No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ዲንዱቦሩ ዩኒቨርስቲ ኮላጅ - ጠበቃ እስክንድር ዘውዳ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡- 1/ ተክለ ኡርጋ ኢደኤ - ቀረቡ።
2/ ቶልሳ መገርሳ ባልቻ - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሾች የነበሩት የአሁኖች ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት የስራ ውላችን ከህግ ውጭ አቋርጦብናል በማለት ነው ። አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ የሥራ ውለ የተቋረጠው የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ተማሪዎችን ተቀብል ማስተማር ባለመቻለ ነው በመሆኑም ከሕግ ውጪ የተፈፀመ ነገር የለም በማለት ተከራክረዋል። እንደ ክርክሩ ያስረዲል ያለውን ማስረጃ አያይዞ ስለማቅረቡ ክሱን ባስተናገደው ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ተገልጾአል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክርም ከሰማ በኋላ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ በማለት ውሳኔ ሰጥቶአል። ከዚህ ውሳኔ በመነሳትም አመልካች የስራ ውል ከሕግ ውጪ ሲቋረጥ ሉከፍለ የሚገባቸውን ክፍያዎች ለተጠሪዎች ይከፈል ብልአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ውድቅ አድርጏአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መስከረም 15 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የስራ ውለ ከሕግ ውጪ ነው የተቋረጠው በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪዎች በአመልካች ኮላጅ በመምህርነት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረ ሲሆን፣ አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ተቀጥረው ሲሰሩበት የነበረው የስራ ክፍል በበቂ ምክንያት ተሰርዞአል። ሥራው የለም በማለት ነው ።ተጠሪዎችም ክሱን የመሰረቱት ሥራው ስላለ ወደ ስራችን እንመለስ በማለት ሳይሆን ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነውና ልዩ ልዩ ክፍያዎች ይከፈለን በማለት ነው። በአሰሪና ሰራተኞች ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28(1)(መ) እንደተመለከተው ሰራተኛው ጉዲይ የያዘው የስራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲቀርብና ሰራተኛውን ወደ ስራ ቦታ ማዛወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ የሥራ ውለ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ /የማስተማር ስራ/ መንግስት ባወጣው መመሪያ መሰረት መሰረዙን በማስመልከት አመልካች ተከራክረዋል። ተጠሪዎችም ይሄንኑ አልካደም መንግስት ያወጣው መመሪያ ከመስከረም ወር 2000 ዓ.ም ጀምሮ ከግል ትምህርት ተቋሞች የሚመረቁ ዔጩ መምህራን በመንግስት የትምህርት ተቋ ሞች እንደማይቀጠሩ መታዘዙን የሚያመለክት ነው። ተጠሪዎች ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩትም እጩ መምራንን ማሰልጠን ነው። መመሪያው ከወጣ በኋላ ግን ለመሰልጠን ተማሪ ሉመዘገብ አልቻለም። ይህ ማለት ደግሞ ተጠሪዎች ይሰሩበት የነበረው የሥራ መደብ የለም ማለት ነው።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች እንደመልሱ ያስረዲልኛል ያለውን ማስረጃ ከመልስ ማመልከቻው ጋር አያይዘን እንዲቀረበለት በውሳኔው ላይ ገልጿል። በልላ በኩል ደግሞ መዝገቡ ለቃል ክርክር በተቀጠረበት ዔለት ነገረ ፈጁ አልቀረበም፤ የሚል ምክንያት በመስጠትና ማስረጃ እንደላለው በመግለጽ አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ ሰጥቶአል። ቀደል ሲል እንደተመለከተው አመልካች በዋነኛነት የጠቀሰው ማስረጃ የመንግስት መመሪያ ነው። በመንግስት የሚወጡ ሕጏች እና መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ ወዘተ በግልጽ የሚታወቁ እንደመሆናቸው ፍ/ቤቶች (ዳኞች) ግንዛቤ የሚወሰደባቸው ናቸው። ተከራካሪ ወገን ለክርክሩ የሚጠቅመውን ሕግ ከአስረጅነት አላቀረበም በሚል ክርክሩን በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ደግሞ አመልካች ለሥራ ውለ ማስረጃ ስለማቅረቡ ፍ/ቤቱ በሚገባ መዝግቦለታል።
ጉዲዩ ለቃል ክርክር በተቀጠረበት ዔለት ነገረ ፈጁ ባለመቅረቡ ማስረጃው እንደላለ ተደርጎ ሉወሰድ አይችልም። ሲጠቃለል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ግንቦት 18 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. ሐምል 21 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ ሕግ ቁ 348 (1) መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የስራ ውል የተቋረጠው በሕጋዊ መንገድ ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።