No summary available.
ታህሳስ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋይ አስማማው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- ማታድር አዱስ ጎማ አክሲዮን ማህበር ጠበቃ ደረጀ ታፈሰወርቅ ቀርበዋል ተጠሪዎች፡-
ክርክሩ በዚህ ሰበር ችልት ላቀርብ የቻለው አመልካቹ ሚያዝያ 10/2000 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 15/2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረምለት በመጠየቁ ነው።
በአሁኑ ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ከሳሾች እንዱሁም የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን የተከራከረ ሲሆን ስር ከሳሾቹ ጥቅምት 30/1999 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ያቀረቡት መሰረታዊ ይዘቱ በተከሳሽ ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት ቅጥር በመፈፀም በወር ብር 288.66 (ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከስድሳ ስድስት ሣንቲም) እየተከፈለን ስንሰራ ከቆየን በኋላ ምንም አይነት ጥፊት ሳንፈፅም ጥቅምት 21/1999 ዓ.ም አላግባብ ከሥራ ስላሰናበተን ውዝፍ ደሞዛችን ከፍል ወደ ስራችን ይመልሰን ይህ ካልሆነ ግን የስንብት ክፍያ የማስጠንቀቂያ ክፍያ፣ ካሳ፣ ክፍያ ለዘገየበት እንዱሁም ከበቂ ወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለን ይወሰንልን የሚል ነው።
ስር ተከሳሹ በበኩለ ታህሳስ 20/1999 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ ይዘቱም የተጫኑ ጎማዎች እንዱያራግፈ ጥቅምት 19 ቀን 1999 ዓ.ም በቅርብ ኃላፉያቸው ሲታዘዙ በአድማ መልክ ተደራጅተው አናራግፍም እንዲለና በማግስቱም ይህ እምቢተኝነታቸው በመቀጠለ በህብረት ስምምነቱ አንቀፅ 4.4 ተራ ቁጥር 5 መሰረት ከስራ ሉሰናበቱ ችለዋል፤ የከሳሾቹ የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ስላልሆነ የሚከፈላቸው ክፍያ የለም ተብል ክሳቸው ውድቅ ይሁንልኝ የሚል ነው።
የስር ፍርድ ቤቱም በግራ ቀኙ ወገኞች መካከል የቃል ክርክር አካሂዶል፤ የግራ ቀኙ ወገኖች ምስክሮችም ሰምቷል፤ የተገኘው ውጤትም ከሳሾቹ ጎማውን አናራግፍም ያለት እሁድ እለት እንደነበርና በዚሁ ጊዜም በተቋሙ ውስጥ በተፈጠረው የስራ ጫና ምክንያት የትርፍ ሰዓት ክፍያ እየተከፈላቸው ስራቸውን በማከናወን ላይ በነበሩበት ሁኔታ ስለነበርና ስራ በዝቶብናል በሚል ምክንያት ነው የሚል ነበር፤ ፍ/ቤቱም ይህንን ሃቅ ከተገነዘበ እና ተከሳሹም የጎማውን ማራገፍ እስከ ሰኞ ድረስ አቆይቶ አሁንም እንዱያራግፈት ከሳሾችን መጠየቁ በአዋጅ ቁ 337/1996 በአንቀፅ 67 የተመለከቱትን ምክንያቶች እንዲልነበሩ ያሳያል በማለት በአጠቃላይ ከሳሾቹ ስራ ለመሥራት አልፈለጉም ተብል በተከሳሽ የተወሰደው ከስራ የማሰናበት ተግባር አግባብነት ያልነበረው በመሆኑ እና ከሳሾቹ በአዋጁ አንቀፅ 10 መሰረት የተቀጠሩ መሆናቸው ማህደራቸው ስለማይገልፅ ተከሳሹ የአዋጁ አንቀፅ 43(4) (ሀ)”ን” መሰረት ያደረገ ካሳ ለከሳሾቹ ሉከፍላቸው ይገባል፤ እንዱሁም የስንብትና የማስጠንቀቂያ ጊዜም ክፍያ ጨምሮ ይክፈል በማለት ወስኗል።
ከላይ በሰፈረው የፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘትም ስር ተከሳሹ ወደ ፋ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙ ወገኖችን ካከራከረ በኋላ መጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም በኮ.መ/ቁ.60960 በሰጠው ፍርድ ስር ከሳሾቹ በስር ፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ በተከሳሹ ድርጅት ውስጥ በጉልበት ሰራተኛነት ተቀጥረው በመሥራት ላይ እያለ የኮንትራት ጊዜያቸው ሳያልቅ የስራ ውላቸው እንዲቋረጠባቸው የሚገልፅ በመሆኑና ይህ ደግሞ የስራ ግንኙነቱ ለተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚያሳይ በመሆኑ ሉከፈላቸው የሚገባ ካሳ በአዋጅ ቁ 377/1996 አንቀፅ 43(4)(ሀ) መሰረት ሳይሆን በአንቀፅ 43(4)(ለ) መሰረት ነው፤ የስንብትና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያዎች በተመለከተ ግን የስር ፍ/ቤቱ የሰጠው ፍርድ ተገቢ ነው በማለት የፋ/መጀ/ደ/ፍ/ቤቱ ውሳኔ አሻሽሎል።
ከላይ በሰፈረው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔም አመልካቹ ቅሬታ በማሳደር ሚያዝያ 10/2000 ዓ.ም በተፃፈ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም የተጠሪዎቹ የስራ ቅጥር ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው እስከተባለ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 35(2) መሰረት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያው በጊዜያዊ የቅጥር ውላቸው በተስማማነው መሰረት የ15 ቀናት ብቻ እንጂ አንደ የ2 ወር ደሞዝ አይደለም ተብል ይታረምልኝ የሚል ነው።
ተጠሪዎቹም መስከረም 27/2001 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው ከፍተኛው ፍርድ ቤቱ ክርክራችን በአግባቡ ሳያገናዝብ የስራ ግንኙነታችን በአዋጁ አንቀፅ 43(4)(ሀ) ሆኖ እያለ ወደ አንቀፅ 43(4)(ለ) መቀየሩ የህግ ስህተት ነው፤ አመልካች ባቀረበው አቤቱታ የኮንትራት ሰራተኞች እንደሆንን ቢገልፅም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 35(መ) መሰረት የሙከራ ጊዜያችን ያጠናቀቅን በመሆኑ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያው የሁለት ወራት ደሞዝ ክፍያ ላሆን ይገባል ተብል በከፍተኛው እና በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶቹ የተሰጠው ውሳኔ ህግን ያማከለ በመሆኑ ሉፀና ይገባዋል ብለዋል።
አመልካቹም ህዲር 08/2001 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልሱ ተጠሪዎች ቅጥራችን በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 43(4)(ሀ) እንጂ በአንቀፅ 43(4)(ለ) አይደለም በማለት እኔ በአቀረብኩት የሰበር አቤቱታ ሉከራከሩ አይችለም የራሳቸው የሆነ አቤቱታ ሉያቀርቡበት የሚገባ ነው፤ የኮንትራት ሰራተኞች መሆናቸው አምነው የተከራከሩ በመሆናቸው እና የኮንትራት ሰራተኛ ሉከፈለው የሚገባ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ በአዋጁ አንቀፅ 35(2) መሰረት በኮንትራት ውለ ላይ የተገለፀው ተብል በመደንገጉ በእኛ የኮንትራት ውል ላይ ደግሞ የ15 ቀናት ክፍያ ተብል በግልፅ የተቀመጠ በመሆኑ የተጠሪዎቹ መከራከሪያ ነጥብ የህግ ድጋፍ የለውም ብሎል።
ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ በተቀመጠው መልኩ ከተገነዘበ በኋላ ለተጠሪዎች ሉከፈላቸው የሚገባ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ስንት ነው የ2 ወር ደሞዝ ወይስ የ15 ቀናት ብቻ የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል ያለው የስራ ግንኙነት ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ፍርድ እንዱሁም እያንዲንደ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ከፈፀመው ስምምነት መረዲት ይቻላል፤
ሉከፈላቸው የሚገባ ካሳም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 43(4)(ለ) መሰረት ሉሰላ እንደሚገባ ነው። ተጠሪዎች በዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት መልስ የስራ ግንኙነታችን ለተወሰነ ጊዜ ስላልሆነ ሉከፈለን የሚገባ ካሳም በአዋጁ አንቀፅ 43(4)(ሀ) መሰረት መሆን ይገባል ቢለም የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ፍርድ በመቃወም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በላለበት ሁኔታ ክርክራቸው ተቀባይነት የለውም። በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል አከራካሪው ነጥብ ለተጠሪዎች ሉከፈላቸው የሚገባ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ መጠን በተመለከተ ነው፤ የግራ ቀኙ ወገኖች የስራ ግንኙነት በተወሰነ ጊዜ የተደረገ በመሆኑ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 35(2) መሰረት የሚሰላ ነው። ይህ አንቀፅም ተዋዋዮቹ ወገኖች በስምምነታቸው ባስቀመጡት መልክ እንደሚከናወን ስለሚገልፅና እያንዲንደ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በፈፀመው ስምምነት አንቀፅ 3.3 መሰረት የ15 ቀናት ደሞዝ ብቻ እንደሆነ ነው፤ የስምምነታቸው በዚህ መልክ ተገልጾ እያለ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የማስጠንቀቂያ ጊዜው ክፍያ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤቱ የወሰነውን የ2 ወር ደሞዝ ተቀብል ማለፈ የግራና ቀኙ ወገኖች የስራ ግንኙነት ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ መጋቢት 15/2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል፤ ይፃፍ።
በአመልካችና በእያንዲንደ ተጠሪ መካከል ያለው የስራ ግንኙነት ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ በመሆኑ ለእያንዲንደ ተጠሪ ሉከፈል የሚገባው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 44 እና በስምምነታቸው አንቀፅ 3.3 መሰረት የ15 ቀናት ደሞዝ ብቻ ነው ብለናል።
ሚያዝያ 20/2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የተላለፈው እግድ ተነስቷል፣ ይፃፍ።
ግራ ቀኙ ወገኖች በዚህ ፍ/ቤት ያካሄደትን ክርክር በሚመለከት ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
ክርክሩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ፍርደ በዛሬው ዔለት 07/05/2001 ዓ.ም በችልት ተነገረ።
No topics extracted.