No summary available.
ታህሳስ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ደሣለኝና ቤተሰቡ ኃላ.የተ.የግል ማህበር - ጠበቃ ወ/ሥላሴ ብርቱ -ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ፈቃደ በላይ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ መስከረም 23 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት የክስ ማመልከቻ በአመልካች መ/ቤት ከመጋቢት 16 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ በሹፋርነት ተቀጥረው እየሰሩ ባለበት ሁኔታ አመልካች ያለጥፊትና ማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን በመግለጽና ሉከፈለ የሚገባቸውን ክፍያዎችን በመዘርዘር በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ሲሆን የአሁኑ አመልካች በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ለስራ ሉገለገለበት የተሰጣቸውን ብሪጅ ስቶን ጏማ ተረኛ በነበሩበት ጊዜ መውሰዲቸውን ወይም እንዱወሰድ በማድረጋቸው በመሆኑና ይህም አድራጏት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/,/ቀ/ እና 14/2/ለ/ መሰረት የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት በመሆኑ የተጠሪ ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ከመከራከሩም በተጨማሪ ክፍያዎችን በተመለከተም ተገቢነት የላቸውም የሚላቸውን ምክንያቶችን በማንሳት ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም በአመልካች በኩል የቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ሐምል 04 ቀን 1998 ዓ.ም ብሪጅ ስቶን ጏማ የጠፊ መሆኑን እና ጠፊ በተባለ ጊዜ ተጠሪ ተረኛ የነበሩ መሆኑን ከሚያስረደ በቀር ተጠሪ ለእራሱ ወይም ለላላ ሰው ብልጽግና በመሻት የአመልካችን ንብረት የሆነውን ጏማ ላይ አላግባብ የተጠቀሙ መሆኑን፣ አመልካች በግልጽ ሳይፈቅድ ከስራ ቦታ ጏማውን የመውሰድ ህገ ወጥ ተግባር ተጠሪ የፈፀሙ መሆኑን አያስረደም፣ አመልካች የማስረዲት ሸክሙን አልተወጣም የሚለትን ምክንያቶችን በመዘርዘር የስራ ውል ማቋረጥ እርምጃ አግባብ አይደለም ሲል ከወሰነ በኋላ ክፍያዎችን በተመለከተም ተገቢ ነው ያለውን ወስኗል። በዚህ የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃ አግባባ አይደለም ተብል በተሰጠው የውሣኔ ክፍል የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ይኸው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/ መሰረት የአሰሪው ንብረት ወይም ገንዘብ መጥፊት ብቻውን ለራሱ ወይም ለላላ ሰው ብልጽግና በመሻት የተፈፀመ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቆረጥ በቂ አይደለም የሚል ምክንያት በመያዝ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሐምል 07 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ የተረከቡት የስኮርት ጏማ እንደጠፊ ራሳቸው በፃፎቸው የተለያዩ ፁሐፍች ተረጋግጦ እያለ እና ለጠፊው ጏማ ኃላፉ የማይሆኑበትን ምክንያት ማስረዲት ሲገባቸው ሳያስረደ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/,/ቀ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ እንዱቀርቡ ተደርጏ መስከረም 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ጠፊ የተባለውን ጏማ በተመለከተ አመልካች ለዓ/ህግ አመልክቶ ክስ ካቀረበ በኋላ ተጠሪ ለስራ ክርክር ችልት ክስ መስርተው በክርክር ላይ ያለ መሆኑን አመልካች እያወቀ በዓ/ህግ በኩል የቀረበውን ክስ ማንሳቱ የአመልካችን ንብረት ተጠሪ ያልወሰደና ለግል ጥቅም አለማዋላቸውን በራሱ የሚያስረዲ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው የወንጀል ክሱ የተነሳበት ምክንያት ለተጠሪ ትብብር ለማድረግ የተደረገ መሆኑንና ይህም አመልካች ጠፊብኝ የሚለውን ተለዋጭ ጏማ አልጠፊም የሚል ማረጋገጫ ያልሰጣቸው መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀው ህዲር 05 ቀን 2001 ዓ.ም መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የፁሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የአመልካች የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃ አግባብ አይደለም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ የተረከቡትን የአመልካች መ/ቤት ንብረት የሆነው ብሪጅ ስቶን ጏማ በእጃቸው አለመገኘቱ እና በኋላም ለአመልካች መ/ቤት ያልመለሱ መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠሪም እስከዚህ ችልት ባደረጉት ክርክር የአከራካሪው ጏማ መጥፊትን ክደው የማይከራከሩ መሆኑን ተገንዝበናል። ተጠሪ የሚከራከሩበት የአመልካችን ጏማ ያልወሰደና ለግል ጥቅማቸው ያላዋለ መሆኑን በመጥቀስ ነው። የበታች ፍ/ቤቶችም ተጠሪ የተረከቡት የአመልካች ጏማ መጥፊቱን አመልካች ማስረዲቱን እያመኑ የአመልካች እርምጃ ህገ ወጥ ነው ወደ ሚለው ድምዲሜ የደረሱት አመልካች ጏማው መጥፊቱን ከማስረዲት በተጨማሪ ተጠሪ ድርጊቱን የፈፀሙት ለራሳቸው ወይም ለላላ ሰው ብልጽግና በመሻት መሆኑን የማስረዲት ሸክም አለበት፣ ይህንኑ ግዳታም አልተወጣም በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27/1/መ/ እና /ቀ/ ስር የተመለከቱት ምክንያቶች የስራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችለ ሕጋዊ ምክንያቶች ናቸው። አመልካች የሚከራከረውም እነዚህን ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው። የሰጠው ምክንያትም ተጠሪ ለስራ ሉገለገለበት የተሰጣቸውን የብሪጅ ስቶን ጏማ አጥፍተዋል በሚል ነው። ይኸው ጏማ የጠፊው ተጠሪ ተረኛ በነበሩበት ወቅት ስለመሆኑ እና መጥፊቱም በስር ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ተጠሪ በሹፋርነት ሙያ የተቀጠሩ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ከመሆናቸውም በላይ ጉማው ተረኛ ከነበረው ላላ ሹፋር አልተረከብኩም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሣያል። በመሆኑም ከተረኛ ሹፋር መኪናውን ተጠሪ ከተረከቡ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13/3/ ስር እንደተመለከተው ለስራው የሚሰጡትን መሣሪያዎች በጥንቃቄ የመጠበቅ አላፉነት አለባቸው። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ግን ተጠሪ ይህንኑ ግዳታ አለመወጣታቸውን ነው።
ይልቁንም ተጠሪ መኪናውን ተረክበው በራሣቸው ቁጥጥር ስር ባደረጉበት ወቅት ጏማው አለመጥፊቱና ይኸው ጏማው በምን ሁኔታና ምክንያት ሉጠፊ እንደቻለ ተጠሪ ማስረዲት ያልቻለ መሆኑ ተረጋግጧል። በዚህም ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 14/2/ለ/ ስር እንደተመለከተው የጏማው በህገ ወጥ መንገድ የመጥፊቱ ሁኔታ ከተጠሪው ጋር በቀጥታ ግንኙነት የለውም ለማለት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት የለም ከዚህም በተጨማሪ ተጠሪ የተረከቡት ብሪጅ ስቶን ጏማ በእጃቸው አለመገኘቱ ከተረጋገጠ ድርጊቱ የተፈፀመው የራስን ወይም የላላ ሰው ብልጽግና በመሻት ጭምር ስለመሆኑ ሉረጋገጥ የሚገባው ነው ተብል በህጉ በመስፈርትነት ያልተቀመጠ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ምክንያቱም ይኸው ነጥብ ንብረቱ መጥፊቱ ከተረጋገጠ ግምት የሚወስድበት ስለመሆኑ ከአሰሪና ሰራተኛ እና ማስረጃ ህግ አጠቃላይ መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነውና። በመሆኑም ከፍ ሲል እንደተገለፀው የጏማው መጥፊት ከተጠሪ ጋር ግንኙነት የለውም የሚባልበት የህግ ምክንያት ካለመኖሩም በላይ ድርጊቱ የተፈፀመው የራስን ወይም የላላ ሰው ብልጽግና በመሻት ስለመሆኑ አመልካች እንዱያስረዲ የሚገደድበት የማስረጃ ሸክም የላለበት ሆኖ ተገኝቷል።
ተጠሪ የአመልካችን ንብረት ያልወሰድኩና ለግል ጥቅም አለማዋላን የሚያረጋግጠው ጉዲይ አመልካች በዓ/ህግ በኩል መስርቶት የነበረውን የወንጀል ክስ ማንሣቱ ነው በሚል ያቀረቡትን ክርክር ስንመለከተውም የወንጀል ክሱን መተው በፍትሐብሕር ረገድ ያለውን ክርክር ሉያቋርጥ የሚችልበት የህግ ምክንያት እና ሥነ ሥርዓት የላለ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች በአመልካች በኩል የቀረቡትን መከራከሪያ ነጥቦች ውድቅ ያደረጉት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/መ/ እና /ቀ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መንፈስ ባግባቡ ባለማገናዘብ በመሆኑ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.