No summary available.
ኀዲር ዐ4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዱስ አበባ የምግብ አዲራሽ አስተዲደር - ነ/ፈጅ ኢሣያስ ኃይለ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ የውብዲር ጥላሁን - ቀረቡ።
መዝገቡን መረምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ድርጅት ውስጥ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ በወር ብር 536.90 (ሦስት መቶ ሰላሣ ስድስት ብር ከዘጠና ሣንቲም) እየተከፈላቸው በገንዘብ ያዥነት እየሰሩ ባለበት ሁኔታ በዓቃቤ ሕግ በኩል ክስ በመመስረቱ የስራ ውላቸው ተቋርጦ መቆየቱንና በኋላም ይኸው ክስ በመዘጋቱ ምክንያት አመልካች ከታህሣሥ 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ስራ የመለሣቸው ቢሆንም የተቋረጠውን ደመወዝ ያልከፈላቸው መሆኑንና ወደ ቀድሞው ስራ ያልመለሣቸው መሆኑን በመዘርዘር ከሐምል 1ዐ ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን ደመወዝ ወደ ሥራ አስከተመለሱበት ቀን ያለውን አስቦ እንዱከፍላቸውና ወደ ቀድሞው የገንዘብ ያዥነት ሥራቸው ከደመወዝ ጭማሪና ከኪሣራ ጋር እንዱመልሣቸው ይወስንላቸው ዘነድ በአመልካች ላይ ታህሣሥ 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በፍ/ቤቱ ጥሪ መሰረት ቀርቦ ጉዲዩ በመደበኛ ፍ/ቤት ላታይ የማይችልበትን ምክንያት በመጥቀስ በመጀሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ከመከራከሩም በተጨማሪ በፍሬ ነገር ረገድም ተጠሪ ከስራ የታገደበት ገንዘብ አጉድለው በመገኘታቸውና የተወሰነ ገንዘብ መልሰው ቀሪውን ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው አለመገኘታቸውን፣ ወደ ሥራ የተመለሱትም ካላቸው የቤተሰብ ኃላፉነት ታይቶ መሆኑን ወደ ቀድሞው የሥራ መደብ ለመመለስ ያልቻለው ከተጠሪ ጥፊት አንፃር መሆኑንና ባልነበሩበት ጊዜ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጥያቄ ማቅረብ የማይችለ መሆናቸውን በነጥብነት በማንሣት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በአመልካች በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቀባይነት የላለው መሆኑን በመጥቀስ ውድቅ ከአደረገው በኋላ የስራ ውል የሚሻሻልበትን የሕግ ምክንያት በመዘርዘርና አመልካች የስራ መደቡን ሲቀይር የስራ ውል የማሻሻል ውጤት የሚኖረው መሆኑን በመግለጽ የአመልካችን እርምጃ ሕገ ወጥ ነው በማለት ተጠሪን የአራት ወር ደመወዝ ከፍል ወደ ቀድሞ የስራ መደብ እንዱመልሳቸው ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን ሰርዞታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የስር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚልባቸውን ምክንያቶች ሚያዝያ 16 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ዘርዝሮ አቅርቧል። ይዘቱም በአጭሩ ጉዲዩ መታየት የነበረበት በአስማሚ መሆኑን፣ ተጠሪ የአመልካችን ገንዘብ ማጉደላቸው ተረጋጋጦ እያለ ወደ ቀድሞ ስራቸው ይመለስ መባለ ስህተት መሆኑን፣ ላልሰሩበትና ታግደው ለቆዩበት ጊዜ የአራት ወር ደመወዝ እንዱከፈል መወሰኑ አግባብነት የላለው መሆኑና የአመልካች ምስክሮች አለመስማታቸውን ተገቢነት ያለው አለመሆኑን በመዘርዘር የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ግንቦት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። አመልካች በበኩለ ሐምል ዐ3 ቀን 2ዐዐዐ በተፃፈ ማመልከቻ የመልስ መልሱን አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጭብጥ ተጠሪ የአራት ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ቀድሞው ስራ እንዱመለሱ ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ነው።
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ በአመልካች ድርጅት በገንዘብ ያዣነት የስራ መደብ ተቀጥረው ሲሰሩ መቆየታቸው በስራው አጋጣሚ ወደ እጃቸው ከገባው የአመልካች ገንዘብ ውሰጥም ብር 4219.00 /አራት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር/ አጉድለው ብር 195ዐ.00 /አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ብር/ መልሰው ቀሪውን ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከስራቸው ታግደው መቆታቸውና በዚህም ወቅት በዓቃቤ ሕግ በኩል ክስ ተመስርቶባቸው የነበረ ቢሆንም ክሱ ተዘግቶ በነፃ የተሰናበቱ መሆኑ የተረጋገጡ ጉዲዮች ናቸው። ከዚህም የምንገነዘበው ተጠሪ ገንዘብ ማጉደላቸውን ሣይክደ በዓቃቤ ሕግ በኩል መዝገቡ ተዘግቶ በነፃ ተሰናብቼአለሁ በማለት ብቻ የሚከራከሩ መሆኑን ነው። እንዱህ ከሆነ ምላሽ የሚያስፈልገው ጥያቄ ተጠሪ በዓቃቤ ሕግ በኩል በተመሰረተው የወንጀል ክስ ነፃ ወጥቻለሁና ወደቀድሞ ሥራ ልመለስ ይገባል ሲለ ያቀረቡት ጉዲይ በሕግ በኩል ድጋፍ አለውን? የሚል ነው።
በመሰረቱ የወንጀል ክስና የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት አድርጎ የሚቀርብ ክስ የተለያየ ይዘትና ዓላማ ያላቸው ከመሆኑም በላይ በማስረጃ አመዛዘን ረገድም የተለያዩ መርሆዎችን መሰረት የሚያደርጉ ናቸው። በልላ አገላለጽ የወንጀል ክስ ለጠቅላላው ማኀበረሰብ ጥቅም ሲባል የሚወሰድ መንግሥታዊና ማኀበረሰባዊ እርምጃ ሲሆን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት የሚያደርግ ክስ ግን እንደ ወንጀለ ስፊት ያለው ይዘት የውስጥ ድርጅት እርምጃ ነው።
የወንጀል ክስ እርምጃ ሉያሣካ የሚያልመው ዓላማ በማኀበረሰቡ ሰላምና ደህንነት አለታዊ ተጽዔኖ የሚያሣድሩ ባሕርያትን ማረምና ማደስ ሲሆን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት የሚያደርጉ ክሶች እርምጃቸው ኢንደስትሪያላዊ ሰላምን ማስፈንና የሥራ ዋስትናን ማስከበር መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም ሁለቱም ክሶች የተለያየ ይዘትና ዓላማ ያላቸው መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም።
ከዚህም በተጨማሪ የወንጀል ክስ የማስረጃ ምዘና መርህ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የፀዲ /Beyond reasonable doubt/ የሚል ሲሆን በዚህ የማስረጃ አመዛዘን መርህ መሰረት በወንጀል ጥፊተኛ ለማሰኘት ጠንካራና የማያሻማ ማስረጃ የሚፈለግ ሲሆን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት የሚያደርግ ክስ በባሕሪይው ከዱሲፕሉን እርምጃ ጋር እጅጉን የተቆራኘ በመሆኑ እንደማንኛውም የዱሲፕሉን ክስ ተፈፃሚነት የሚኖረው የማስረጃ ምዘና መርህ ከወንጀል ክስ የማስረጃ ምዘና ላላ ያለ ነው። በመሆኑም በወንጀል ተከሶ ነፃ የሚወጣ ሰራተኛ በዱፕሉን ቢከሰስ አጥፉ ሆኖ የመገኘት ዔድለ ሰፉ ላሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት የወንጀል ክስ ነፃ በማውጣት ብቻ አንድ ሰራተኛ ወደ ቀድሞ ሥራ ልመለስ ይገባል በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ የሕግ ድጋፍ አይኖረውም። ስለሆነም የሰራተኛው ጥያቄ ሉስተናገድ የሚገባው ላላ ያለ የማስረጃ ምዘና መሰረት ተደርጎ ለአድራጎቱ ተጠያቂ ሆኖ መገኘት አለመገኘቱን መሰረት በማድረግ ነው።
እጃችን ወደአለው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ የአመልካችን ገንዘብ ማጉደላቸውን አምነው ተመላሽ ማድረጋቸውን በመግለጽ መከራከራቸውን የሥር ፍ/ቤት አረጋግጧል። አመልካች ተጠሪን ወደቀድሞው ሥራ ባይመልሣቸውም በልላ የሥራ መደብ በመመደብ እንዱሰሩ ፈቅዶል። የበታች ፍ/ቤቶች ይህንኑ የአመልካችን እርምጃ ሕገወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 15 ሥር የተመለከቱትን የሥራ ውል ማሻሻያ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ እና በእነዚህ ምክንያቶች የተፈፀመ ስለመሆኑ አላስረዲም በሚል ነው። ይሁን እንጂ አመልካች የተጠሪ የስራ መደብ ለውጥ ያደረገው ተጠሪ የገንዘብ ጉድለት ስለአስከተለ መሆኑ ሲታይ እርምጃው ይህንን አጠቃላይ መንፈስ የሚጋጭ ነው ልባል የሚገባው አይደለም ለሰራተኛ አግባብነት ያለውን የሥራ መደብ በመስጠት የማሰራት ኃላፉነትም ከአሰሪው የአስተዲደር ስራ ነፃነት /managerial prerogative power/ ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። አሰሪው በንብረቱ ላይ ጉዲት ያደረሰ ሰራተኛን ከስራው ያለማስጠንቀቂያ ለማባረር የሚችል ስለመሆኑም የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1ሸ) ድንጋጌ ያስረዲል። ተጠሪ ከወንጀለ ክስ ነፃ ወጥቻለሁ ከማለት ውጪ የገንዘብ ጉድለት አልተከሰተም በማለት አልተከራከራከሩም። በመሆኑም የገንዘብ ጉድለቱ መከሰቱ አከራካሪ አይደለም። እንዱህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ ወደቀድሞ የስራ ገበታቸው የሚመለሱበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። አዋጁ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/(ሐ),(መ) እና (ሸ) ድንጋጌዎች መሰረት አሰሪው የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ የሚያቋርጥበትን ሁኔታ ያስቀመጠበት ዓላማ ሲታይም ሰራተኛው ስራውን በታማኝነት እንዱያከናውን ለማድረግ መሆኑ ይታመናል። አንድ ሰራተኛ ታማኝነት የላለው መሆኑ ከታወቀ በኋላ ደግሞ አሰሪው ወደ ቀድሞ ሥራ እንዱመልሰው ማድረግ ሕጉን ለማሣካት ያለውን ግብ የሚፃረርም ጭምር ነው።
በአጠቃላይ የሥር ፍ/ቤት የአመልካች እምርጃ ሕገወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደሰረሰው በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር ባላገናዘበና የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 15”ን” ያለቦታው በመጥቀስ ከመሆኑም በተጨማሪ የሕጉንም አጠቃላይ መንፈስ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 234ዐ1 የካቲት 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 6477ዐ ሚያዝያ 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
ተጠሪ ወደ ገንዘብ ያዥነት ሥራ ሉመለሱ አይገባም በማለት ወስነናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.