No summary available.
ኀዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ቃሉቲ ባላስትራ ማምረቻ - ገ/እግዚአብሕር ተስፊዬ ጠበቃ ተጠሪ፡- ብርሃኑ ልደት ወልዳ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ተወስኗል።
ይህ ጉዲይ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረ ሲሆን አመልካች የሥር ተከሣሽ ተጠሪ ከሣሽ ነበሩ።
ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት በጥበቃ ሙያ እያገለገለ ቆይተው የሰራተኛ አበል እና ገንዘብ ሰብባቢ በመሆናቸው በሕገ ወጥ መንገድ እንደተሰናበቱ ገልፀው ውዝፍ ደሞዝ ተከፍልኝ ወደ ሥራዬ ልመለስ ወይም ተገቢው ክፍያ እንዱፈፀምልኝ በማለት ጠይቋል።
አመልካችም ለቀረበበት ክስ መልሱን ሲሰጥ ተጠሪ እንደሚለው በጥላቻ ውላቸው አልተቋረጠም የተሰናበቱት የድርጅቱ ስራ ስለቀዘቀዘ ነው። የሚገባቸውን ክፍያ ወስደው ነው የስራ ውላቸው የተቋረጠው የአገልግልትና የ”2” ወር የማስጠንቀቅያ ወስዶል። በማለት ተከራክረዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የቀረበለትን የግራ ቀኙን ክርክር ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሮታል በመሆኑም አመልካች ተጠሪ የተሰናበቱት የድርጅቱ ስራ ስለቀዘቀዘ ነው ይበል እንጂ ይህ ለመሆኑ አላስረደም። በልላ በኩል ተጠሪ በስምምነት የአገልግልትና የ”2” ወር የማስጠንቀቂያ ተከፍልት ይገልፃል ይሁን እንጂ የተደረገው ስምምነት በአዋጁ ቁጥር 24 መሰረት በጽሁፍ ለመደረጉ አላስረደም ሕጉ በሥምምነት የስራ ውለን ማቋረጥ በጽሁፍ መሆን አለበት ይላል በእርግጥ ተጠሪ የአገልግልትና የማስጠንቀቂያ ወስዶል። የተቀረውን መብታቸውን መተዋቸው በሕግ ፉት ዋጋ የለውም።
ስለዚህ ተጠሪ ውዝፍ ተከፍልኝ ወደ ስራ ልመለስ ያለውን ፍ/ቤቱ ተቀብልታል ምክንያቱም ተጠሪ ውላቸውን በጽሁፍ አላቋረጠም በማለት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው የ6 ወር ውዝፍ ከፍል ወደ ስራ ይመልሣቸው ሲል ወሰነ።
አመልካችም በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ቅሬታውን አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የስር ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት አሻሽል ተጠሪ በአዋጁ ቁጥር 43/5/ መሰረት የአንድ አመት ደመወዝ ይከፈላቸው ሲል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ላይ ነው። አመልካች ግንቦት 4 ቀን 2000 ጽፈው ባቀረቡት ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረም ጠይቋል።
ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል። ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው የተደረገው የሥራ ውል በጽሁፍ አልተቋረጠም ተብል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ባግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረት ይህን ነጥብ ግራ ቀኙ ወገኖች ካሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እኛም የጉዲዩን አመጣጥ እንዲየነው ተጠሪ ከአመልካች ድርጅት ሲሰራ ቆይቶ የአገልግልትና የማስጠንቀቂያ ክፍያ በመቀበል ከሄደ በኋላ ውዝፍ ደሞዝ ተከፍልት ወደ ሥራ እንዱመለስ ካልሆነም ክፍያ እንዱፈፀምለት የጠየቀ መሆኑን ተረድተናል። ምንም እንኳ አመልካችም በስምምነት የሚጠበቅብኝን ክፍያ ፈጽሜ አሰናብቸዋለሁ ቢልም የሥራ ውልን በስምምነት ማቋረጥ የሚቻለው በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 25/2/ መሰረት በጽሁፍ የተደረገ ሥምምነት ሲኖር ነው በተያያዘነው ጉዲይ ግን ይህ አልተፈፀመም ስለሆነም ስንብቱ ሕጋዊ ነው ለማለት አይቻልም።
ይሁን እንጂ ከመዝገቡና ከቀረበው አቤቱታ ለመረዲት እንደቻልነው ተጠሪ የአገልግልትና የማስጠንቀቂያ ስለመቀበለ የሥር መዝገብ ይገልፃል። ይህ ሆኖ እያለ በሥር ፍ/ቤት ስንብቱን ተከትል ተጠሪ ወደ ሥራው ይመለስ ውዝፍ ደሞዝ ይከፈለው ተብል ተወስኗል።
ተጠሪ ወደ ሥራው ይመለስ የሚለውን ነጥብ ስናየው ፍ/ቤት በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 43/3/ መሰረት ሰራተኛው ወደ ቀድሞ ስራቸው ቢመለሱ በስራቸው ግንኙነት ላይ ሉከሰት የሚችለውን ችግር በማጤን ሰራተኛው ካሣ ተከፍልት እንዱሰናበት ማድረግ እንደሚችለ ሕግ ይደነግጋል ይህ ሆኖ ሳለ ወደ ስራው ተጠሪ ይመለስ መባለ አግባብ አይደለም።
በተጨማሪም የውዝፍ ደሞዝን አስመልክቶ ተጠሪ ክፍያዎች (የአገልግልትና የማስጠንቀቂያ) ተከፍልት እያለ ተጨማሪ ውዝፍ ደሞዝ ይከፈለው መባለ አግባብ ያለው ሆኖ አላገኘንም ይሁን እንጂ ተጠሪ ካሣ የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለዚህ በሥር ፍ/ቤት ተጠሪ ውዝፍ ደሞዝ ተከፍልት ወደ ሥራው ይመለስ መባለ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
58532 በመጋቢት 22 ቀን 2000 የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽልአል።
ተጠሪ ወደ ስራው ሉመለስም ሆነ ውዝፍ ደሞዝ ሉከፍለው አይገባም ብለናል።
ተጠሪ የስንብትና የማስጠንቀቂያ ቀደም ሲል የተከፈለው ስለሆነ ያልተከፈለው ካሣ በሕጉ መሰረት ተከፍልት ይሰናበት ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጭ እና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.