No summary available.
ህዲር 16 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት - ነ/ፈጅ አለምፀሐይ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ መሐመድ አደን - በላለበት
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ሰራተኛው መብቱን የሚጠይቅበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ነው።
በደብቲ ወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ክስ አመልካች ያለአግባብ ከስራ ስላሰናበታቸው ወደ ስራ ለመመለስ ጠይቀዋል። አመልካችም ተጠሪ በፈፀሙት ጥፊት ከስራ መሰናበታቸው በሕጉ መሰረት መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።
የደብቲ ወረዲ ፍ/ቤትም ስንብቱ ሕገ- ወጥ ነው በማለት ተጠሪ ወደስራቸው እንዱመለሱ አልያም ካሣ ተከፍሎቸው እንዱሰናበቱ ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ የይግባኝ ቅሬታ ለዞን አንድ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ክሱ በይርጋ አይታገድም፣ ስንብቱም ሕገወጥ ነው፣ ተጠሪም ወደ ስራ ቢመለሱ መልካም ግንኙነት አይኖርም ተብል የሚገመትበት ምክንያት ስለላለ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደስራ ይመለሱ በማለት የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ አሻሽሎል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ቅሬታውም ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ሐምል 1/1999 ዓ.ም ሲሆን ክስ የመሰረቱት ጥቅምት 14/2ዐዐዐ ዓ.ም በመሆኑ ወደ ስራ ለመመለስ ያቀረቡት ጥያቄ በይርጋ ይቋረጣል የሚል ነው። የሥር ፍ/ቤቶች የይርጋውን ጥያቄ ያልተቀበለት በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል የሰበር አቤቱታ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበው መልስ እንዱሰጡ መጥሪያ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት ታይቷል።
እኛም የሰበር አቤቱታውን የሰበር አቤቱታ ከቀረበባቸው ውሣኔዎች እና ከሕጉ አኳያ መርምረናል።
ከመዝገቡ ላይ እንደተመለከትነው ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ሐምል 1/1999 ዓ.ም ነው በማለት አመልካች ባቀረበው መከራከሪያ ላይ ተጠሪ ያቀረቡት ተቃውሞ የለም እንደዚሁም ተጠሪ ወደ ስራ ለመመለስ ክስ ያቀረቡት ጥቅምት 14/2ዐዐዐ ዓ.ም መሆኑንም ግራ ቀኙ አልተካካደበትም። በመሆኑም ተጠሪ ከስራ ከተሰናበቱበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ ለመመለስ ክስ እስከመሰረቱበት ጊዜ ድረስ ሲታሰብ ከ3 ወር በላይ ነው። በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/2/ መሰረት ደግሞ ሰራተኛው የስራ ውለ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ስራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውለ በተቋረጠ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚቋረጥ ተመልክቷል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካችን የይርጋ ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ተጠሪ ፈጽመዋል በተባለት ጥፊት ክስ ተመስርቶባቸው ሲጣራ ቆይቶ ፖሉስ ከወንጀለ ነፃ መሆናቸውን ያረጋገጠው መስከረም 18/2ዐዐዐ በመሆኑ ይርጋው መቆጠር የሚጀምረው ከዚሁ ቀን ነው በማለት ነው። ይሁን እንጂ ይርጋ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች በአዋጁ አንቀጽ 164 ሥር የተዘረዘሩ ሲሆኑ ፍ/ቤቱ የገለፀው ሁኔታ ይርጋን ያቋርጣለ ተብለው ከተመለከቱት ሁኔታዎች ስር የሚካተት አይደለም። በመሆኑም ፍ/ቤቱ ተጠሪ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ጉዲዩ በፖሉስ ተጣርቶ ነፃ መሆናቸው እስኪረጋገጥ ድረስ የነበረውን ጊዜ በይርጋ አቆጣጠር ጊዜ ውስጥ አይካተትም በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህም አልፍ አመልካች ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ላይ ተጠሪ ያቀረቡት መስቀለኛ ይግባኝ እንኳን ሣይኖር ተጠሪውን በሚጠቅም መልኩ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ማሻሻለ የዲኝነት አሰራር ስርዓት አለመከተለን ያመለክታል። በአጠቃላይ የተጠሪ ወደ ስራ የመመለስ ጥያቄ ከ3 ወር በኋላ የቀረበ በመሆኑ በይርጋ ውድቅ ላደረግ ሲገባ ይህ ታልፍ በዋናው ጉዲይ ላይ ውሣኔ መሰጠቱ መሰረታዊ ስህተት የተፈፀመበት ነው።
ው ሣ ኔ
የደብቲ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ/21/2ዐዐ በ28/2/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
በአፊር ክልል የዞን አንድ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐ993 በ18/4/2ዐዐዐ የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ተጠሪ ወደ ስራ ለመመለስ ያቀረቡት ክስ በአ/ቁ. 377/96 አንቀጽ 162/2/ በይርጋ ውድቅ ሆኗል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ መዝገቡ ተዘግቷል። መዝገቡ ለመዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.