No summary available.
ኀዲር 2 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያና የጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት - ወይንሸት እንድሪስ ቀረበ።
ተጠሪ፡- ተሾመ ኩማ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የሚታይ የስራ ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ ክሰ የመሰረተውም የስራ ውላ ከሕግ ውጪ ተቋርጦብኛል።
ስለዚህም ውዝፍ ደመወዜ ተከፍልኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካችም ለክሱ በሰጠው መልስ የሥራ ውለ የተቋረጠው ተጠሪ በፈጸመው ሕገ ወጥ ድርጊት ምክንያት ነው። ድርጊቱ ከሥራ የሚያሰናብት ነው በማለት የተከራከረ ሲሆን ፍ/ቤቱም ክርክሩን ከሰማ በኋላ፣ አመልካች የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃ የወሰደው ድርጊቱ ከተፈጸመ ከአንድ ወር በኋላ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ተጠሪ የስድስት ወር ደመወዝ ተከፍልት ወደ ሥራው እንዱመለስ ወስኖአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠው ብይን ጉድለት የለበትም ብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች መጋቢት 5 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች የወሰደው የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃ በይርጋ የታገደ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ብይን እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከአመልካች የቀረበውን የስረ-ነገር ክርክር አልሰማም።
ባጭሩ ብይኑን የሰጠው የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው ለውለ መቋረጥ ምክንያት ነው የተባለው ድርጊት /ጥፊት/ ከተፈጸመ አንድ ወር ካለፈ በኋላ በመሆኑ በይርጋ ታግድአል በማለት ነው። በመሆኑም በአሁኑ ደረጃ ሉመረመርና ውሣኔ ለሰጠው የሚገባው ነጥብ በእርግጥ ለክርክሩ አወሳሰን በዋቢነት የተጠቀሰው የአዋጅ ቁ. 337/96 አንቀጽ 27/3/ የሚለይው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንደሚለው ነው ወይ የሚለው ነው። ከዚህም ጋር በማያያዝ ድርጊቱ በተፈጸመበት እና አመልካች የሥራ ውል የማቋረጥ እርምጃ በወሰደበት መሃከል ያለው ጊዜ ምን ያሕል ነው የሚለው የፍሬ ነገር ሁኔታም መታየት ያለበት ነው።
ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር በተለይ ደግሞ አቤቱታ ከቀረበበት ብይን ይዘት መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ ጥፊቱን /ድርጊቱን/ ፈጸመ የተባለው መስከረም 24 እና 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ሲሆን፣ አመልካች የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃ የወሰደው ጥቅምት 25 ቀን ነው። ይህ እንግዱህ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሕጉ ምን ይላል የሚለውን ደግሞ ቀጥለን እንመልከት። የአዋጁ አንቀጽ 27 አሰሪው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ማቋረጥ የሚችልባቸውን ምክንያቶች /ሁኔታዎች/ በዝርዝር የያዘ ነው። የዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ /3/”ም” አሰሪው የስራ ውለን ለማቋረጥ ያለው መብት በይርጋ የሚቀርበትን ምክንያት ይዟል። ይህም የሚሆነው /የስራ ውለን ለማቋረጥ ያለው መብት በይርጋ ቀሪ የሚሆነው/ ውለ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት ከ3ዐ /ሰላሣ/ የሥራ ቀናት በኋላ እንደሆነ በሕጉ በግልጽ ተቀምጦአል። እዚህ ላይ በሚገባ ሉተኮርበት የሚገባውም “የስራ ቀናት” የሚለው ሐረግ ነው። በሕጉ አባባል አሰሪው መብቱን በይርጋ የሚያጣው /የሚቀርበት/ ሰላሣ ቀናት ወይም አንድ መሆን አለባቸው። በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ከመስከረም 24 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 1999 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ የሚታሰበው ቢያንስ እሁድን ጨምሮ ነው። እሁድ የስራ ቀን አይደለም ብለን ብንወስድ አራት እሁድች እንዲለ እንገነዘባለን። በዚህ ስላት መሰረትም አመልካች የስራ ውል የማቋረጥ እርምጃውን የወሰደው ተጠሪ ፈጸመ የተባለው ድርጊት /ጥፊት/ መከሰቱን ባወቀ በ26ኛው የስራ ቀን ነው ማለት ነው። በመሆኑም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዲለው የአመልካች መብት በይርጋ የታገደ ወይም ቀሪ የሆነ አይደለም። ተጠቃል ቢታይ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል። ስለዚህም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 25115 ሰኔ 26 ቀን 1999 ዓ.ም. ተሰጥቶ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 5768ዐ ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ በሰጠው ትዕዛዝ የፀናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
አመልካች የስራ ውል የማቋረጥ መብቱ በይርጋ አልታገደበትም ብለናል። ስለዚህ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር በዚያው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግ የስራ ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው ወይስ ከሕግ ውጪ ነው በሚለው ጭብጥ ላይ ከግራ ቀኝ ወገኖች የሚቀርብለትን ክርክር ከሰማ በኋላ የመሰለውን ውሣኔ ይስጥ በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341 መሰረት ይመለስለት ብለናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራ በሚመለከት የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ይመለስ።
No topics extracted.