No summary available.
ኀዲር 04 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዱስ መለዋወጫ እቃዎች አስመጪና አከፊፊይ አ.ማ - ጠ/ብስራት መኮንን ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ካሣሁን ከበደ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በተከሣሽ ድርጅት ከታህሳስ 1 ቀን 1979 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 15 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ ማገልገላቸውን፣በመጨረሻ የነበረው የስራ መደብ ደረጃም ግምጃ ቤት ትራንዚት አምስት መሆኑን ከሕብረት ስምምነቱ ውጪ ዝውውር መፈፀሙንና የስራ ውለም ያላግባብ መቋረጡን በመዘርዘር ዝውውሩ እንዱሻር ወደ ስራ እንዱመለሱም ይወሰንላቸው ዘንድ በአሁኑ አመልካች ላይ መጋቢት 17 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ ክስ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ስለመሰረቱ ነው። የአሁኑ አመልካችም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ በሰጠው የመከላከያ መልስ ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ያለበቂ ምክንያት ከስራ ስለቀሩ በአዋጁና በህብረት ስምምነቱ መሰረት መሆኑን፣ ተጠሪ በደረሰባቸው አደጋ በጊዜአዊነት ደመወዝና የውል አበል እየተከፈላቸው በሕብረት ስምምነቱ መሰረት ተመድበው ሣለ በእምቢተኛነት ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ከስራ መደባቸው ላይ ባለመገኘታቸው በገዛ ፈቃዲቸው ስራውን የለቀቁና የሄደ መሆናቸውን በመዘርዘር ስንብቱ ባግባቡ ስለሆነ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ከሣሽ ዝውውሩ አላግባብ ነው የሚል ተቃወሞ ሲኖራቸው ክስ መመስረት ያለባቸው ወደ የተዛወሩበት ቦታ ሂደው ስራቸውን እየሰሩ መሆን አለበት እንጂ ስራቸውን አቋርጠው መሆን አልነበረበትም በሚል ምክንያት ከሣሽ ከስራ የተሰናበቱት ባግባቡ ነው በማለት ወስኖአል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ሰራተኛው የተፈፀመበትን ዝውውር ሕገ ወጥ ነው የሚል ቅሬታ ካለው የግድ ወደ ተዛወረበት የስራ ቦታ በመሄድ ጥያቄውን ማቅረብ የለበትም። ዝውውሩም በህብረት ስምምነቱ መሰረት የተፈፀመ አይደለም። የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮ ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ሲል ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ውሣኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነ/ፈጅ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ያለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የህብረት ስምምነቱንና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን ድንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ የስር ፍ/ቤትን ውሣኔን መሻሩንና ዝውውሩ ትክክል አይደለም የሚባል ቢሆን እንኳ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ሣይኖረው ተመልክቶ መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ውሣኔው ሉሻር ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል ተጠሪ ቀርበው ሐምል 17 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን የሰጡ ሲሆን የአመልካች ነ/ፍጅም በበኩላቸው መስከረም 27 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ መሻሩ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው ተጠሪ ወደተዛወሩበት ቦታ ሳይሕደ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት መቅረታቸውን መሰረት በማድረግ መሆኑንና ተጠሪ በበኩላቸው የሚከራከሩት ወደተዛወሩበት ቦታ ያልሄደት ዝውውሩ በስራ ላይ ያለውን የህብረት ስምምነት እና አዋጁን ያላገናዘበ በመሆኑ የዝውውር ደብዲቤው ከደረሣቸው ጊዜ ጀምሮ ከስራ ቦታቸው ሣይቀሩ ቅሬታ እያሰሙ ባለበት ሁኔታ በስራህ ላይ አልተገኘህም በሚል ሕጋዊ ሽፊን የስራ ውል ማቋረጥ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው በሚል መሆኑን ነው። እንግዱህ አመልካች ተጠሪን ከአዱስ አበባ ወደ ጏንደር አዛውሮ ተጠሪ የዝውውሩ ደብዲቤ ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ተዛወሩበት ቦታ በመሄድ ስራ ሣይጀምሩ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ያለፈባቸው፣ ለዚህም በቂ ምክንያት ብለው የሚከራከሩት የዝውውሩን ሕገ ወጥነት በመቃወም ቅሬታ በማሰማት ምላሹን እየተጠባበቁ የነበሩበትን ሁኔታ ነው። በመሆኑም ተጠሪ ወደ ተዛወሩበት ቦታ አለመሄዲቸውንና ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ላይ አለመገኘታቸውን በማመን የተከራከሩ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ነው።
በመሰረቱ በቂ ምክንያት ሣይኖረው በተከታታይ ለአምስት የስራ ቀናት በስራ ገበታው ያልተገኘ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሣያስፈልግ ከስራ እንዱያባርረው ለአሰሪው ሕጉ ፈቃድ የሰጠው መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ለ/ ድንጋጌ ያስረዲል። ሰራተኛው የአሰሪውን አድራጏት ሉቃወመው የሚችለው ለመቅረቱ በቂ ምክንያት መኖሩን በማስረዲት ነው። ከስራ ለመቅረት በቂ ምክንያት ላሰጥ የሚችለት ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ግን ሕጉ አመልካች ወይም ዝርዝር ሁኔታዎች አላስቀመጠም። ሆኖም በቂ ምክንያት የሚለው ሐረግ መመዘኛቸው ሰራተኛው ከስራ ቦታው ሉገኝ በማይችልበት ደረጃ ላይ አድረሰውት ነበር ተብል ሉታመንበት የሚገባ ስለመሆኑ ከአዋጁ አጠቃላይ አላማና ከተጠቃሹ ድንጋጌ መንፈስ ለመገንዘብ አያዲግትም። በመሆኑም ከስራ የቀረ ሰራተኛ በቂ ምክንያት ኑሮት ቀርቷል ለመባል የሚቀርበው ማስረጃ ሰራተኛውን በስራ ቦታ ለመገኘት የሚያስችል መሰናክል የነበረ መሆኑን ሉያረጋግጥ ይገባል።
ይህ ካልሆነ ግን ሰራተኛው በማይረባ ምክንያት ሁለ ከስራ ገበታው ባለመገኘት በአሰሪው ምርትና ምርታማነት ላይ የራሱን አለታዊ ተጽእኖ ማሣደሩ አይቀሬ ነው።
እጃችን ወደ አለው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ ከስራ ገበታቸው ያልተገኙበት ምክንያት የአመልካችን ዝውውር በመቃወም ቅሬታ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ ስለመሆኑ ከላይ ተገልጿል። አንድ ሰራተኛ ከአንድ ቦታ ወደ ላላ ቦታ መዛወር ደግሞ ሰራተኛው ወደ ተዛወረበት ቦታ በመሄድ በስራው ላይ ለመገኘት የሚያስችል መሰናክል ነው ተብል በበቂ ምክንያት መመዘኛ ስር የሚወድቅ አይደለም። ሰራተኛው በዝውውሩ ቅሬታ ካለውም ወደ ተዛወረበት ቦታ በመሄድና ስራውን በተገቢው መንገድ እያከናወነ ስልጣን ላለው አካል አቅርቦ ተገቢውን መፍትሕ ከመጠየቅ በስተቀር ከስራ ቦታው ሣይገኝ ቅሬታውን በማቅረቡ ብቻ ከስራ ገበታው በበቂ ምክንያት ቀርቷል ልባል አይገባም። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜ ተቀባይነት ከላለው የመነሻ ሐሣብ የመነጨ ከመሆኑም በላይ በስረ-ነገር ስልጣኑም የሚወድቅ አይደለም።
ሲጠቃለልም ተጠሪ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ገበታቸው አለመገኘታቸው እና ያቀረቡት ምክንያትም በቂ ነው ተብል የሚወሰድ አለመሆኑ በአግባቡ ተረጋግጦ እያለ የከፍተኛው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ መሻሩ ተቀባይነት ባለው ምክንያት ሆኖ ስላላገኘነው ውሣኔው የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ለ/ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ ነው በሚል ምክንያት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ልባል የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም መሰረት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 58518 ሚያዝያ 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 26458
No topics extracted.