No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 4ዐ3ዐ5 ታህሣሥ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኢትዮጵያ ፏልፕና ወረቀት አ/ማ - ነ/ፈጅ አብደልቃድር ተጠሪ፡- እነ አቶ ታመነ ጫላ
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲዩ የጀመረው በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሣሾች ሲሆኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበር።
ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት በተከሣሽ /አመልካች/ ላይ ባቀረቡት ክስ፤ አመልካች ተጠሪዎችን በጥበቃ የሥራ መደብ ቀጥሮ ሲያሰራቸው ቆይቶ ያለአግባብ ከሥራ ስላሰናበታቸው የሥራ መደባቸው በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ መሰረት መሆኑ ቀርቶ በአንቀጽ 9 መሰረት ቋሚ ሰራተኛ አድርጎ ወደ ስራቸው እንዱመልሳቸው ጠይቀዋል። አመልካችም ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ ጉዲዩን ለማየት ፍ/ቤቱ ስልጣን የለውም፣ የመክሰስ መብት የላቸውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቦ ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ሥራ ለማቃለል ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ ስራው ሲቃለል ማሰናበቱ አግባብ ነው፤ በመሆኑም ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ላይ ለምስ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የወረዲ ፍ/ቤቱን ውሣኔ አጽንቷል።
በዚህ ውሣኔ ላይ ተጠሪዎች ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች ተጠሪዎች የተቀጠሩት ሥራ ለማቃለል የተቀጠሩ መሆኑን ያላረጋገጠ በመሆኑ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ናቸው በማለት አመልካች የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎቸው ወደ ሥራቸው እንዱመልሣቸው በማለት ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታም ተጠሪዎች በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 1ዐ/1/ሐ/ መሰረት የተቀጠሩ ሲሆን ስራው ሲቃለል መሰናበቻው አግባብ ነው የሚል ነው። ይህ ችልትም የተጠሪዎች ስንብት ሕገ-ወጥ ነው የመባለን አግባብነት ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረጉ ተጠሪዎች ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተደምጧል።
ከመዝገቡ እና ከክርክሩ ሂደት ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት በጥበቃ የሥራ መደብ ሲሰሩ ቆይተው በመሰናበታቸው የተቀጠሩበት ሥራ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ቋሚ ሰራተኛ ሆነው ወደ ሥራ እንዱመለሱ መሆኑን ተገንዝበናል።
ከዚህም የተጠሪዎች ክስ ተጠሪዎች ቀድሞውኑ የተቀጠሩት ለተወሰነ ሥራ ወይም ጊዜ መሆኑን ነገር ግን ሥራው ቀጣይነት ስላለው በቋሚነት ለመቀጠር የጠየቁ መሆኑ ግልጽ ነው። ከአመልካች ክርክርና ማስረጃም ተጠሪዎች በአ/ቁ.
337/96 አንቀጽ 1ዐ/1/ሐ/ መሰረት መቀጠራቸውን ተገንዝበናል። በእርግጥ የአንድ የሥራ ውል በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 1ዐ ሥር በተመለከቱት ሁኔታዎች የተደረገ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር የሥራ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል፤ የሥራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ መደረጉን የማስረዲት ሸክም ያለበት ደግሞ አሰሪው ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎች የተቀጠሩት ለተወሰነ ጊዜ መሆኑን የፈረሙትን ውል በማቅረብ አስረድቷል። የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ የሰጠው ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው የሥራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ አልተደረገም በሚል ሣይሆን በእርግጥም አመልካች ተጠሪዎችን ሥራ ለማቃለል የቀጠራቸው ለመሆኑና ያሰናበታቸውም ሥራው በመቃለለ መሆኑን አላስረዲም በማለት ነው። ነገር ግን ተጠሪዎች ለተወሰነ ጊዜ ሥራ ለማቃለል መቀጠራቸው ውለ በሚገባ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ የሥራ ውላቸው በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ መሆኑ ቀርቶ በአንቀጽ 9 መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ እንዱሆን መጠየቃቸው የተቀጠሩት አመልካች እንዲለው ሥራ ለማቃለል መሆኑን ያውቁ እንደነበርና በወቅቱ አመልካችና ተጠሪዎች የነበራቸው ሃሣብ ይኸው መሆኑን በሚገባ ያመለክታል።
በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪዎች ሥራ ለማቃለል የተቀጠሩ ላለመሆኑ ያስረደት ነገር የለም።
ተጠሪዎች ሥራው ቀጣይነት አለው በማለት ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተ ምንም እንኳን ስራው የአሰሪው ቋሚ ስራ ቢሆንም እንኳን መብዛት የሚኖርበት ጊዜ ሥራን ለማቃለል ለተወሰነ ጊዜ የሥራ ውል መፈፀም የሚቻል መሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 1ዐ/1/ሐ/ የሚፈቅድ በመሆኑ የተጠሪዎች ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በመሆኑም ተጠሪዎች የተቀጠሩት ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ሥራ ይመለሱ በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 67773 በ14/11/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የምስ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13ዐ61 በዐ5/ዐ2/2ዐዐዐ የሰጠውና የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16ዐ81 በ17/ዐ8/99 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ተጠሪዎች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 1ዐ/1/ሐ/ መሰረት ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ በመሆኑ ጊዜው ሲያልቅ መሰናበታቸው ሕጋዊ በመሆኑ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.