍ ይረደ የነበሩ የሟች ወላጆች ስለመሆናቸው ተመልክቷል። ይሁን እንጂ ህጉ ጥገኝነት ማለት ምን እንደሆነ ትርጓሜ ያልሰጠበት ሲሆን ከህጉ አቀራረፅና ይዘት በመነሣት ግን የቃለን ትርጉም ለመገንዘብ አያዲግትም።
በመሆኑም በህጉ የተመለከተው ጥገኞች የሚለው ቃል ከሟች የምግብ፣ የመጠለያ፣የልብስና ለጤናው አጠባበቅ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንዱሟላላቸው የሚጠይቁትን ወገኖችን የሚመለከት ስለመሆኑ ተገንዝበናል ሥራ ሰርቶ እራሡን ለማስተዲደር የሚችልና ችግረኛ መሆኑ በቅድሚያ ያልተረጋገጠበት ወገን የሟች ሰራተኛ ባል ወይም ሚስት በመሆኑ ብቻ የጉዲት ካሣ የሚያገኝበት ምክንያት አይኖርም። ከጉዲት ካሣ ዓላማ ጋርም አንድ ላይ ይሄዲል ተብል እይታሰብም።
ስለሆነም የሟች ሰራተኛ ባል ወይም ሚስት መተዲደሪያ የሚሆነው በቂ ሀብት ካለው ጥገኛ ልባል አይችልም። ከዚህም በተጨማሪ በአንቀጽ 110(1) እና (2) የተመለከቱት ድንጋጌዎች አቀራረፅና ይዘት እንዱሁም በዘርፍ መሰረት የሚደረጉ ክፍያዎች ከገቢ ግብር ነፃ መሆናቸው፣ ሉተላለፍ፣ ሉከበር ወይም በዔዲ ማቻቻያነት ሉያዝ አለመቻለ በአዋጁ አንቀጽ 112 ስር መመልከቱ የጉዲት ካሣ ዓላማው መተዲደሪያ የሚሆነው በቂ ሀብት የላለውን የሟች ሰራተኛ ለመደገፍ የታሰበ ነው የሚለውን ክርክር የሚያጠናክር ነው ።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አንደኛ አመልካች የሟች ባል ቢሆኑም በቂ የሆነ መተዲደሪያ ሀብት ያላቸው ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት ያሣያል። ስለሆነም አንደኛ አመልካች የሟች ጥገኛ ባለመሆናቸው የጉዲት ካሣ የሚያገኙበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ሁለተኛ አመልካችን በተመለተ ግን የሟች ልጅና በህጉ አግባብም የሟች ጥገኛ መሆኗ ስለተረጋገጠ የጉዲት ካሣ የሚገባት ሆኖ ተገኝቷል።
የቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ ክፍያ የስር ፍ/ቤት ያለው አደጋው የደረሰው በስራ ምክንያት አይደለም። በሚል ነው። ሆኖም ከላይ እንደተመለከትነው ተጠሪ በአሰሪነቱ አላፉነት አለበት ተብሎል። ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(1(ለ) መሰረት የቀብር ሥነ ሥርዓት ማስፈፀሚያ የመክፈል አላፉነት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። የዓመት ፈቃድ ክፍያን በተመለከተ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠ ውሣኔ የሚነቅፍ ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠው አላፉነትን መሰረት በማድረግ በመሆኑ የጉዲት ካሣ መጠኑን አልወሰነም ከላይ እንደተመከለተው ተጠሪ ለጉዲቱ አላፉነት ያለበት የሟች ልጅ ለሆነችው ሁለተኛ አመልካች የጉዲት ካሣ የመክፈል አላፉነት ያለበት መሆኑን ተገልጿል። ለጥገኞች የሚከፈል የጉዲት ካሣ መጠን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(3) እና (4) ስር ተመልክቷል ። ስለሆነም የካሣ መጠኑን በተመለከተ የስር ፍ/ቤት ጉዲዩን እንደገና ተመልክቶ እንዱወሰን ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ 1/ አላፉነትን በተመለተ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ ታህሣሥ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው የውሣኔው ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2/ የስር ፍርድ ቤት የዓመት እረፍት እና የስንብት ክፍያን በተመለከተ የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
3/ ሟች የሞቱት በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ነው ልባል በሚችል ምክንያት በመሆኑ ተጠሪ የጉዲት ካሣ የመክፈል አላፉነት አለበት ብለናል።
4/ ተጠሪ የሟች የቀብር ሥርዓት ማስፈፀሚያ የመክፈል አላፉነት አለበት ብለናል።
5/ አንደኛ አመልካች፤ ዶ/ር ማንደፍሮ እሸቴ የሟች ጥገኛ ባለመሆናቸው የጉዲት ካሣ አይገባቸውም ብለናል።
6/ ሁለተኛ አመልካች ህፃን ጀሲካ ማንደፍሮ የሟች ጥገኛ በመሆኗ የጉዲት ካሣ ሉከፈላት ይገባል ብለናል።
7/ ለህፃን ጀሲካ ማንደፍሮ ሉከፈላት የሚገባትን የካሣ መጠንና የሟች የቀብር ሥነ ሥርዓት ማስፈፀሚያ መጠንን በተመለከተ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን በመመርመር ተገቢውን ይወስን ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
8/ በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.