No summary available.
የሰ/መ/ ህዲር 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የንኮማድ ኃ.የተ.የግል ማህበር - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ቡሽራ በቀለ - አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዮ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ በልደር ኦፕሬተርነት ሙያ ከሚያዝያ 05 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ ሲያገለግለ መቆየታቸውንና በወቅቱም ይከፈላቸው የነበረው ወርሃዊ ደመወዝ ብር 1800.00(አንድ ሺህ ስምንት መቶ) መሆኑን ዘርዝረው ከጥር 22 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጠው የስራ ውል ያላግባብ መቋረጡን ጠቅሰው ውዝፈ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ወይም የተለያዩ ክፍያዎችን በመክፈል ከስራ እንዱያሰናብት ይወሰንላቸው ዘንድ በአሁኑ አመልካች ላይ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው ፍ/ቤቱም የአሁኑ አመልካች እንዱቀርብ ጥሪ አድርጏ አመልካች መልስ በሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ በቂ ምክንያት የላለው መሆኑን በመጥቀስ ይህንኑ መብቱን ከአለፈ በኋላ ግራ ቀኙን በቃል አከራክሮ አመልካች ተጠሪ ከአምስት ቀን በላይ ከስራ የቀረ ስለመሆኑ አላስረዲም ተጠሪም ማስረጃ ላቀርብ ስል ተከለከልኩ በማለት ክደው ተከራክረዋል የሚል ምክንያት በመያዝ ተጠሪ ከስራ የተሰናበቱት ያላግባብ ነው ሆኖም ወደ ሥራ ቢመለሱ መልካም የሆነ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ስለማይፈጥር የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍለው ተጠሪ ከስራ ይሰናበቱ በማለት ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚልባቸውን ምክንያቶች ሚያዝያ 28 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዘርዝሮ አቅርቧል። ይዘቱም በአጭሩ በስር ፍ/ቤት መልሱን በጽሐፍ የማቅረብ መብት ያለፈበትን ምክንያት ያላግባብ መሆኑ ተጠቅሶ በቀረበው የይግባኝ ቅሬታ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ ሣይሰጥበት ማለፈ ተገቢነት የላለው መሆኑን ተጠሪ ከስራ ላይ ከአምስት ቀን በላይ መቅረትቸውን በቃል ክርክር ወቅት አምነው እያለ እና የህክምና ማስረጃ ለማቅረብ ስሄድ የድርጅቱ ዘበኛ ከለከለኝ በማለት ተጠሪ የገለፁት ፍሬ ነገር በተጨባጭ ማስረጃ ተደግፍ ባልቀረበበት ሁኔታ ይህንኑ የማስረዲት ሸክም ወደ አመልካች የማዞር ውሳኔ መሰጠቱ ስህተት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ለሰበር ችልቱ ላታይ ይገባል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 26 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ቅሬታ ነጥቦችን ተቀባይነት የላላቸው መሆኑን በመዘርዘር መልስ ሰጥተዋል። አመልካች በበኩለ ሐምል 17 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዮ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ ከአምስት ቀናት በላይ በተከታታይ ከሥራ መቅረታቸውን ሣይክደ በሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪ የሐኪም ማስረጃውን ለአመልካች ላቀርብ ስል ዘበኛው ከልክልኛል በማለት ያቀረቡትን ክርክር መሰረት በማድረግ ተጠሪ የተሰናበቱት ያለአግባብ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሎቸው ከሥራ እንዱሰናበቱ የወሰኑት ውሳኔ በአግባቡ መሆኑን ያለመሆኑን ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ በስራ ገበታቸው አለመገኘታቸውን በመግለጽ ያልተገኙበት ምክንያት በህመም ሆኖ ይህንኑ ማስረጃ ለአመልካች በወቅቱ ያላቀረቡ መሆኑንና ማስረጃውን ለማቅረብ ያልቻለበት ምክንያትም የአመልካች ድርጅት ዘበኛ ወደ ግቢው ሉያስገባቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ስለመሆኑ በመግለጽ ተጠሪ የሚከራከሩ መሆኑን ነው። የበታች ፍ/ቶችም ይህንኑ የተጠሪ ክርክር በቃል ክርክር ወቅት ያረጋገጡት መሆኑን ውሣኔው ያሣያል። ተጠሪ የሀኪም ማስረጃውን ለአመልካች ያላቀረቡበት ምክንያት በዘብ ጥበቃ ግቢ እንዲይገቡ በተደረገው ድርጊት ነው ይበለ እንጂ ይህንኑ ፍሬ ጉዲይ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው ስለመሆኑ ገልፀው ያልተከራከሩ መሆኑን የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ግልባጭ ይዘት የሚይሣይ ከመሆኑም በላይ ለዚህ ችልት በሰጡት መልስም በዚህ ረገድ ማስረጃ የነበራቸው መሆኑን በመግለጽ አልተከራከሩም።
እንግዱህ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮች ከላይ የተገለፁት ከሆኑ የአመልካችን ተግባር ህገ ወጥ ሉያሰኑ የሚችለት ህጋዊ ምክንያቶች ከአዋጁ ጋር አገናዝቦ መመልከትን የግድ ይሎል።
በመሰረቱ ያለበቂ ምክንያት ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ከስራ ገበታው ያልተገኘን ሰራተኛ አሰሪው ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ማሰናበት መብት ያለው ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ያሣያል።
ይህንኑ የአሰሪን ህጋዊ መብት ሰራተኛው ሉቃወመው የሚችለው በቂ ምክንያት ኖሮት ተቀባይነት ሲያጣ ብቻ ነው ከስራ ገበታው መቅረት አከራካሪ ባልሆነበት ሁኔታ በቂ ምክንያት ስለመኖሩ የማስረዲት ሸክም ከስራ ገበታው መቅረቱን ያልካደው ሰራተኛ እንጂ አሰሪ ላሆን አይችልም እንደሚታወቀው ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ የክሱን ፍሬ ነገር እንዱረጋገጥለት ዲኝነት የሚጠይቅ ወገን ነው። በልላ አገላለጽ ከሣሽ ክሱን የሚያስረዲ ማስረጃ (Prima facie evidence) የማቅረብ ግዳታ አለበት ይኸው ግዳታ ወደ ላላው ተከራካሪ ወገን ሉተላለፍ የሚችለው ክሱን ለማስረዲት የቀረበው ማስረጃ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ብቃት ነው።
በእጃችን ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ ከስራ ገበታቸው ቀረሁ የሚለበትን ምክንያት ለማስረዲት የህክምና ማስረጃ አለኝ ቢለም ይህኑ ማስረጃ ለአመልካች አላቀረቡም። ለአመልካች የህክምና ማስረጃውን አለማቅረባቸውን ገልፀው ማስረጃውን ለማቅረብ የተቸገሩበትን ምክንያት በመጥቀስ ተከራክረዋል። ተጠሪ ይኸው ፍሬ ነገር በማስረጃ የተደገፈ ስለመሆኑ ግን አይገልፅም። የህክምና ማስረጃውን በወቅቱ ይዘው ለአመልካች ያላቀረቡት ምክንያት በአመልካች ዘብ ጥበቃ በተደረገባቸው ክልከላ መሆኑ የማስረዲት ገዳታ ደግሞ የተጠሪ ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት ተጠሪ ክደው ተከራክረዋል በሚል ምክንያት ብቻ የማስረዲት ሸክሙን ወደ አመልካች በማዞር ውሣኔ መስጠቱ የማስረጃ አቀራረብ ግዳታ መርህንና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መንፈስ ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ ተገኝቷል። ተጠሪ ተገቢውን ማስረጃ ባላቀረቡበት ሁኔታ ደግሞ የአመልካች እርምጃ ህገ ወጥ ነው ልባል ሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ሲጠቃለልም ተጠሪ ከስራ ገበታቸው ከአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በላይ መቅረታቸውን በግልጽ አምነው ተከራክረው እያለና ለዚህ ከስራ ለቀሩበት ጊዜም በቂ ምክንያት ያላቸው መሆኑን የማስረዲት ግዳታ ባልተወጡበት ሁኔታ የማስረዲት ሸክሙ ወደ አመልካች በማዞር እርምጃው ህገ ወጥ ነው ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
No topics extracted.