No summary available.
ህዲር 02 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ዓለማየሁ ጠ/ሥራ ተቋራጭ - ጠ/ሃይለማርያም ኢቲቻ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አብዮት በፈቃደ - ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። ተጠሪ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ ያለአግባብ ከስራ ስለተሰናበቱ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። አመልካች ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ አስቸኳይ ስራ ስላለ በሣምንት እረፍት ቀን ስራ እንዱገቡ ተጠይቀው እምቢተኛ ሆነው በአመልካች ላይ ጉዲት በማድረሣቸው ነው ሲል ተከራክሯል ፍ/ቤቱም ተጠሪ በእሁድ ቀን ለምን አልሰሩም ተብለው መባረራቸው ተገቢነት ስለላለው በግራ ቀኙ የተቆጠሩትን ምስክሮች ማስቀረብ ሣያስፈልግ ስንብቱ ህገወጥ በመሆኑ የተለያየ ክፍያ እንዱከፈላቸው በማለት ወስኗል። ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም የአመልካችን ይግባኝ ቅሬታ ሣይቀበል ቀርቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች ቅሬታም ለስራ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በእረፍት ጊዜ መስራት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚጥለው ግዳታ በመሆኑ ውሣኔው ስህተት ነው የሚል ነው። ሰበር ችልትም ይህንኑ ነጥብ ለማጣራት ተጠሪ እንዱቀርቡ በማድረጉ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፅሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም የአመልካችን ቅሬታ የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና ከህጉ ጋር አገናዝቦ መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀው አመልካች ተጠሪን ከስራ ማሰናበቱን ሣይክድ ያሰናበታቸው ግን በሣምንት እረፍት ቀን አስቸኳይ ስራ ገጥሞ እንዱሰሩ ተጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በድርጅቱ ላይ ጉዲት በማድረሣቸው መሆኑን ተከራክሯል። በመሆኑም በሣምንት እረፍት ቀን ሰራተኛው እንዱሰራ በአሰሪው ታዞ ፈቃደኛ አለመሆኑ ከስራ ለማሰናበት በቂ ምክንያት መሆን አለመሆኑን መመርመር ተገቢ ይሆናል።
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 69(1) መሰረት ማንኛውም ሰራተኛ በሰባት ቀናት ጊዜ ውስጥ ያልተቆራረጠ ከ24 ሰዓት የማያንስ የሣምንት እረፍት ሉያገኝ እንደሚገባ በአስገዲጅነት ተቀምጧል በመሆኑም በመርህ ደረጃ ማንኛውም ሰራተኛ አንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ቀን ያላነሰ የሣምንት እረፍት የማግኘት መብት አለው።
ከዚህ አጠቃላይ መርህ በተለየ ሁኔታ ግን ሰራተኛው በሣምንት እረፍቱ ሥራ እንዱሰራ ማድረግ የሚቻል መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 71(1) ሥር ተመልክቷል። ይኸውም በዚሁ ድንጋጌ ከፉደል ሀ-ሐ የመለከቱት ምክንያቶች ሲያጋጥሙና የድርጅቱን መደበኛ ተግባር የሚያደናቅፍ ሁኔታዎችን ለማስወገድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሰራተኛው በማንኛውም የሣምንት የዔረፍት ጊዜው እንዱሰራ ማድረግ ይችላል። እነዚህም ምክንያቶች ሀ/ አደጋ ሲደርስ ወይም የሚደርስ መሆኑ ሲያሰጋ ለ/ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም ሐ/ በአስቸኳይ የሚሰራ ሥራ ሲያጋጥም ናቸው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች የሚከራከረው አስቸኳይ ስራ አጋጥሞ ተጠሪ በእረፍት ቀናቸው እንዱሰሩ ቢጠየቁ ፈቃደኛ ሣይሆኑ በመቅረት በአሰሪው ላይ ጉዲት በመድረሱ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ነው። ከፍ ሲል እንደተገለፀው ምንም እንኳን በመርህ ደረጃ አንድ ሰራተኛ በሣምንት ውስጥ ከ24 ሰዓታት ያላነሰ የሣምንት እረፍት የማግኘት መብት ቢኖረውም በአስቸኳይ የሚሰራ ስራ ባጋጠመ ጊዜ ግን በማንኛውም የሣምንት እረፍት ሰራተኛው ሥራ የመሥራት ግዳታ ህጉ ጥልበታል። በአዋጁ አንቀፅ 13(7) ሥር ሰራተኛው የአዋጁን ድንጋጌዎች ጨምሮ የህብረት ስምምነቱን፣ የስራ ደንቡንና በህግ መሰረት የሚተላለፍ መመሪያዎችንና ትዔዛዞችን የማክበር ግዳታ አለበት ሰራተኛው እነዚህን ህጎችና ደንቦች የሚጥስ መሆኑ ከተረጋገጠ የስራ ግዳታውንና ኃላፉነቱን ባለመወጣቱ አሰሪው ሉያሰናብተው የማይችልበት ምክንያት የለም።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የአዋጁን ድንጋጌ ባለማክበራቸው የተሰናበቱ መሆኑን አመልካች ተከራክሯል። አመልካች አስቸኳይ ስራ በማጋጠሙ ተጠሪ በሣምንት እረፍታቸው እንዱሰሩ መጠየቁን እና ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጿል። የስር ፍ/ቤትም በአዋጁ አንቀፅ 71(1)(ሐ) ሥር የተመለከተው ሁኔታ መከሰት አለመከሰቱን በማጣራት ተገቢውን ውሣኔ መስጠት ሲገባው በሣምንት እረፍት እንዱሰሩ መጠየቁ ብቻ ህገ-ወጥ ነው በማለት በግራ ቀኙ የተቆጠሩትን ማስረጃዎች ሣይሰማ የሰጠው ውሣኔ ከፍ ሲል የተመለከቱትን የአዋጁን ድንጋጌዎች ያላገናዘበና ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ በ37659 በ28/6/2000 የሰጠው ውሣኔና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 6704 በ8/9/2000 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል።
2/ ተጠሪ በሣምንት እረፍታቸው እንዱሰሩ የታዘዙት በአዋጁ አንቀፅ 71(1)(ሐ) መሰረት አስቸኳይ የሚሰራ ስራ አጋጥሞ መሆን አለመሆኑን የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ በማጣራት ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩ ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 343(1) መሰረት ተመልሷል።
3/ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.