No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 02 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድርመሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ኩመላ በጅሣ- ቀረቡ ተጠሪ፡- ብሕራዊ አስጏብኚና ጏዞ ወኪል ድርጅት - ነ/ፈጅ በርሃኑ ከፍነው ቀረቡ መዝገቡን መረምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰሪተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ድርጅት ከሚያዘያ 29 ቀን 1975 ዓ.ም ጀምሮ በሹፋርነት ሙያ ለ24 ዓመታት ማገልገላቸውንና ያገኙት የነበረውን የደመወዝ መጠን ጠቅሰው ተጠሪ ያላግባብ የስራ ውለን በማቋረጥ ያሰናበታቸው መሆኑን በመዘርዘር የስንብት ክፍያ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የ6 ወራት ደመወዝ ካሣ ክፍያ እና ስራ ሰርተው ያልተከፈላቸው የ14 ቀን ደመወዝ እንዱከፈላቸው እንዱሁም የምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ በአሁኑ ተጠሪ ላይ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። ተጠሪ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው መልስ የአመልካች የሥራ ውል የተቋረጠው በተከታታይ አምስት ቀን ከሥራ ገበታቸው በመለየታቸው በሕጉ አግባብ መሆኑን የሚገባቸው ክፍያ አለመኖሩንና በድርጅቱ ውስጥ 24 አመታት ያገለገለ በመሆኑ የአገልግልት ጡረታ አበል በእድሜ ልክ ስለሚከፈላቸው የአገልግልት ካሣ ክፍያ የመጠየቅ መብት የላላቸው ሆኑን በመዘርዘር ተከራክሯል። ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የተጠሪ እርምጃ በማስረጃ ያልተደገፈ መሆኑን በመጥቀስ የሥራ ስንብቱ አላግባብ መሆኑን በመግለጽ የአሁኑ አመልካች የጡረታ መብት ተጠቃሚ በመሆናቸው የስንብት ክፍያ እንደማይገባቸው የ14 ቀን ደመወዝ እንደሚገባቸው ይህ ክፍያ ለዘገየበት የሁለት ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸውና የምስክር ወረቀትም እንዱሰጣቸው ዘርዝሮ ከወሰነ በኋላ የስንብት ወይም የጡረታ መብት ለአመልካች አንደ ካልተፈፀመ አቤቱታ የማቅረብ መብታቸውን ጠብቆላቸዋል የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኝት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ታህሳስ 16 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ የስር ፍ/ቤት የጡረታ መብት የመከልከል ሥልጣን ሣይኖረው በዚህ ረገድ የሰጠው ውሣኔ እርስ በራሱ የሚጋጭና ህጋዊ መሰረት የላለው መሆኑን ስንብቱን ህገ-ወጥ ነው ብል ከወሰነ በኋላ በህጉ መሰረት ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎችን ማለፈ ያላግባብ መሆኑን በመዘርዘር ውሣኔው ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርቦ ሐምል 07 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል። በመልሱ ላይም የአመልካች የስራ ስንብት ህገ-ወጥ ነው ተብል አለመወሰኑን የስር ፍ/ቤት የአመልካችን ዘላቂ የጡረታ መብት ተጠቃሚነት ከልክል የሰጠው ውሣኔ አለመኖሩን በመዘርዘር አመልካች የስር ፍ/ቤት ያልሰጠውን ውሣኔ እንደሰጠ በማስመሰል እንዱሁም የማይገባቸው ክፍያ ስር ፍ/ቤት ላይ ያልነበረን ጭብጥ በማንሣት እንዱከፈላቸው መጠየቃቸው ያላግባብ በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካች በበኩላቸው ሐምል 30 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የስር ፍ/ቤት አመልካች ከሥራ የተሰናበቱት ያላግባብ ነው በማለት ከወሰነ በኋላ የካሣ ይከፈለኝ ጥያቄውን ማለፈና በስንብት ክፍያ ላይ የሰጠው ውሣኔ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመርመር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው የአመልካች የስራ ስንብት ያላግባብ ነው ተብል በስር ፍ/ቤት መወሰኑን ነው ተጠሪ ለዚህ ችልት የጽሐፍ መልስ ሲያቀርብ የአመልካች የስራ ስንብት ህገ-ወጥ ነው በሚል ውሣኔ አለመሰጠቱን የገለፀ ቢሆንም በመ/ ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም በስር ፍ/ቤት የተሰጠው የውሣኔ ግልባጭ ግን የስራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በሚል የተሰጠው ውሳኔ የለም የሚለው ክርክር መሰረት የላለው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለናል።
የአመልካች የስራ ስንብት ህገ-ወጥ ነው ከተባለ ጉዲዩ እልባት ሉያገኝ የሚገባው ከህግ ውጪ የሆነ የስራ ውል ማቋረጥ የሚያስከትላቸው ውጤቶችን የሚገዛውን የህጉን ዘርፍ ባገናዘበ መልኩ ነው።
በያዝነው ጉዲይ አመልካች ከሥራ የተሰናበቱት ያላግባብ መሆኑን ገልፀው የተለያዩ ክፍያዎች በተጠሪ እንዱከፈል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው የስራ ስንብቱ ህገ-ወጥ መሆኑ ተገልጾ ከተወሰነ በኋላ እንዱከፈላቸው የተደረገው አመልካች የጠየቋቸው ክፍያዎች ሁለ አይደለም። በአመልካች ከተጠየቁት ክፍያዎች ውስጥ የካሣ እና ይሄው ካሣ የዘገየበት የ3/ሦስት/ ወር ደመወዝ ክፍያ በስር ፍ/ቤት በዝምታ የታለፈ ናቸው። ይሁን እንጂ የስራ ውል ከህግ ውጪ ነው የተቋረጠው እየተባለ ውጤቱ በግልጽ ዲኝነት ተጠይቆበት በዝምታ ማለፈ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን ዓላማ የሚፃረር ነው። የስራ ውል ከህግ ውጪ ሲቋረጥ የሚያስከትላቸውን ውጤቶች ህጉ የደነገገው ኢንደስትሪያላዊ ሰላምን በመጠበቅ ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ እና ያላግባብ የሚባረርን ሰራተኛ ለመካስ ነው። በመሆኑም የስራ ውል ከህግ ውጪ መቋረጡ ከተረጋገጠ የኢንደስትሪውን ሰላም የመጠበቅና የሰራተኛውን የመካስ መብቱን ህጉ ዓላማ ማድረጉን ግንዛቤ ውስጥ ለማስገባት ዲኝነት ላሰጥ ይገባል በዚህ ረገድ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ተግባራዊ የሚደረጉትም ግልጽ ዲኝነት መጠየቁን አግባብነትና ብቁነት ያለው ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው።
እጃችን ወደተያዘው ስንመለስም አመልካች ሉከፈለኝ ይገባል የሚሎቸውን ክፍያዎች ዘርዝረው አቅርበው ተጠሪ ክፍያዎቹ አይገባም የሚልበት ምክንያት በዋናነት የስራ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ሲሆን የአመልካች የአገልግልት ጡረታ አበል የማግኘት መብት በህጉ የተጠበቀ በመሆኑ የአገልግልት ክፍያ ሉያገኙ አይገባም በማለትም ጭምር ነው።
ይሁን እንጂ የአመልካች የስራ ስንብት ባግባቡ አይደለም ተብል ተወስኗል። እንዱሁም አመልካች የ24 ዓመታት አገልግልት ያላቸው ቢሆንም በጡረታ ህግ የተመለከተውን መደበኛ የጡረታ ዔድሜ ላይ ደርሶ ከስራ የተገለለ መሆኑ አልተረጋገጠም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ አመልካች የስራ ስንብት ክፍያ የማያገኙበት ህጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2(ሰ) ድንጋጌ ያገናዝባል። የስር ፍ/ቤት የስንብት ወይም የጡረታ መብት አንደ ካልተፈፀመ አመልካች አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለት መወሰኑ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገርና የተጠየቀውን ዲኝነት እንዱሁም የዲኝነት አሰጣጥ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም።
በአጠቃላይ የአመልካች የስራ ውል የተቋረጠው በህገ-ወጥ መንገድ ነው እየተባለ በአመልካች የተጠየቁት ክፍያዎች ውስጥ የካሣ ክፍያና ይህው ክፍያ ለዘገየበት ጊዜ እና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ጥያቄዎች በዝምታ መታለፊቸውና የስራ ስንብት ክፍያ በአማራጭ መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 05 ቀን 2000 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪ ለአመልካች የስራ ስንብት ክፍያ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የሦስት ወር ደመወዝ ክፍያው ለዘገየበት የ3(ሦስት) ወር ደመወዝ የስራ ውል ከህግ ውጪ ስለተቋረጠ የ6(ስድስት) ወር ደመወዝ ስራ ተሰርቶ የልተከፈላቸው የ14 ቀን ደመወዝ ይከፈል ብለናል የምስክር ወረቀትም ይሰጣቸው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል
No topics extracted.