No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 30 ቀን 2001 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገረ ፈጅ ወ/ሮ ኮከብ ስለሺ ተጠሪ፡- አቶ ሙላት ታረቀኝ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ በመጋቢት 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቀ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በከሳሽነት በመቅረብ ከታህሳስ ወር 1972 ዓ.ም ጀምሮ ተቀጥሮ በአመልካች ድርጅት ውስጥ የተለያየ ስራ ሲሰራ የቆየ መሆኑን ከገለፀ በኋላ ህዲር 23 ቀን 1998 ሃላፉነትህን አልተወጣህም የሚል ምክንያት በመስጠት አላግባብ ከሥራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ የሥራ ስንብቱን ውድቅ እንዱያደርግለት ጠይቋል። አመልካች በበኩለ በተከሳሽነት ቀርቦ የይርጋ የጊዜ ገደብ አልፎል፣ የሚልና ተጠሪ ሰራተኛ ሳይሆን የሥራ መሪ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለውም የሚል መቃወሚያ አቅርቧል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን መቃወሚያ በመቀበል ተጠሪ የሥራ መሪ መሆኑን በመግለጽ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት ዘግቶታል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ከግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጠሪ ምክትል የግምጃ ቤት ሐላፉ በመሆን ያገለገለው በጊዜአዊነት ስለሆነ በቋሚነት ተመድበው ያልሰሩበት የሥራ መደብ የሥራ መሪ ሉያሰኛቸው አይችልም በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት አከራክሮ እንዱወሰን በማለት መልሶለታል። አመልካች ይኸ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። ተጠሪ የሥራ መሪ ናቸው። በሥራቸውም የሚመሯቸውና የሚያስተደድሯቸው ሰራተኞች አለ። በምክትል ግምጃ ቤት ሃላፉነት የተመደቡት በጊዜያዊነት ቢሆንም ሙለ ሃላፉነቱን እና የሚያስገኘውን መብት ተረክበው እስከሰሩ ድረስ በጊዜያዊነት በመመደባቸው ብቻ ሰራተኛ አያደርጋቸውም። ስለዚህ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 377/1993 አንቀጽ 3/2/ሐ ድንጋጌና የህብረት ስምምነቱን አንቀጽ 14 የሚተላለፍ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ እኔ በቦታው ላይ ተመድቤ እየራ የነበረው በተጠባባቂነት ነው። የሰራተኛ ወገን እንጅ የአሰሪ ወገን አይደለሁም። አመልካች ለክርክር ያቀረበው የሥራ መዘርዝር ለእኔ ያልተሰጠኝና እኔ የማላውቀው ነው። አመልካች በመከራከሪያነት የሚጠቅሰው አስረኛውን የህብረት ስምምነት ሲሆን እኔ ሥራ ላይ በነበርኩ ጊዜ የነበረው ዘጠነኛው የህብረት ስምምነት ነው። በወቅቱ የሰራተኛ ማህበሩ ከፍተኛ ኃላፉ የነበርኩ ስለሆነ አመልካች ሥራ መሪ ነው ለማለት የሚያቀርበው ክርክር ተገቢነት የላለው ነው፣ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ያሰናብተኝ በማለት ተከራክሯል። አመልካች በጽሐፍ የመልስ መልስ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህ ችልት የአመልካችንና የተጠሪን የቃል ክርክር አዲምጧል። እንደዚሁም አመልካችና ሰራተኛ ማህበሩ የተስማሙበትን ዘጠነኛውን የህብረት ስምምነትና አስረኛውን የህብረት ስምምነት በማስቀረብ ተመልክቷል።
በሥርና በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች የሥራ መሪ ነው ወይስ ሰራተኛ? የሚለው ነጥብ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ተጠሪ በተጠባባቂነት ተመድበው ይሰሩበት የነበረው የሂሳብ ክፍል ረዲት ኃላፉ የሥራ ቦታ ላይ የነበረ መሆኑና ተጠሪም የክፍለን እንቅስቃሴዎች የመቆጣጠር የዔለት ከዔለት የሑሳብ ቁልፍችን መያዝና የሑሳብ ከፊዬችን የዔለት ተዔለት የሥራ ምደባ ፕሮግራም እንደሚያዘጋጅ ተጠሪ ተመድቦ ይሰራበት የነበረው የሥራ መደብ የሥራ መዘርዝር በማየት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህም ተጠሪ የሰራተኛነት ሳይሆን የሥራ መሪነት የሥራ ድርሻ የነበረው መሆኑን ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ በተጠባባቂነት ተመድቦ ይሰራበት የነበረው የሥራ መደብ ተጠሪ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ተፈፃሚነት በነበረው ዘጠነኛ የሕብረት ሥራ ስምምነት መሰረት የሰራተኛ የሥራ መደብ ሣይሆን የሥራ መሪ የሥራ መደብ መሆኑ በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 14 ንዐስ አንቀጽ 10 በግልጽ ተደንግጓል። ከዚህም ተጠሪ በተጠባባቂነት ተመድቦ ሲሰራበት የነበረው ምክትል የግምጃ ቤት /የሂሳብ ክፍል/ ኃላፉ የሥራ መደብ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 ንዐስ አንቀጽ 3/2/ሐ/ መሰረት የሥራ መሪ የሥራ መደብ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ በተጠባባቂነት የሚሰራበት የነበረው የሥራ መደብ የሥራ መሪ የሥራ መደብ ነው ከተባለ ተጠሪ በሥራ መደቡ ይሰራ የነበረው በቋሚነት ሳይሆን በተጠባባቂነት መሆኑ ተጠሪን ሰራተኛ ያሰኘዋል ወይስ አያሰኘውም? የሚለውን ነጥብ ማየት አስፈላጊ ነው። ተጠሪ በተጠባባቂነት ተመድበው ሲሰሩ ለቦታው የሚገባውን ጥቅማጥቅም የሚያገኙ እንደነበርና ለሥራው ሙለ ሀላፉነት ወስደው ይሰሩ እንደነበር በስርና በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያሳያል።
በአዋጅ ቁጥር 494/1998 ከተደረገው፣ ማሻሻያ መሰረት የሥራ መሪ ማለት በቋሚነት ብቻ ሣይሆን በአሰሪው በተሰጠው ውክልና መሰረት በአዋጁ አንቀጽ 3 ንዐስ አንቀጽ 2/ሐ/ የተዘረዘሩትን ተግባራት የሚያከናውን ነው። ከዚህ አንፃር ተጠሪ በቦታው ላይ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት በተጠባባቂነት መሆኑ ተጠሪ ሰራተኛ ናቸው ከሚለው መደምደሚያ ላይ የሚያደርስ ምክንያት ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ከላይ የተገለፁትን የህግ ድንጋጌዎች ሳያገናዝብ ተጠሪ ሰራተኛ ነው የሥራ መሪ አይደለም በማለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 15 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ብይን ፀንቷል ይፃፍ።
ተጠሪ የሥራ መሪ እንጅ ሰራተኛ ባለመሆኑ ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ 377/1996 በአዋጅ ቁጥር 494/1998 እንደተሻሻለ የሚታይ አይደለም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ታህሳስ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.