No summary available.
ታህሣሥ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አበባ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግል ማህበር ነ/ፈጅ ምናለ በሪሁን ቀርበዋል ተጠሪ፡- ዓለምሰገድ ኃይለ አልቀረበም።
ጉዲዩን በመመርመር የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 03 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 62997 ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱሻርለት በመጠየቁ ነው።
የአሁኑ አመልካች በፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት የፍርድ ባለእዲ፣በፋደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ መልስ ሰጭ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ በፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት የፍርድ ባለመብት፣የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ደግሞ ይግባኝ ባይ በመሆን ተከራክረዋል።
የፍርድ ባለመብት የሆኑት የአሁኑ ተጠሪ ታህሳስ 29 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ለፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ቀደም ብል ማለትም በመ/ቁ. 36237 ከባለ እዲው ጋር ባደረጉት የስራ ክርክር ወደ ስራቸው እንዱመለሱ፣ውዝፍ ደሞዝና ወጪና ኪሳራ እንዱከፈላቸው ተወስኖላቸው እንደነበር በማስታወስ ወደ ስራ የመመለሱ ሁኔታ እንደማይፈልጉትና በምትኩ የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍለዋቸው ከስራ እንዱሰናበቱ ጠይቀዋል። የመጀ/ደ/ፍ/ቤቱም የፍርድ ባለመብቱ በፍርደ እንደሰፈረው በአመራጭ የጠየቋቸው ላልች ክፍያዎች ያልነበሩ በመሆኑና የአራት ወር የደሞዝ ክፍያ የተከፈላቸው በመሆኑ ወደ ሥራ ለመመለስ እንዲልፈለጉ በመቁጠርና የሚከፈላቸው ላላ ቀሪ ክፍያ የለም በማለት መዝገቡን ዘግቶ አስናብቷቸዋል።
ከላይ የሰፈረውን ትእዛዝ በመቃወምም የአሁኑ ተጠሪ ወደ ፋ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም ደቀም ብል በተፈረደልኝ መሰረት መልስ ሰጭው ምክንያት እየፈጠረ ወደ ስራ ሳይመልሰኝ በመቅረቱና የስራ ግንኙነታችን በመሻከሩ ወደ ስራ መመለሴ ቀርቶ በካሳ ልሰናበት በማለት ላቀረብኩት ጥያቄ ስራውን እንዲልፈለኩት በመቁጠር ያለምንም መፍትሄ መዝገቡ መዝጋቱ ተገቢ አይደለም የሚል ነው።
መልስ ሰጭ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በሰጡት መልስም በውሳኔው መሰረት ተፈጽሟል፤የተወሰነላቸው ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሎቸዋል፤ ወደ መደበኛ ስራቸውም እንዱመለሱ የመኪናው አረካካቢ ተመድቦላቸው እያለ የተዘጋውን መዝገብ እንደገና አንቀሳቅሰው ካሳ ተከፍልኝ ልሰናበት ማለታቸው አላግባብ ነው ብሎል።
ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍ/ቤትም በኮ/ቁ. 62997 ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ይ/ባይ በስር ፍ/ቤት በዋና ክርክራቸው በአማራጭ በካሳ ልሰናበት ብለው ባይጠይቁም ውሳኔው ከተሰጠ በኋላ በአፈፃፀም መጠየቅ እንደሚችለ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43/3/ በግልጽ የተመለከተ ስለሆነና የአፈፃፀም መዝገቡ ሳይዘጋ ወደ ስራ መመለሳቸው ቀርቶ ካሳ ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ የጠየቁ ሰለሆነ ወደ ስራ ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆኑም በማለት የስር ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ በመሻር በፍርደ መሰረት ውዝፍ ደሞዝ እንደተከፈላቸው በማረጋገጥና ይህንን ውዝፍ ደሞዝ ይዘው ወደ ስራቸው ይመለሱ ብሎል።
የአሁኑ አመልካችም ከላይ የሰፈረውን የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ሰኔ 03 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ወደዚህ ሰበር ችልት አቅርቧል፤መሰረታዊ ይዘቱም በፍርደ መሰረት የአራት ወራት ውዝፍ ደሞዝና ወጪና ኪሳራ ለተጠሪው በመክፈል ስራቸውም እንዱጀምሩ ደብዲቤ ጽፈንላቸው እያለና በዚህ ደረጃም ፍርደ የተፈፀመ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ከዚህ በኋላ ተጠሪው ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ ካሳና ላልች በፍርደ ያልተፈረደላቸውን ክፍያዎች ተከፍሎቸው ከስራ እንዱሰናበቱ ያቀረቡት ጥያቄ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በትክክል የወሰነውን ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በይግባኝ አከራክሮ ወደ ስራ ይመለሱ ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤በአዋጁ አንቀጽ 43/3/ መሰረት ተጠሪው ጥያቄውን ማቅረብ የሚገባው ዋናውን ፍርድ ለሰጠው ፍ/ቤት እንጂ የአፈፃፀም ክርክር ለሚያካሂደው አይደለም፤በመሆኑም የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ይሻርልኝ የሚል ነው።
ተጠሪዋ ሐምል 11 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ይዘቱም ያቀረብኩት ጥያቄ አዋጅ ቁ.
377/1996 አንቀጽ 43/3/ መሰረት በማድረግ በዋናው ጉዲይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላም ቢሆን ወደ ስራ በመመለስ ፈንታ ካሳ ተከፍልኝ ልሰናበት ማለት እችላለሁ፤ጥያቄዬ ያቀረብኩት በተዘጋ የፍርድ አፈፃፀም መዝገብ ሳይሆን በቀጠሮ ላይ ወይም በሂደት በነበረ የአፈፃፀም መዝገብ ውስጥ ነው፤ወደ ስራ መመለሱ ይቅርብኝ ያልኩት በመካከላችን ያለው የስራ ግንኙነት የተባላሸ መሆኑ ስለተገነዘብኩኝ ነው፤አመልካች በስር ፍ/ቤት ባደረጋቸው ክርክሮችም ካሳ ተከፍልኝ እንድሰናበት ፍላጏቱ እንደነበር ነው፤አመልካች ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነው።
የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እየተዘረዘረ እንደመጣው ሲመስል ተጠሪው ወደስራቸው እንዱመለሱ ማድረጉ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ሉከፈላቸው የሚገባ ክፍያስ ምንድን ነው ? የሚለትን መሰረታዊ ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ መረዲት እንደሚቻለው የአሁኑ ተጠሪ ቀደም ብል ማለትም በመ/ቁ. 36237 በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋና ጉዲይ በቀረበው ክስ መሰረት አመልካች ወደ ስራ እንዱመልሰው፣የአራት ወራት ውዝፍ ደሞዝ እንዱከፈለው እና ወጪና ኪሳራም እንዱከፈለው በተወሰነለት መሰረት የተጠቀሱት ክፍያዎች አመልካች ለተጠሪው እንደከፈለና ወደ ስራው እንዱመለስም በደብዲቤ አሳውቆት በርክክብ ደረጃ አያለ ተመልሶ ወደ ፋ/መ/ደ/ፍ/ቤቱ በመቅረብ ወደ ስራው ከመመለስ ይልቅ ካሳ የስንብት ክፍያና ላልች ክፍያዎች ተከፍለውት ከስራ እንዱሰናበት እንደጠየቀ ነው። ይህ ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 43/3/ ከሰፈረው አኳያ ሲታይ ልዩነት ያለው ነው። በተጠቀሰው አንቀጽ የተቀመጠው መብት ተግባራዊ የሚሆነው ተጠሪው በፍርደ መሰረት የተወሰነለትን ውዝፍ ደሞዝና ላልች ክፍያዎች ሳይወስድ ቢሆን ኖሮ ነው፣በዚህ ጉዲይ ግን ተጠሪው በፍርደ መሰረት ወደ ስራው እዱመለስ ወስኖ በፍርደ የተወሰኑለትን ክፍያዎች ከተቀበለ በኋላ ነው፤ስለሆነም በፍርደ መሰረት መብቱ ከተፈጸመለት በኋላ በአዋጅ አንቀጽ 43/3/ መሰረት ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ የተለያዩ ክፍያዎች ተከፈለውት በአማራጭ እንዱሰናበት የቀረበ ጥያቄ ነው ማለት አይቻልም፤በመሆኑም ተጠሪው ስራ መስራት እንደማይፈልግ ገልጾ እያለ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ስራው ይመለስ ብል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 37264፣ጥር 08 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል፣ይፃፍ።
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 62997፣ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
ተጠሪው ካሳና የስራ ስንብት ክፍያ ተከፍልት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43/3/ መሰረት ከሥራው እንዱሰናበት የጠየቀው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 36237 ፣
No topics extracted.