No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ አሉ መሐመድ አመልካች፡- አድማስ ኮላጅ - ጠበቃ አበበ ኃይላ ቀረበ ተጠሪ፡- ሰለሞን ሙለዓለም - በላለበት የሚታይ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዮ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ መጋቢት 08 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ከታህሳስ 01 ቀን 1995 ዓ.ም እስከ የካቲት 29 ቀን 1998 ዓ.ም ድረስ በወር ብር 1800.00 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር/ እየተከፈላቸው በመምህርነት ስራ ከአመልካች ድርጅት ጋር መስራታቸውን ሆኖም ያላንዲች ጥፊትና ማስጠንቀቂያ አሰሪው ድርጅት ከሥራ ያሰናበታቸው መሆኑን ዘርዝረው የሥራ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ተብል ወደ ስራ እንዱመለሱ ወይም የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ የስራ ማስረጃ እንዱሰጣቸው ይወስንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም የተጠሪን የስራ ስንብት አግባብነት በመጥቀስ ተከራክሯል። የተጠሪ የስራ ስንብት አግባብ ነው በማለት በምክንያትነት ያቀረባቸው ነጥቦችም ተጠሪን በመደጋገም የስራ ሰዓት አለማክበር የተማሪዎችን ውጤት ከአንድ ወር በላይ በእጁ ማቆየቱና ውጤቱን ሣይመልስ መቅረቱ እንዱሁም ተማሪዎች ያላገኙትን ውጤት መስጠታቸው በኮሚቴ ተጣርቶ መረጋገጡን የሚመለከቱ ናቸው። የስር ፍ/ቤትም የአመልካችን ምስክሮች ከሰማ በኋላ የተጠሪን ከስራ መሰናበት አግባብነት በጭብጥነት ይዞ ጉዲዮን ከመረመረ በኋላ በስንብት ደብዲቤው ላይ የተገለፀው ጥፊት ተጠሪን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት አይደለም በማለት የስራ ስንብቱ ያላግባብ ነው ካለ በኋላ የተጠሪ ወደ ስራ ልመለስ ጥያቄ ተቀባይነት ስለላለው በአማራጭ የጠየቋቸው የስንብትና የካሣ ክፍያዎች እንዱከፈለ የምስክር ወረቀትም እንዱሰጣቸው ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይሄው ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ታህሳስ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ የተማሪዎችን የፈተና ወረቀት ሣይመልስ መቅረቱ ለተማሪዎች ድጋሚ ፈተና መሰጠቱን ይህን ለማድረግም ከፍተኛ ገንዘብና ጊዜ ማወጣታቸውን ይህም በኮላጁ ንብረት ላይ ጉዲት መድረሱን የሚያረጋጋጥና በአዋጅ ቀጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ስር የሚወድቅ ሆኖ እያለ የታለፈው ያላግባብ በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባል ተብል ተጠሪ በጋዜጣ ጥሪ ቢደረግላቸውም ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ታዝዟል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የሥራ ውለ የተቋረጠው በህገ-ወጥ መንገድ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ ይሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ ተጠሪ ከስራ እንዱሰናበቱ የተደረገው በአመልካች ድርጅት በሚሰሩት የመምህርነት ሙያ የተማሪዎችን ውጤት በወቅቱ ሣያስገቡ በመቅረታቸው ስለመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ፈተናውን በድጋሚ እንዱወስደ መደረጉንና እንዱህ ሲደረግም ለተማሪዎቹ ለአንድ ሣምንት ‹‹ቲቶሪያል›› ተሰጥቶ ስለመሆኑ የአመልካች የሰው ምስክሮች መመስከራቸውን ከስር ፍ/ቤት ዋና መዝገብ ተመልክተናል። ተጠሪ የተማሪዎችን ውጤት እንዱያስገቡም በስልክና በተለያዩ መንገድች ተጠይቀው ሉመልሱ ያልቻለ ስለመሆኑ ተረጋግጧል።
እንዱህ ለስራ ስንብቱ በምክንያትነት የተጠቀሰው የተጠሪ የተማሪዎችን ውጤት በወቅቱ አለመመለስና ይህንኑ አላፉነታቸውን ባግባቡ አለመወጣት ስለመሆኑ የአመልካችን ማስረጃዎች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። የስር ፍ/ቤትም ይኸው ፍሬ ጉዲይ በማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ተገንዝቦ ምክንያቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ስር የሚወድቅ አይደለም ሲል ነው የሥራ ሥንብቱን ሕገ ወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው። በእርግጥ የስር ፍ/ቤት በስራ ስንብቱ ላይ የተመለከተውን የተጠሪን ጥፊት ይዘቱን በተፃፈው መልክ ከተመለከተው ጥፊቱ በአዋጁ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት ከሚያስችለ ምክንያቶች ውስጥ ሉካተት የማይችል መሆኑን መገንዘብ ይችል ይሆናል። ይሁን እንጂ በተጠቃሹ አዋጅ ስር የተመለከቱት ምክንያቶች በክርክሩ ወቅት የሚረጋገጡ ፍሬ ጉዲዩችንና የአዋጁን አጠቃላይ ዓላማ በመመርመር ሉተረጏሙ የሚችለ ስለመሆናቸው መገንዘብ አያዲግትም። አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ በንብረት ላይ ጉዲት አድርሷል በማለት ነው። ጉዲት ደረሰ የተባለውም ተማሪዎች እንደገና ሉፈተኑ ሲደረግ የጊዜ፣ የጉልበት፣ የወረቀት ወጪ ከመደረጉም በላይ የኮላጁ መልካም ስም ጠፍቷል በሚልም ጭምር ነው አመልካች ለዋቢነት የሚጠቅሰው ድንጋጌም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ሸ) ስር የተመለከተውን ነው። በዚህ ድንጋጌ በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረስ ሰራተኛን ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ ለማሰናበት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ነው። ንብረት ለሚለው ቃል በአዋጁ ሥር የተመለከተ ትርጓሜ የለም። ይሁን እንጂ ከአዋጁ ዓላማና ከአሰሪው ድርጅት ባህርይ እንዱሁም ከንብረት ህግ ጽንሰ ሀሣቦች ጋር በማዛመድ ለቃለ ትርጉም መሰጠት ፍትሐዊነት ይኖረዋል ምክንያቱም ንብረት ለሚለው ጽንሰ ሀሳብ ሁለንም የሚያስማማ ትርጉም መስጠት የሚችል አይደለምና። በመሆኑም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን አጠቃላይ ዓላማም ሆነ የንብረት ህግ ጽንሰ ሀሣቦች ባህርያት ግንዛቤ ውስጥ ስናስገባ ንብረት ማለት ዋጋና ኢኮኖማያዊ ጠቀሜታ ያለው እንዱሁም በአብዛኛው ሀብትነት ሉያዝ የሚችል ነገር መሆኑን ለመገንዘብ አስቸጋሪ አይሆንም ዋጋና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ሆኖ በባለሀብትነት ሉያዝ የሚችል ነገር ላይ ሆን ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ያደረሰ ሰራተኛ ከሆነ በአሰሪው ንብረት ላይ በህጉ አነጋገር ጉዲት አድርሷል ለማለት የማይቻልበት ምክንያት የለም።
እጃችን ወዲለው ጉዲይ ስንመለስም የተጠሪ አድራጏት ለአመልካች ዋጋና ኢኮኖማያዊ ጠቀሜታ ባለው ነገር ጉዲት አላደረሰም የሚል አይደለም በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በተጠሪ የስንብት ደብዲቤ ላይ የተገፀውን ምክንያት እንዲለ በመውሰድ የደረሰበት ድምዲሜ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ ባለመምረጥና አጠቃላይ ይዘቱንና መንፈሱን ባለማገናዘብ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 06 ቀን 1999 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ታህሳስ 09 ቀን 2000 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች ወጪና ኪሣራ የራሱን ይቻል ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.