No summary available.
ታህሣሥ 14 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ማታድር አዱስ ጎማ አ/ማ - ጠበቃ ደረጀ ታፈሰወርቅ ቀረበ ተጠሪ፡- ደረጀ ኡመታ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የስራ ውላ ከሕግ ውጪ አቋርጦብኛል በማለት ነው። ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደስራው እንዱመለስ እንዱወሰንለትም ጠይቆአል። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የስራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ በፈፀመው ጥፊት ምክንያት ነው። የተፈፀመውም በሕጉ እና በሕብረት ስምምነታችን መሰረት ነው በማለት ተከራክሮአል። ክሱን ያስተናገደው ፍ/ቤትም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ፣ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው። ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደስራው ይመለስ በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተጠሪ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልት ወደስራው ይመለስ በማለት ወስኖአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ ጥፊት ስለመፈፀሙ በሥር ፍ/ቤቶች ታምኖበት እያለ የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በሚል የመወሰኑን አግባብነት ለመመር ነው።
በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ይዘት መገንዘብ እንደቻለነው አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው በሁለት ምክንያቶች ነው። እነዚህም ተጠሪ ቀደም ሲል በፈፀመው ጥፊት በገንዘብ /በደመወዙ/ ቅጣትና በማስጠንቀቂያ ታልፍ ነበር የተባለው የማጭበርበር ተግባር እና በምርት ማምረት ሂደት በፈፀመው ጥፊት የጎማ ምርት ከጥቅም ውጪ እንዱሆን አድርጎአል የተባለው ናቸው። እነዚህ ድርጊቶች በእርግጥም በተጠሪ የተፈፀሙ ለመሆናቸው የስር ፍ/ቤቶች አረጋግጠዋል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የስራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው ለማለት የበቃው ተጠሪ የፈፀመው ጥፊት ከስራ ለማሰናበት "የሚችል በቂ ኃይል" የለውም። አመልካች ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ ሲችል ተጠሪን ከስራ ያናበተው አላግባብ ነው የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም የራሱ የተገለፀ ምክንያት የሰጠ ሲሆን፣ ይህም ለሥራ ውለ መቋረጥ መሰረት የተደረገው ጥፊት በህብረት ስምምነቱ እንጂ በአዋጁ አንቀጽ 27 የተመለከተ አይደለም የሚል እንደሆነ ከውሣኔው ይዘት ተገንዝበናል።
ተጠሪ ቀደም ሲል ፈጽሞት ነበር የተባለው ጥፊት እንዲየነው በአንድ ወቅት ሞተዋል በማለት የሐዘን ፈቃድ የወሰደባቸውን አክስቱን ለሁለተኛ ጊዜ ሞተዋል በማለት የሐዘን ፈቃድ መጠየቁ ስለተረጋገጠበት ነው። ይህን መሰል ጥፊት የፈፀመ ሰራተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ የአስር /1ዐ/ ቀን ደመወዝ ከመጨረሻ ደረጃ ማስጠንቀቂያ ጋር እንደሚቀጣና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በማንኛውም ጥፊት ላይ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከስራ እንደሚሰናበት በህብረት ስምምነቱ ተደንግጎአል። በእርግጥ ይህ ጥፊት ከሥራ ያሰናብታል ተብል በአዋጁ አንቀጽ 27 አልተመለከተም። አንቀጽ 27 ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለሚቋረጥባቸው ምክንያቶች በተመለከተ የተደነገገ ሲሆን፣ በንዐስ አንቀጽ /1/ እንደተመለከተው በህብረት ስምምነት በልላ አኳኋን የተወሰነ የሥራ ውል የሚቋረጥበት ምክንያት ካለ በአዋጁ ባይመለከትም ተፈፃሚ ይሆናል። በዚህ ረገድ ሕጉ ግልጽ ነው። በህብረት ስምምነቱ ከሥራ ውል መቋረጥ በቂ ምክንያት ነው ተብል የሚቀመጠው ድንጋጌ ምን ዓይነት ላሆን እንደሚገባ ሕጉ አላመለከተም። ከሁለ በላይ ደግሞ በተያዘው ጉዲይ እንደምናየው በሕብረት ስምምነቱ ላይ የተቀመጠው ሁኔታ ብቻውን አይደለም ለስራ ውል መቋረጥ በቂ ምክንያት የሚሆነው በህብረት ስምምነቱ የተመለከተውን ጥፊት መፈፀም ተከትል የሚፈፀም ጉዲት ሲኖር ነው የስራ ውለ የሚቋረጠው፤ ይህ ደግሞ በትክክል ተሟልቶአል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ከአዋጁ አንቀጽ 134/2/ ጋር አነፃጽሮ መመለከቱ ተገቢ የማይሆነውም በዚህ ምክንያት ነው። ሲጠቃለል አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ሕጉንና ሕብረት ስምምነቱን መሰረት በማድረግ በመሆኑ በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበባቸው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 23162 ሰኔ 1ዐ ቀን 99 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 57742 መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ተመስርቶ የነበረው የስራ ውል የተቋረጠው በሕጉ መሰረት ነው በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.