No summary available.
ኀዲር 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ደረጀ ማሞ - አልቀረበም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ መስከረም 15 ቀን 1999 ዓ.ም በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም በአጭሩ፡በአመልካች ድርጅት ከጥር 06 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ በፀሐፉነት የስራ መደብ ተቀጥረው እየሰሩ መቆየታቸውን፣ ከዚሁ የስራ መደብ ላይ የቲኬት ሽያጭ ስራ መደብ ደርበው እንዱሰሩ ተደርጏ የብር 5,918.00/አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ብር/ የገንዘብ ጉድለት የተከሰተባቸው መሆኑን፣ በዚህም ምክንያት የድርጅቱን ገንዘብ ለግል ጥቅም አውለዋል ተብለው ያላግባብ ከስራ መሰናበታቸውን ዘርዝረው ስንብቱ ሕገ ወጥ በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ የተሰናበቱበት ክፍያ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ እና ወጪና ኪሣራ እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ሲሆን የአሁኑ አመልካች በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ ለግል ጥቅማቸው ያዋለት መሆኑን አለመካዲቸውን በመጥቀስ በሕብረት ስምምነቱ አባሪ/1/ሀ(3) መሰረት የተወሰደባቸውን እርምጃ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙ የቃል ክርክርና የተከሣሽን ምስክር ቃል ከሰማ በኋላ ተጠሪ የገንዘብ ጉድለት የተገኘባቸው መሆኑ ቢረጋገጥም ጏደለ የተባለውን የገንዘብ መጠን ለግል ጥቅማቸው ያዋለ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበ አሣማኝ ማስረጃ ባለመኖሩ አመልካች የሕብረት ስምምነቱን ጠቅሶ ተጠሪን ማሰናበቱ አግባብ አይደለም በማለት ተጠሪ የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ምድብ ስራቸው እንዱመለሱ ወስኗል።
የአሁኑ አመልካች በዚህ የስር ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ ባለመስማማት በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥር 29 ቀን 2000 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም በአጭሩ፡- ተጠሪ በስራቸው አጋጣሚ በእጃቸው ሉገባ የቻለውን ብር 5,918.00 ሉጏድልባቸው የቻለው በስልጠና ማነስና ከስራ ጫና የመጣ ነው ከማለት ውጪ ገንዘቡን ለግል ጥቅሜ አላዋልኩም በማለት ባልተከራከሩበት ሁኔታ ገንዘቡን ካልመለሱ ደግሞ ለግል ጥቅማቸው እንዲዋለ ህጋዊ ግምት የሚወሰድበት ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤቶች የደረሱበት ድምዲሜ ተቀባይነት በላለው መመዘኛ ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 28 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ ጥፊተኛ ስለመሆናቸው የቀረበ ማስረጃ በላለበት እና መከላከያ ባልቀረበበት ጉዲይ የክርክር ጭብጥ ተነስቶ የሰበር አቤቱታ መቅረቡ ያላግባብ በመሆኑ የሰበር አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው የተጠሪን የመልስ ይዘት በመንቀፍ የሰበር አቤቱታውን ደግሞ በማጠናከር የመልስ መልሣቸውን ሐምል 30 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ በስራቸው አጋጣሚ ወደ እጃቸው የገባውን የአመልካች ገንዘብ ማጉደላቸው ተረጋግጦ እያለ ለግል ጥቅማቸው ያዋለ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል አሣማኝ ማስረጃ አልቀረበም ተብል የአመልካች እርምጃ ህገ ወጥ ነው መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ የቲኬት ሽያጭ ሰራተኛ ሆነው ሲሰሩ የገንዘብ ጉድለት የተከሰተባቸው ስለመሆኑ ያመኑ መሆኑ ከመረጋገጡም በላይ በአመልካች በኩል የቀረቡት የሑሣብ ባለሙያም በኦዱት ሪፖርቱ የተገኘውን ውጤት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ገንዘቡ መጉደለን ያስረደ ስለመሆኑ የስር ፍ/ቤትም የተገነዘበው ጉዲይ ነው። ይህ ፍሬ ነገር ተረጋግጦ እያለ አሣማኝ ማስረጃ አልቀረበም የተባለው ተጠሪ ገንዘቡን ለግል ጥቅማቸው ያዋለ ስለመሆኑ በማስረዲት ረገድ ነው። ይሁን እንጂ ይህ የስር ፍ/ቤት ድምዲሜ በሕጉ ላይ ያልተመለከተውን መስፈርት መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር ሕጋዊ መሰረቱ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1(ተ) ስር በተመለከተው አኳኋን የአመልካች ድርጅት አለ በማለት የሚከራከረውንና በተጠሪም ያልተካደውን የህብረት ስምምነት አባሪ 1(ሀ)(3)”ን” ያላገናዘበ ነው በዚህ ድንጋጌ መሰረት የድርጅቱን ወይም በድርጅቱ ኃላፉነት የሚገኝ ንብረት ጥሬ ገንዘብ ወይም በድርጅቱ የስራ ግንኙነት ምክንያት ሰራተኛ እጅ ሉገቡ የሚችለ የደንበኞችን የሰራተኞችን ንብረት/ገንዘብ መስረቅ፣ መደበቅ፣ ለግል ጥቅም ማዋል ወይ እንዱወሰድ መተግበር ወይም እምነት ማጉደል ወይም የድርጅቱን ንብረት ወይም ቅጥር ግቢ ህገ ወጥ ለሆነ ተግባር መጠቀም ወይም ላላ ወገን እንዱጠቀምበት ማድረግ ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ማባረር የሚቻል ስለመሆኑ ተመልክቷል። ይህ ድንጋጌ የገንዘብ ጉድለት የተከሰተበት የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ ስለማዋለ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ በመስፈርትነት አያስቀምጥም። ይልቁንም የገንዘብ ጉድለት/እምነት ማጉደል/ ስለመከሰቱ መረጋገጥ ብቻ ሰራተኛውን ከስራው ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የሚያስችል መሆኑን በግልጽ ያስረዲል። የገንዘብ ጉድለት የተከሰተበት ሰራተኛ ገንዘቡን ለግል ጥቅም ያላዋለ መሆኑን የማስረዲት ሸክም ይኖርበታል እንጂ ይህንኑ የገንዘብ ጉድለት መኖሩን ያስረዲ አሰሪ እንዱያስረዲ አይጠበቅም። የገንዘብ ጉድለት የተከሰተበት መሆኑ የተረጋገጠበት ተከሣሽ ገንዘቡን ለግል ጥቅሙ ያዋለው ነው ተብል ህጋዊ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ የማስረጃ ሕግ መርሆዎች የሚያስገነዝቡት ነጥብ ነውና። በመሆኑም ተጠሪ የገንዘቡ ጉድለት መከሰቱን አምነው ገንዘቡን ለድርጅቱ መመለሣቸውን ባላስረደበት ሁኔታ የአመልካች ድርጅት ማስረጃ አሣማኝነት የለውም መባለ በጉዲዩ ላይ የቀረበው ማስረጃ የሚመዘንበትን መርህና በግራ ቀኙ መካከል ገዥነት ያለውን የህብረት ስምምነት ይዘት ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ የበታች ፍ/ቤቶች የተጠሪ ከስራ መሰናበት ህገ ወጥ ነው በማለት የደረሱበት ድምዲሜ ህጋዊነት የላለውን መነሻ ሐሣብ በመያዝ ሆኖ ስለተገኘ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል። በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከመጀ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.39196 ጥቅምት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 60895 ጥር 15 ቀን 2000 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው ባግባቡ ነው ብለናል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.