No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 3621ዐ ኀዲር 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቃቂ መለዋወጫ እቃዎችና መሣሪያዎች አ/ማ - አልቀረበም።
ተጠሪ፡- አቶ ኃይለ ሳልቫልቶር - ቀርቧል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ተወስኗል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የሥር ተከሣሽ ተጠሪ የሥር ከሣሽ ነበሩ። ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት የሥራ ድልድል አብረውኝ እንደሚሰሩት ሰራተኞች ከደረጃ 6 ወደ 8 ላይ እንድመደብ ይወሰንልኝ ሲል ጠይቋል።
አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ ደረጃ 8 ላይ የተመደቡት 19 ዓመት እና በላይ ልምድ ያላቸውና በራሳቸው መስራት የሚችለትን ነው። ተጠሪ ልምድም የላቸውም፣ መዋቅሩ መሰረት ያደረገው የሥራ ፍላጎትና ፍቅር፣ ውጤታማነት ታይቶ ነው፤ ስለዚህ ተጠሪ ለቦታው አይገቡም ብል ተከራክሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የቀረበለትን የግራ ቀኙን ክርክር ካለው ሕግ ጋር በመመርመር አመልካች የሥራ ምድቡን ለመስጠት መሰረት ያደረገው ልምድና የትምህርት ደረጃ ብቻ አይደለም የታየው፣ ነገር ግን ታማኝነት የስራ አፈፃፀም እና ውጤታማነትም ታይቶ ስለሆነ በአግባቡ ነው ብልአል፤ ነገር ግን ቦታው ለምን እንደማይገባቸው ከመናገር ውጪ ቦታው እንደማይገባቸው ያቀረበው ማስረጃ የለም።
ተጠሪ አብረውኝ ለነበሩት ደረጃ 8 ሰጥቷል የሚለውን ቅሬታ አመልካች አላስተባበለም በማለት ተጠሪ በደረጃ 8 ላይ እንዱመደብ እና በደረጃ 8 የሚከፈለው ክፍያ እንዱከፈለው ወስኗል።
አመልካችም በዚህ ፍ/ቤት በተሰጠው ውሣኔ ባለመስማማት ቅሬታውን ቢያቀርብም ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ውሣኔው ጉድለት የላለበት መሆኑን ገልፆ ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም በዚህ ላይ ነው።
አመልካች መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አቤቱታውን አቅርቧል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል። ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነውም ተጠሪ በአመልካች መ/ቤት መዋቅር መሰረት ወደ ደረጃ 8 ከፍ ብል እንዱመደብ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረት ይህንን ነጥብ ግራ ቀኙ ወገኖች ካሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
በዚህ ጉዲይ ለክርክሩ ዋናው ነጥብ የሆነው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በደረጃ 6 ላይ ሲሰራ ቆይቶ ወደ ደረጃ 8 መመደብ ሲገባው የተከለከለ መሆኑን ገልፆ በማመልከቱ ነው። የሥር ፍ/ቤትም በማከራከር ተጠሪ ወደ ደረጃ 8 እንዱመደብ እና ክፍያውም እንድፈጽምለት ወስኗል።
የአመልካች ድርጅት አዱስ መዋቅር መዘርጋቱን ሳይክድ በዚሁ አዱስ አሰራር ከደረጃ 6 ወደ 8 ሉያድጉ የሚችለትን /የሚገባቸውን/ ሰራተኞች ራሱ ባወጣው መስፈርት መሰረት እንደለየ እና ተጠሪ ለዚህ ቦታ እንደማይመጥኑ ከምክንያቱ ጋር ገልጿል። ተጠሪም በዚሁ መሰረት በደረጃ 7 ላይ እንዲለም መዝገቡ ያስረዲል። ይህ የሚያመለክተው ተጠሪ ሉመጥን በሚችልበት የተመደበ መሆኑን መገመት ይቻላል። አሰሪ የራሱን ሥራ ለማቀላጠፍ እና ምርታማ ለመሆን ሰራተኞችን እንደየችልታቸውና እውቀታቸው ይጠቅሙኛል ባለው ቦታ በሕጋዊ መንገድ መደልደልም ሆነ መመደብ የሚከለክለው ሕግ የለም። ከሱ /ከድርጅቱ/ በላይ ስለሰራተኞቹ የሚያውቅ ሉኖር አይችልምና።
ስለዚህ የአመልካች ድርጅት ተጠሪን ወደ ደረጃ 8 /ስምንት/ የማታሳድግበትን ምክንያት አላስረዲህም እና ወደ ደረጃ 8 አሳድገህ የመደቡን ክፍያም ፈጽም ተብል መወሰኑ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 28621 በቀን 11/4/2ዐዐዐ ዓ.ም. የፋ/ከ/ፍ/በመ/ቁ. 62/ዐ9 በቀን 16/5/2ዐዐዐ የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ፍ/ቤቶች በድርጅቱ /በአመልካች/ ሥራ ገብተው ሰራተኛን አሳድግ በማለት መወሰን አይችለም ብለናል።
ይፃፍ።
No topics extracted.