No summary available.
ህዲር 2 ቀን 2001 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብድልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ -ነ/ፈጅ መ/ኩ መለሰ ተጠሪ፡- አቶ ሳህለ ምትኩ - አልቀረቡም ከተባለ በኋላ እንዲልካቸው ይላቅ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ስንብት ክፍያ የሚከፈልበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው።
በአሁኑ ተጠሪ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዲቸው የለቀቁ ቢሆንም ከአምስት አመት በላይ የሰሩ በመሆኑ የስራ ስንብት እንዱፈቀድላቸው ጠይቀዋል። አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪ ከአምስት አመት በላይ የሰሩ ቢሆንም የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ በመሆናቸው የስንብት ክፍያ አይገባቸውም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ አያገኝም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ላይ ተጠሪ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ በጡረታ ህግ የተመለከተውን መደበኛ የጡረታ እድሜ ላይ ደርሶ ከስራ እስካልተገለለ ድረስ ክፍያ አይከለክልም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮ ለተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ እንዱሰጣቸው ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስለወጥ ነው።
ይህ ችልት የአመልካችን አቤቱታ መርምሮ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ያለው መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታውን ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረጉ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጹሁፍ አቅርበዋል ችልቱም የአመልካችን አቤቱታ ስህተት ተፈጽሞበታል ከተባለው ውሳኔና አግባብነት ካለው ህግ አኳያ መርምሯል።
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የስራ ስንብት ክፍያ መብትን የሚመለከት ነው።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39 ስር የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈል የሚገባውን ሁኔታዎች ዘርዝሮ አስቀምጧል በዚሁ አንቀጽ ከፉደል ’'ሀ’' እስከ ’'ረ’' ድረስ ተዘርዝረው በተቀመጡት ሁኔታዎች መሰረት የሰራተኛው ጥፊት ባልሆነ ምክንያት አሰሪው የስራ ውለን ሲያቋርጥ ወይም በአሰሪው ጥፊት ወይም በሰራተኛው የጤና ሁኔታ ሰራተኛው በፈቃደ ስራውን ሲለቅ የስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ያለው መሆኑን ያመላክታለ። በልላ በኩል ደግሞ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 494/98 በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 39(1) ስር አዱስ ድንጋጌዎችን ጨምሯል።
በዚህም መሰረት ሰ. የፕሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም ጡረታ መብት የላለው ሲሆንና በጡረታ ህግ የተመለከተው መደበኛ የጡረታ ዔድሜ ደርሶ ከስራ ሲገለል፣ ሸ. ቢያንስ አምስት ዓመት በአሰሪው ዘንድ የስራ አገልግልት ኖሮት በህመም ወይም በሞት የስራ ውለ ሲቋረጥ ወይም የስራው ላይ የሚያስቆይ ከስልጠና ጋር የተያያዘ ለአሰሪው የውል ግዳታ ሳይኖርበት ስራውን በገዛ ፈቃደ ሲለቅ ቀ. በኤች አይ ቪ ኤድስ ህመም ምክንያት በራሱ ጥያቄ የስራ ውለ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ ማግኘት የሚችል መሆኑን ተቀምጠDል።
ይህ የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 2 ቀደም ሲል በአ/ቁ 377/96 አንቀጽ 39 (1) ስር ያልተካተቱ አዱስ ሁኔታዎች ተጨምረዋል ይኸውም አንድ ሰራተኛ በገዛ ፈቃደ ስራውን ቢለቅ እንኳን የተወሰኑ ሁኔታዎች እስከተሟለ ድረስ የስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ተሰጥቶታል። እነዚህም ሁኔታዎች ከፉደል ’'ሰ’' እስከ ’'ቀ’' የተመለከቱት ናቸው ። በተለይ ከተያዘው ጉዲይ ጋር አግባብነት ያላቸው በፉደል “ሰ” እና “ሸ” የተመለከቱት ናቸው። በፉደል ’'ሸ’' እንደተመለከተው ቢያንስ አምስት ዓመት ከሰራና በህመም ወይም በሞት ስራ ውለ ከተቋረጠ ወይም ከስልጠና ጋር በተያያዘ ስራው ላይ የሚያስቆይ ለአሰሪው የውል ግዳታ ከላለበት የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት ይኖረዋል። ነገር ግን ይህ ድንጋጌ በተናጠል ሳይሆን በፉደል ’'ሸ’ ስር ከተመለከተው ጋር ተገናዝቦ ላታይ ይገባዋል። በዚህም መሰረት አንድ ሰራተኛ ከ5 ዓመት በላይ የሰራ ቢሆንም እንኳን የስንብት ክፍያ ማግኘት የሚችለው የፕሮቪደንት ወይም የጡረታ መብት ከላለውና የጡረታ ዔድሜው ደርሶ ከስራ ከተገለለ ነው።
የስር ፍ/ቤትም እነዚህ ሁለት ንዐሳን ቁጥሮች በአንድነት ተገንዝበው መተርጎም ያለባቸው መሆኑን ቢቀበልም የስንብት ክፍያ የሚከለከለው የፕሮቪደንት ፈንድ መብት ኖሮት የጡረታ ዔድሜው ደርሶ ከስራ ከተሰናበተ ወይም የጡረታ መብት ኖሮት የጡረታ እድሜው ደርሶ ከስራ ከተሰናበተ መሆኑን አትቷል። በልላ አነጋገር የስንብት ክፍያ በመከልከል የፕሮቪደንት ፈንድ መብት መኖርና የጡረታ እድሜ ደርሶ ከስራ መገለል በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው።
ስለሆነም የጡረታው ዔድሜ ሳይደርስ በገዛ ፈቃደ ከስራ የለቀቀ ሰራተኛ የፕሮቪደንት ፈንድ መብት ያለው ቢሆንም ዔድሜው ደርሶ በጡረታ የተገለለ ባለመሆኑ ምክንያት የፕሮቪደንት ፈንድ የማግኘት መብት ያለው ነው በማለት ለድንጋጌው ትርጉም ሰጥቶታል።
ይህ ችልትም እነዚህ ሁለት ንዐሳን ቁጥሮች ግልፅ ባለመሆናቸው ትርጉም የሚያስፈልጋቸው መሆኑን አምኗል።
ድንጋጌዎች ግልፅ ባልሆኑ ግዜም በመጀመሪያ ሉተረጎሙ የሚገባው የህግ አውጭውን ሐሳብ በመፈለግ መሆኑ የሕግ አተረጓጎም መርህ ያመለክታል። በመሆኑም የእነዚህ ድንጋጌዎች አላማ ማወቁ ተገቢ ይሆናል።
የስራ ስንብት ክፍያ ዋነኛው አላማ አንድ ሰራተኛ ከስራ ሲሰናበት ችግር ላይ እንዲይወድቅ ራሱን እንዱያቋቁም ለመርዲት ነው። እንዱሁም የኘሮቪደንትና የጡረታ አላማም ቢሆን አንድ ሰራተኛ ዔድሜው ደርሶ በጡረታ ቢገለል የሚጦርበት የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ነው። በእርግጥ ኘሮቪደንት ፈንድና ጡረታ ተመሣሣይ አላማ ያላቸው ቢሆንም የጡረታ ክፍያ የሚጀምረው አንድ ሰው የጡረታ ዔድሜው ደርሶ ሲሰናበት ሲሆን አከፊፈለም በአንዳ ሣይሆን በየወሩ የሚከፈል ነው ፕሮቪደንት ፈንድ ግን ሰራተኛው ከስራ ሲወጣ (የጡረታ ዔድሜው ደርሶ ላሆን ይችላል ወይም ሳይደርስ) በአንድ ግዜ የሚከፈል ነው። በመሆኑም በአከፊፈል በኩል በሁለቱ መሃከል ልዩነት መኖሩ ሉዘነጋ አይገባም። በአከፊፈል ያለው ልዩነት እንዲለ ሆኖ ግን ሁለቱም ክፍያዎች ሰራተኛው ከስራ ሲሰናበት ችግር እንዲይገጥመው የሚከፈለ በመሆናቸው የስንብት ክፍያ አላማን የሚጋሩ ናቸው። ስለሆነም አንደ ሰራተኛ ከስራ በሚወጣበት ጊዜ የፕሮቪደንት ፈንድ ወይም ጡረታ የሚከፈለው ከሆነ በድጋሚ የስራ ስንብት ክፍያ እንዲይከፈለውና በሁለት መንገድ ተጠቃሚ እንዲይሆን ታስበው የወጡ ድንጋጌዎች ናቸው።
በልላ በኩል አንድ ሰራተኛ ለ5 እና 6 ዓመታት ሰርቶ የጡረታ ዔድሜው ሳይደርስ በራሱ ፈቃድ ከስራ በመልቀቁ ብቻ ከፕሮቪደንት ፈንድ በተጨማሪ ስንብት ክፍያ እንዱያገኝና ላላው ደግሞ እስከ ጡረታ ዔድሜው ድረስ በመስራቱ ፕሮቪደንት ፈንድ ካለው ስንብት ክፍያ እንዱከለከል ማድረጉ በሰራተኞች መሃከል ልዩነት የሚፈጥርና ፍትሐዊ ባለመሆኑ ህጉ ይህን ልዩነት የመፍጠር አላማ ይዞ የወጣ ነው ለማለት አልቻልንም።
በመሆኑም አንድ ሰራተኛ አምስት አመትና ከዚያ በላይ የሰራ ከሆነና በራሱ ፈቃድ ስራ ከለቀቀ የስራ ስንብት ክፍያ ለማግኘት የሚችለው ስራ በለቀቀበት ሰዓት የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ወይም የጡረታ መብት ተጠቃሚ ካልሆነ ብቻ ነው።
ስራውን በለቀቀበት ሰዓት ፕሮቪደንት ፈንድ የሚከፈለው ወይም በጡረታ መብቱን መገልገል የሚጀምር ከሆነ ግን 5 አመትና ከዛ በላይ መስራቱ ብቻውን የስንብት ክፍያ መብት አያስገኝለትም። ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የጡረታ እድሜው ደርሶ በጡረታ ከስራ እስካልተገለለ ድረስ ፕሮቪደንት ፈንድ ማግኘት ይችላል በማለት የደረሰበትን መደምደሚያ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል ይህንኑ የህጉን ድንጋጌ በተመለከተ በመ/ የተሰጠውን የህጉን ትንታኔም መመልከት ይቻላል።
No topics extracted.