No summary available.
የሰ/መ/ ታህሣሥ 16 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብዱልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡ ሰላም የቴክኒክና የሙያ ማሰልጠኛ ማዔከል ነ/ፈጅ በቀለ ነዱ ቀረቡ ተጠሪ፡- ከበደ ሰይፈ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና በመዝገብ ሚያዝያ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሚያዝያ 28 ቀን 2000 ዓ.ም ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በመጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርበው ከሚያዚያ ወር 1993 እስከ መስከረም 25 ቀን 1999 ዓ.ም በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥሮ ከአመልካች ድርጅት ከማገልገል ላይ እያለ አመልካች አላግባብ የሥራ ውለን በማቋረጡና ከሥራ በማሰናበቱ ፍርድ ቤቱ ወደ ሥራ እንዱመለስ ይወሰንልኝ ወደ ሥራዬ የማልመለስ ከሆነ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን እንዱከፍል ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክተዋል። የአሁን አመልካች ሥር በከሳሽነት ቀርቦ ተጠሪ ከሥራ የተሰናበተው በየዔለቱ የዘብ ሥራውን ሲያከናውን የቅርብ አለቃውን ትእዛዝ የማይቀበል በመሆኑ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ በቀርብ አለቃው ላይ በመዛቱና የተለያዩ የፅሁፍና የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ሉስተካከለና ሥራቸውን በአግባቡ ሉያከናውኑ ባለመቻላቸው ነው። ለተጠሪው (ከሳሽ) ሉፈፀም የሚገባው ክፍያ የለም በማለት ተከራክሯል። የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች በየጊዜው ለተጠሪ ጽፋአቸዋለሁ ከሚላቸው የጽሐፍ ማስረጃዎች ውጭ ተጠሪ በሥራቸው ላይ አንባጓሮ የፈጠሩ መሆኑን የሚያሣይ ማስረጃ አላቀረቡም በማለት የተጠሪን ወደ ሥራ የመመለስ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ልዩ ልዩ ክፍያዎች ተከፍለዋቸው ተጠሪ ከሥራ እንዱሰናበቱ ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ አመልካችና ተጠሪ ቅር በመሰኘት ሁለቱም በየበኩላቸው ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበው ይግባኝ የሚያስቀርብ ህግ ወይም የፍሬ ገዲይ ምክንያት የለም በማለት በመዝገብ ሚያዘያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ተጠሪ ባቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ ላይ አመልካች መልስ እንዱሰጥ ካደረገ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ወደ ሥራ አይመለሱም ብል መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑ የስምንት ወር ደመወዝ ተከሎቸው ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመለሱ ወስኗል።
አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሥራ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የእኛን ይግባኝ በመሰረዝና የተጠሪን ይግባኝ በመቀጠል ተጠሪ ወደ ሥራ ቢመለስ የሚፈጠር ችግር የለም በማለት ተጠሪ ወደ ሥራ እንዱመለስ የሰጠው ውሣኔ መሰታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል ተጠሪ በበኩለ የሥር ፍርድ ቤት ካሣ ተከፍልት ይሰናበት በማለት የሰጠው ውሣኔ ህጋዊነት የላለው ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤት እኔ ያቀረብኩትን ይግባኝ በመመርመር ወደ ሥራ እንዱመለስ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ይሁንልኝ በማለት ሀምላ 18 ቀን 2000 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር በመልስ መልሱ ተከራክሯል። የሥር የክርክሩ አመጣጥ በዚህ ፍርድ ቤት በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እጅም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ የስምንት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደ ሥራ እንዱመለስ የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ተጠሪ ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፊት የፈፀሙ ስለመሆናቸው በቂና አሣማኝ ማስረጃ አላቀረበም በማለት የሥር ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም አመልካች አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም ጉዲዩ የፍሬ ጉዲይ ክርክርና የማስረጃ የምዘና እንጂ መሰረታዊ የሆነ የህግ አተረጓጏም ሆኖ ያላገኘነው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፊት የፈፀመ መሆኑን የሚያሣይ ማስረጃ የለም በማለት አመልካች የፈፀመው የሥራ ስንብት ህጋዊነት የላለው ነው በማለት ከወሰነ በኋላ የተጠሪ ወደ ሥራው መመለስ በአሰሪውና ሰራተኛው ግንኙነት ላይ የሚፈጥረውን አለታዊና አዎንታዊ ጎን በመመዘን ተጠሪ በአሰራና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን በመክፈል ከሥራ እንዱሰናበት ወስኗል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ምክንያት አላምንበትም ከማለት ውጭ የተጠሪ ወደ ሥራ መመለስ ከአመልካች ጋር መልካም ግንኙነት እና ጥሩ የሥራ ሁኔታ የሚፈጥር ስለመሆኑ የሰጠው ምክንያትና ለዚህም መነሻ የሆኑትን ነባራዊ እውነታዎችና መረጃዎች በዝርዝር አልገለፁም።
ተጠሪ በጥበቃ ሥራ የተሰማራና በእጁም ትጥቅ የሚይዝ ከመሆኑና ከቅርብ አለቆቹ ጋር በተለያየ ጊዜ ግጭት የሚፈጥር ስለመሆኑ ከመገለፁ አንፃር እና ከዚህም መነሻ ከሥራ ተሰናብቶ የቆየ መሆኑና አመልካች ይህንን በበቂ ማስረጃ ባለማስረዲቱና የሥራ ስንብቱን ህጉ የሚጠይቀውን ፍርሟሉቲ አሟልቶ ባለማከናወኑ ምክንያት አመልካች የፈረመው የሥራ ስንብት ህጋዊነት የጏደለው ነው እንደተባለ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ይዘት ለመረዲት ይቻላል። አንድ ሰራተኛ የሥራ ቅጥር አላግባብ ከተቋረጠ ፍርድ ቤቱ ወደ ሥራው እንድመለስ ወይም ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት ሲወሰን እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። ፍርድ ቤቱ ሰራተኛው ወደ ሥራው እዱመለስ የሚወሰነው ከሥራ ግንኙነት ጠባይ የተነሳ የሥራ ግንኙነቱ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር ሉከተል ይችላል ብል በማያምንበት ጊዜ መሆኑንና ከሥራ ባሕሪው የተነሳ የሥራ ግንኙነቱ ቢቀጥል ከፍተኛ ችግር ያስከትላል ብል ካመነ ሰራተኛው ወደ ሥራ ለመመለስ ቢፈልግ እንኳን ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት ማዘዝ እንደሚችል ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ አንፃር ስናየው የተጠሪ የሥራ ባህሪ የአመልካች ድርጅት ጠቅላላ ንብረት ፀጥታና ደህንነት መጠበቅ ከመሆኑ አንፃርና ይኸም በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የሚጠይቀውን ከፍተኛ የሆነ መተማመን የሻከረውና ግንኙነቱ ቢቀጥል በአመልካች ድርጅት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዲትና ችግር ሉያስከትል የሚችል በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን ወደ ጏን በመተው የተጠሪ ወደ ሥራ መመለስ ሉፈጥር የሚችለው ከፍተኛ ችግር ስለላለ ወደ ሥራ እንዱመለስ በለማት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የተገፀውን የህግ ድንጋጌ የሚቃረንና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 1 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ
No topics extracted.