No summary available.
ታህሣሥ ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ድካምየለህ ጥበቡ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አርሾ የሕክምና ላብራቶሪ ኃላ/የተ/የግል ማኀበር - ጠበቃ ጌታቸው ብሩ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች መስከረም 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ከላልች ከሣሾች ጋር ጽፈው ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን የሥራ ውል የጡረታ ዔድሜ ደርሷል በሚል ምክንያት መቋረጡን ገልፀው በድርጅቱና በሰራተኛ ማኀበሩ መሃከል በተደረገው የሕብረት ስምምነት በፈቃደ ሥራ የለቀቀ ሰራተኛ ፕሮቪደንት ፈንድና የሥራ ስንብት ክፍያ እንደሚያገኝ ስለሚደነግግ ተጠሪ ይህንኑ እንዱፈጽም በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ፈቃደኛ ሣይሆን መቅረቱንና መከልከለን ጠቅሰው የሥራ ስንብት ክፍያና ክፍያ ለዘገየበት ክፍያ ብር 2ዐ,189.00 /ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር/ ተጠሪ እንዱከፍል ይወስንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪም አመልካች ዔድሜያቸው ለጡረታ በመድረሱ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ተፈጽሞላቸው በሕብረት ስምምነቱ መሰረት ከሥራ የተሰናበቱ በመሆኑ የስራ ስንብት ክፍያ ጥያቄው ሉፈፀም እንደማይገባ፣ ለአመልካቹ ተገቢው ክፍያና ጥቅማጥቅም የተፈፀመላቸው በመሆኑ ክፍያ ለዘገየበት ጥያቄ አላፉነት እንደላለበት በመግለጽ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም አመልካች በጡረታ የተሰናበቱ መሆኑን አምነው የተከራከሩ ከመሆኑ እና በሕብረት ስምምነት መሰረት የስራ ስንብትና የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ የሚፈፀመው በፈቃድ ለለቀቀ ሰራተኛ ብቻ ነው በማለት የሚደነግግ በመሆኑ እንዱሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ሰ/ መሰረት የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ በጡረታ የተገለለ ሰራተኛ የስራ ስንብት የማይፈፀምለት መሆኑን የሚደነግግ ነው የሚለትን ምክንያቶች ጠቅሶ የአመልካችን የሥራ ስንብት ክፍያና ክፍያ ለዘገየበት ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሚያዝያ 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ የበታች ፍ/ቤቶች ከጡረታ በኋላ ጡረተኛው ከላላ አሰሪ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት ሲቋረጥ ያለውን የሕግ ከለላ እና በሕብረት ስምምነት ለሰራተኛው የበለጠ መብት የሚሰጥ ከሆነ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት መፈፀም ያለበት መሆኑን ባላገናዘበ መልኩ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት በመሆኑ ታርሞ አመልካች ስራቸውን በራሣቸው ፈቃድ የለቀቁ መሆኑ ተረጋግጦ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያ ከወጪና ኪሣራ ጋር እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ሉተይ ይገባል በመባለ ተጠሪ እንዱቀርብ ተደርጎ ሐምል 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሱን ጠበቃቸው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ አመልካች በሁለት መ/ቤቶች ቅጥር እንደፈጽሙ አድርገው ያቀረቡት ክርክር አዱስ በመሆኑ ሥነ ሥርዓታዊ አይደለም፣ የስራ ስንብት ክፍያም አመልካቹ በጡረታ የተገለለና የጡረታ መብትም ተጠቃሚ በመሆናቸው ሉጠየቅ የማይገባ መሆኑን በመዘርዘር የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
የአመልካች የመልስ መልስ የማቅረብ መብት ከታለፈ በኋላም ግራ ቀኙ ማጣሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው መልሣቸውን እንዱሰጡ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የአመልካች የሥራ ስንብት ክፍያ ጥያቄ ውድቅ የተረገው ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
በክርክሩ ሂደት አመልካች በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተቀጥረው ሲያገለግለ ቆይተው እድሜያቸው ሃምሣ ዓመት ሲሞላ በፈቃዲቸው ስራውን ለቀው ለዚህ አገልግልታቸው የጡረታ መብት ተጠቃሚ መሆናቸው፣ ከዚህ መስሪያ ቤት በጡረታ ከተገለለ በኋላ በተጠሪ መስሪያ ቤት ከሐምል 19 ቀን 1989 ዓ.ም. ጀምሮ ተቀጥረው ለአስር ዓመታት ያሕል አገልግለው እድሜ ለጡረታ ደርሷል በሚል ምክንያት ከነሐሴ 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ መገለላቸው የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው።
ተጠሪ አመልካች በሁለት መ/ቤቶች ሁለት የተለያዩ የቅጥር ውልችን የፈፀሙ መሆኑንና በዚህ ረገድ ያለውን የሕግ ከለላ በሰበር አቤቱታቸው መጥቀሣቸው በሥር ፍ/ቤት ያልተነሣ አዱስ የክርክር ነጥብ ነው በማለት ያነሱትን መቃወሚያ ስንመለከተው አመልካች የጡረታ መብት ተጠቃሚነታቸው የተጠበቀው በተጠሪ መ/ቤት ላበረከቱት አገልግልት መሆኑ ያልተረጋገጠ በመሆኑ፣ አመልካች በሁለት የተለያዩ መ/ቤቶች ሁለት የተለያዩ የቅጥር ውልችን መፈፀሜ እየታወቀ በዚህ ረገድ ያለው የሕግ ከለላ ግንዛቤ ውስጥ ሣይገባ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መስጠታቸው ስህተት ነው። በማለት በሰበር አቤቱታው ላይ መግለፃቸው በይዘቱም ሲታይ በሥር ፍ/ቤት ያልተነሣ የክርክር ነጥብ ነው።
ለማለት የሚያስችል ሁኖ አልተገኘም። በመሆኑም የተጠሪ ጠበቃ በዚህ ረገድ ያቀረቡት መቃወሚያ ተቀባይነት የላለው ሆኖ ተገኝቷል።
ወደ ዋናው ጉዲይ ስንመለስም፤ አመልካች ከተጠሪ ድርጅት የተሰናበቱት የጡረታ ዔድሜ ስለደረሰ ሕጉም ስለሚያስገድዲቸው ጠይቀው ጡረታ ወጡ እንጂ ሥራ መልቀቅ ፈልገው አይደለም በማለት የተጠሪ ጠበቃ ያልቀረቡት መከራከሪያ ሲታይ አመልካች ከጥቁር አንበሣ ሆስፒታል በጡረታ የተገለለ መሆኑ እየታወቀ በተጠሪ መስሪያ ቤት የተቀጠሩ መሆናቸው ጋር ተዲምሮ ሲታይ ተቀባይነት የላለው ነው። በመሆኑም አመልካች በጡረታ ከተገለለ በኋላ በተጠሪ መ/ቤት ተቀጥረው ሲሰሩ ቆይተው ስራውን የለቀቁትን በገዛ ፈቃዲቸው እንጂ የጡረታ ዔድሜ ደርሶ ሕጉ የሚያስገድዲቸው ሆኖ አይደለም። አመልካች ከተጠሪ መ/ቤት ስራቸውን የለቀቁት ዔድሜያቸው የጡረታ ዔድሜ ደርሶ ነው ቢባልም የጡረታ ዔድሜ የደረሰ ሰራተኛ የተጠሪን ጅርጅት ለመልቀቅ ከፈለገ ሉከለከል የሚችልበት ምክንያት የለም።
ስለሆነም አመልካች ከተጠሪ ድርጅት የተሰናበቱት በገዛ ፈቃዲቸው ውጪ በልላ ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት አመልካች በጡረታ የተሰናበቱ መሆኑን አምነዋል ወደሚለው ድምዲሜ መድረሱ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል።
አመልካች ስራቸውን የለቀቁት በገዛ ፈቃዲቸው ነው ከተባለ በተከታይ ላታይ የሚገባው ውጤቱ ነው። አመልካች በገዛ ፈቃደ ስራውን የሚለቅ የተጠሪ ሰራተኛ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት የመጠባበቂያ መዋጮውንና የአገልግልት ካሣውን ወዱያውኑ የማግኘት መብት ስላለው ያልተፈፀመልኝ የአገልግልት ካሣ ሉከፈለኝ ይገባል በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በበኩለ አመልካች የጡረታ ዔድሜ ደርሷቸው ከሥራ በሕጉ አግባብ የተለለ ከመሆኑም በላይ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ስለሆኑ የአገልግልት ካሣ ሉወስደ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሰረቱ አመልካች የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆኑት በተጠሪ ድርጅት ላበረከቱት አገልግልት አለመሆኑን ከላይ ተመልክተናል። በተጠሪ ድርጅት አዱስ የስራ ውል ፈጽመው ዔድሜያቸው ከስልሣ ዓመት በላይ እስኪሆናቸው ሰርተዋል። ዔድሚያቸው ስልሣ ዓመት ሲሞላቸውም በሕብረት ስምምነቱ መሰረት የጡረታ ዔድሜ ደርሷል በሚል ምክንያት ከሥራ እንዱገለለ ሣይደረግ ከተጠሪ ጋር ያላቸው የስራ ግንኙነት እንዱቀጥል መደረጉ አመልካች ሥራውን የለቀቁት የጡረታ ሕጉ እና የሕብረት ስምምነቱ ስለማያስገድዲቸው ነው የሚለው የተጠሪ ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ተጠሪ አመልካች የጡረታ መብት ተጠቃሚ በመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ሰ/ መሰረት የአገልግልት ካሣ ሉያገኙ አይገባም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ስንመለከተውም አመልካች የጡረታ መብት ተጠቃሚነታቸው የመነጨው ለተጠሪ ላበረከቱት አገልግልት ካለመሆኑም በላይ አዋጅ ቁጥር 494/98 ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ነሐሴ 1ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. በተደረገ ስምምነት የተጠሪን ድርጅት ለመልቀቅ የሚፈልግ ሰራተኛ የድርጅትን የመጠባበቂያ መዋጮውንና የአገልግልት ካሣውን በጣምራ የማግኘት መብት እንደለው በአንቀጽ 38/1/ ስር የተመለከተ በመሆኑ እና የሕብረት ስምምነቱ ከአሰሪና ሰራተኛ ሕግ የተሻለ ሁኖ ሲገኝ ደግሞ ተፈፃሚ ላሆን እንደሚገባ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 134/2/ ሥር የተደነገገ ስለሆነ የተጠሪ ክርክር በሕግ ፉት ተቀባይነት ሉኖረው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን የሥራ ግንኙነት በፈቃዲቸው የለቀቁ መሆኑ ተረጋግጦ እያለና የሕብረት ስምምነቱ ደግሞ ለፕሮቪደንት ፈንደና የአገልግልት ካሣ በአንድነት ሉያገኙ የሚገባ መሆኑን የሚደነግግ ሆኖ እያለ የሥር ፍ/ቤት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉም ሆነ የከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ ማጽናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22619 ጥር ዐ2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 63ዐ19 መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው እና የአመልካችን የአገልግልት ካሣና ክፍያው ለዘገየበት ክፍያ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ ለአመልካች የአገልግልት ካሣና ክፍያ ለዘገየበት ብር 2ዐ,189.00 /ሃያ ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር/ እንዱከፍል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.