No summary available.
ኀዲር 16 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢት/ኤላክትሪክ ኃ/ኯርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ዝግአለ አሰፊ ተጠሪ፡- ወ/ት ትርሲት ደገፈ - ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው የስራ ውል አመሰራረትን የሚመለከት ጉዲይ ነው።
ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ድርጅት የምስ/ሪጅን ጽ/ቤት ለክለርክ ታይፒስት ፀሐፉ ደመወዝ ብር 453.00(አራት መቶ ሃምሳ ሶስት) በድርጅቱ ስኬል መሰረት ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ አውጥቶ ተጠሪ ተወዲድረው ማለፊቸው በጥቅምት 27 ቀን 1999 ዓ.ም ተገልፆላቸዋል። ከሕዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምረው የድርጅቱ ሰራተኛ መሆናቸው ከአሻራ ምርመራ በተፃፈ ደብዲቤና በጡረታ ቅጽ ላይ ተገልጿል። ምድብ ቦታቸው ደደር መሆኑ ተገልፆላቸዋል የመጀመሪያ ስራቸውን ለቀው ለመሄድ ሲዘጋጁ ያለበቂ ምክንያት የስራ ውላቸው መሰረዙ በታሕሣስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ተገልፆላቸዋል። ስለዚህ የስራ ውለ የተቋረጠው ያለአግባብ በመሆኑ ወደ ስራቸው እንዱመለሱ፣ ከሕዲር 1 ቀን 1999 - ታህስስ 25 ቀን 1999 ያለው ደመወዛቸው እንዱከፈላቸው፣ የስራ ውላቸው ያለአግባብ ስለተቋረጠ የ6 ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል።
አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ፤በአመልካችና በተጠሪ መሐከል የፀና የስራ ውል የለም፣በድርጅቱ አሰራር መሰረት የተፈፀመ የቅጥር ውል የለም፣ አሻራ ምርመራ እንዱያደርጉ መላክ የስራ ውል መፈፀም ማለት አይደለም፣በቅጥር ውል ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛን እንኳን ያለምንም ማስጠንቀቂያ ማሰናበት ይቻላል። ከስራ ተሰናበትኩ ይበለ እንጂ የስንብት ደብዲቤ አላያያዙም፣የቅጥር ውል አለ ቢባል እንኳን ወደ ስራ ለመመለስ ያቀረቡት ጥያቄ በ3 ወር ጊዜ በይርጋ ይታገዲል፣የውል ድርድር አለ ቢባል እንኳን በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1693/1/ እና /2/ መሰረት ድርድሩ እንዲልተደረገ ይቆጠራል፣ከክሣቸው ጋር ያቀረቧቸው ማስረጃዎች የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መኖሩን አያስረደም፣ ስለሆነም ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም፣ላልተሰራ ስራ ደመወዝ ሉከፈል አይገባም፣ የመብት ጥያቄ ማንሣት የሚችለው 45 ቀናት ያገለገለ ሰራተኛ ነው፣የአሻራ ምርመራ ደብዲቤው የአሻራ ውጤት ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያለ መሆኑን ስለሆነ ውጤቱ ሣይደረስ ቅጥር ሉፈጸም አይችልም በማለት የቀረበበትን ክስ አስተባብል ተከራክሯል።
የሥር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኋላ በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የቅጥር ውል አለ፣ተጠሪ የ6 ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ምድብ ስራቸው ይመለሱ፣ እንዱሁም ከሕዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ታህሣስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ያለው ደመወዝ ይከፈላቸው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ በአመልካችና በተጠሪ መሐከል የስራ ውል የለም፣ላልተሰራ ስራ ደመወዝ ሉከፈል አይገባም፣የሚለ ናቸው። ይህ ችልትም የተጠሪ የስራ ውል የተቋረጠው ያለአግባብ ነው ተብል ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ መወሰኑ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረግ ተጠሪም ቀርበው ተከራክረዋል።
ከላይ የተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክርና የፍ/ቤቶቹ ውሣኔ ሲሆን ይህ ችልትም የሰበር አቤቱታውን አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከተገቢው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሯል።
በዚህም መዝገብ ውሣኔ ማግኘት የሚያሻቸው ነጥቦች 1. በአመልካችና በተጠሪ መሃከል የስራ ውል አለ? የለም?
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፣ተጠሪ በክሣቸው በአመልካችና በተጠሪ መሐከል የስራ ውል አለ በማለት ተከራክረዋል። ለዚህም መሰረት ያደረጉት የአመልካች ድርጅት ምስ/ሪጅን ጽ/ቤት ለክለርክ ታይፒስት ፀሐፉ ደመወዝ ብር 453.00 ማስታወቂያ ወጥቶ ተወዲድረው ማለፊቸውን፣ከዚህ በኋላ አመልካች መስሪያ ቤት ከኀዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ የመ/ቤቱ ሰራተኛ መሆናቸውን ገልፆ የአሻራ ምርመራ ደብዲቤ መፃፈንና በጡረታ ቅጽ ላይ ማረጋገጡን፣ምድብ ቦታቸውም ደደር መሆኑን ማሣወቁን ነው። አመልካች በበኩለ ከፍ ሲል በተጠሪ የተገለፁትን ፍሬ ነገሮች ክድ አልተከራከረም። ነገር ግን ፈተናውን ማለፊቸውም ሆነ ለአሻራ ምርመራ የተፃፈው ደብዲቤ የስራ ውል አይመሰርትም።
በመ/ቤቱ አሰራር መሰረት የተፈፀመ የስራ ውል ስለላለ ከተጠሪ ጋር ውል አለ ልባል አይችልም በማለት ተከራክሯል።
በመሆኑም የስራ ውል አመስራረትን በተመለከተ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የሚደነግገውን መመልከት ተገቢ ይሆናል። በዚህ አዋጅ በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነትን በሚመለከተው ክፍል ስር የሚገኘው ምእራፍ አንድ ዘርፍ አንድ የስራ ውል በምን መልኩ መመስረት እንደሚገባው ይናገራል። የአዋጁ አንቀጽ 4/1/ “ ማንኛውም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው፤በአሰሪው መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ስራ ለአሰሪው ለመስራት ቢስማማ በሁለቱ ማሐከል የስራ ውል ይመሰረታል።” በማለት ያስቀምጠዋል። በመሆኑም የስራ ውል ማለት አንድ ሰራተኛ በአሰሪው መሪነት የአሰሪውን ስራ፤ በውለ ላይ ለተመለከተው የስራ ጊዜ፤ለመስራት የሚያደርገው ስምምነት መሆኑ በዚህ አንቀጽ ትርጓሜ ተሰጥቶበታል። በልላ በኩል ደግሞ የስራ ውለ እንዳት መደረግ እንዲለበትና ሉይዛቸው ስለሚገባው ነገሮች በንኡስ ቁጥር 2 እና 3 ሥር ተመልክተዋል። በዚህም መሰረት የስራ ውል ተዋዋይ ወገኖች በውለ መሰረት የሚኖራቸው መብትና ግዳታ በማያጠራጥር አኳኋን በሚያውቁበት ሁኔታ በግልጽ መደረግ ያለበት ሲሆን ውለም የስራውን አይነትና ቦታ፣ ለስራው የሚከፈለውን ደመወዝ መጠን፣ የስላቱን ዘዳ፣ የአከፊፈለን ሁኔታና ጊዜ እና ውለ ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ መያዝ እንደሚኖርበት ተገልፆል። የስራ ውለ በዚህ መልክ መደረግ የሚኖርበት ቢሆንም ግን በሕግ በተለየ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር የተለየ ፍርም የላለው መሆኑ፣ በአንቀጽ አምስት ስር ተመልክቷል። ስለሆነም የስራ ውል፤ሕግ ካላስገደደ በቀር፤በማንኛውም አይነት ሉቋቋም እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።
ከነዚህ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎች አኳያ የተያዘውን ጉዲይ ስንመረምር አመልካች ለክለርክ ታይፒስት ጸሐፉ ቦታ በወር ብር 453.00 ደመወዝ ለመቅጠር ማስታወቂያ በማውጣቱ ተጠሪ በማስታወቂያው መሰረት ለመቀጠር ቀርበው ፈተናውን ተፈትነው አልፈዋል። ፈተናውን ማለፍ ብቻ ሣይሆን ከኀዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ የድርጅቱ ሰራተኛ መሆናቸው ተገልፆ የአሻራ ምርመራ እንዱደርግላቸው ደብዲቤ ተጽፍ እና የጡረታ ቅጽ ተሞልቶ ለሚመለከታቸው ክፍልች ተላልፎል። ከዚህም በተጨማሪ ምድብ የሥራ ቦታቸው ደደር መሆኑም ተገልፆላቸዋል። የስራ ውል የተለየ ፍርም የላለው በመሆኑ አመልካች የክለርክ ታይፒስት ፀሐፉ ለመቅጠር የውል ድርድር ማቅረቡ ተጠሪ ደግሞ ድርድሩን ተቀብለው ፈተና ተፈትነው ማለፊቸው በቀጣይነትም አመልካች ተጠሪ የድርጅቱ ሰራተኛ ሆነው መቀጠራቸን በመግለጽ ለተለያዩ መ/ቤቶች በላከው ደብዲቤና የጡረታ ቅጽ ማረጋገጡ በሁለቱ በሐከል የውል አቀራረብና አቀባበል መኖሩን ያመለክታል። የተጠሪዋ የምድብ ስራቸው ደደር መሆኑ፣የስራው አይነት የክለርክ ታይፒስት ጸሐፉ መሆኑ የተጠሪዋ ደመወዝ በወር ብር 453.00 እና በድርጅቱ ስኬል መቀጠራቸው ሁለ ግራ ቀኙ አውቀውት የተስማሙበት በመሆኑ በአዋጁ የስራ ውል አመሰራረት የሚጠይቀውን የሚያሟላ ነው። ስለሆነም አመልካች ከተጠሪ ጋር የስራ ውል የለንም በማለት ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም። አመልካቹ ተጠሪ በመ/ቤቱ የአሰራር ደንብ መሰረት አልተቀጠርኩም በማለት የሚከራከር ሲሆን ይህ ደንብ መኖሩንና በዛ ደንብ መሰረት አለመቀጠራቸውን ለማስረዲት አለመቻለን ከመዝገቡ ተረድተናል። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መሐከል የቅጥር ውል አለ በማለት የስር ፍርድ ቤት የደረሱበት መደምደሚያ የህግ ስህተት አለው ለማለት አልተቻለም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የሥራ ውል አለ ከተባለ ውለ የተቋረጠ ነው? አይደለም? አይደለም የሚባል ከሆነ ውጤቱ ምንድነው የሚለው ነው።
አመልካች በስር ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ከተጠሪ ጋር የስራ ውል አልመሰረትንም ከማለት በቀር የስራ ውለ የተቋረጠበትን ምክንያት አልገለፀም። በእርግጥ በሰበር ችልት በቀረበው አቤቱታ ላይ ለውስጥ ሰራተኞች የእድገት ማስታወቂያ ሣይወጣ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ መውጣቱ ተገቢ ባለመሆኑ ውለ መሰረዙን ገልጿል። ይህ ክርክሩ በስር ፍ/ቤት ያልተነሣ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ምክንያቱም የስራ ውልን ለማቋረጥ በቂ አልነበረም። የስራ ውል ያለአግባብ ከተቋረጠም ሰራተኛው ወደ ስራው ሉመለስ የሚገባው መሆኑና ወደ ስራ መመለስ ካልፈለገ ግን ካሣ ተከፍልት ሉሰናበት እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 43/1/ ሥር ተመልክቷል። በእርግጥ የስራ ግንኙነቱ ላይ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ሰራተኛውን ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት መወሰን እንደሚቻል የዚሁ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር 3 ያመለክታል። በተያዘው ጉዲዩ ተጠሪ ወደ ስራ መመለስ የፈለጉ በመሆኑና ወደ ስራ መመለሣቸው በስራ ግንኙነቱ ላይ የሚፈጥረው ችግር ስለመኖር በአመልካች በኩል የተነሣ ክርክር ስለላለ ተጠሪ ወደ ስራቸው እንዱመለሱ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ማለት አልተቻለም።
በልላ በኩል ደግሞ ያላግባብ የስራ ውለ የተቋረጠበት ሰራተኛ ወደ ስራ እንዱመለስ ሲወሰን በተጨማሪ ከስድስት ወር የማይበልጥ ውዝፍ ደመወዝ እንደሚወሰንለት ከአዋጁ አንቀጽ 43/5/ መረዲት ይቻላል። በመሆኑም በዚሁ መሰረት ተጠሪ ወደ ስራ ሲመለሱ የ6 ወር ደመወዝ እንዱከፈላቸው መወሰኑ በአግባቡ ነው።
በልላ በኩል ከክርክሩ ሂደት ተጠሪ ገና ስራ ሣይጀምሩ ውለ መቋረጡን መረዲት ችለናል። ነገር ግን በአ/ቁ.
377/96 አንቀጽ 54/1/ መሰረት በሕግ በልላ አኳኋን ካልተወሰነ ደመወዝ የሚከፈለው ለተሰራ ስራ ብቻ መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም አመልካች ስራ ሣይሰሩ ከሕዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ያለው የአንድ ወር ከ25 ቀናት ደመወዝ እንዱከፈላቸው መወሰኑ ተገቢነት የላለው መሆኑን ተገንዝበናል። ስለዚህ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 19067 በሰኔ 12 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 03174 በጥር 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ከኀዲር 1 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም ያለው የአንድ ወር ከ25 ቀናት ደመወዝ ሉከፈላቸው አይገባም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ
ይህ ችልት በመጋቢት 29 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ።
No topics extracted.