No summary available.
ጥቅምት 4 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሜታ አቦ ቢራ አክሲዮን ማህበር - አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- እነ ሳሙኤል ተፈራ (4 ሰዎች) - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረት የሚታይ ክርክር ሆኖ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። የአሁኑ አመልካች ተከሣሽ ተጠሪዎች ከሣሾች ነበሩ። ተጠሪዎች አመልካችን የከሰሱት በድርጅቱ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ የሕክምና ሰራተኞች መሆናቸውን ገልፀው ከጽሁፍ ሥራ ጋር በተያያዘ የተቋረጠባቸውን ክፍያ፣ በሽፍት ለሰሩት ሥራ ሉከፍል የሚገባውን ክፍያ እና የአልጋ ክፍያ እንዱከፍላቸው እንዱሁም የጽዲት ሰራተኛ እንዱመድብላቸው በመጠየቅ ነው።
አመልካችም ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ አመልካች ቢራ አምርቶ ለመሸጥ የተቋቋመ ድርጅት ነው፤
ተጠሪዎችም ስራቸው የመጀመሪያ የህክምና እርዲታ መስጠት ነው፤ ድርጅቱ ባወጣው የፈረቃ ድልደላ መሰረት እሁድ ስራ ላይ ለዋለ ሰራተኛ በቀጣዩ ቀን 24 ሰዓት እረፍት ይሰጠዋል፤ በሣምንት 48 ሰዓት ይሰራለ፤ ላልሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሉጠይቁ አይገባም፤ በሽፍት ሥራ ለሚሰራ ሰራተኛ የአልጋም ሆነ የእራት ክፍያ የሚፈጸምበት ህጋዊ ምክንያት የለም፤ የሕክምና መሣሪያቸውን የማጽዲት ሐላፉነት የተጠሪዎች ስለሆነ የጽዲት ሰራተኛ ልመድብላቸው አይገባም፤ በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ክርክሩን መርምሮ ተጠሪዎች በሣምንት 48 ሰዓት እንደሚሰሩ እና እሁድ ቀን በሥራ ላይ ከተገኙ በሚቀጥለው ቀን 24 ሰዓት የሚያርፈ መሆናቸውን በመረዲት ተጠሪዎች በሣምንት 48 ሰዓት ብቻ መስራታቸው እየታወቀ በሽፍት ሥራ እንሰራለን በማለት ብቻ ያቀረቡት የክፍያ ጥያቄ እና የጽዲት ሰራተኛ ይመደብልን ጥያቄ የሕግ ድጋፍ የለውም ውድቅ ነው ሲል ወስኗል።
ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ባለመስማማታቸው ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ተከራክረዋል።
የከፍተኛ ፍ/ቤቱም በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 61/1/ መሰረት የማንኛውም ሰራተኛ የስራ ሰዓት በቀን ከስምንት ወይም በሣምንት ከ48 ሰዓት አይበልጥም ስለሚል እና የተጠሪዎች ቅሬታ በሣምንት ከ48 ሰዓት በላይ ሰራን ሣይሆን በቀን 16 ሰዓት ሰራን ነው ስለዚህ እንደሰራተኛ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ መሥራት ግዳታ ባለመሆኑ አመልካች ተጠሪዎች በቀን 8 ሰዓት ብቻ እንዱሰሩ የሥራ ጊዜውን ያመቻች በማለት በማሻሻል ወስኗል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ላይ ነው።
አመልካች በጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አቤቱታ አቅርቧል። ይህ የሰበር ችልትም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርቦ ክርክሩን ሰምቷል።
ጉዲዩ በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በከፍተኛው ፍ/ቤት ለተጠሪዎች የሥራ ሰዓት ይመቻችላቸው በማለት የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጁ እና ከሕብረት ስምምነቱ አኳያ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረት ይህን ነጥብ ግራ ቀኙ ወገኖች ካሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እኛም የጉዲዩን አመጣጥ ስናየው ተጠሪዎች በአመልካች ድርጅት ሲሰሩ ድርጅቱ ባወጣው የሥራ ሽፍት መሰረት ተስማምተው ሲሰሩ የቆዩ እና በድልድለ መሰረት እሁድ ቀን ከሰሩ በሚቀጥለው 24፡00 ሰዓት እንደሚያርፈ ተገንዝበናል። አንድ ድርጅት እንደስራው ፀባይ በሕግ ከተደነገገው ማእቀፍ ሳይወጣ (ሳይጥስ) የሥራ ሰዓቱን ለማሻሻል የሚከለክለው ሕግ የለም። ተጠሪዎችም በዚሁ ተስማምተው በሣምንት ከ48 ሰዓት በማይበልጥ መልኩ በሽፍት ሲያገለግለ ቆይተው የላላቸውን (ያልሰሩበትን) የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚጠይቁበት የሕግ ድጋፍ የላቸውም። ላላው የጽዲት ሰራተኛ እንዱመደብላቸው የጠየቁትንም በሚመለከት ቀድሞውኑም ተጠሪዎች የህክምና ባለሙያ በመሆናቸው የራሳቸውን የሕክምና መሣሪያ ላላ ሰው ያጽዲልን ማለታቸው ተቀባይነት አይኖረውም። ስለዚህ የሰራተኛ ምደባው ውድቅ ነው።
ባጠቃላይ ተጠሪዎች በሕጉ አግባብ በአመልካች ድርጅት እንደሚሰሩ ግልጽ ሆኖ ሳለ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የድርጅቱን የስራ ፀባይ ግምት ውስጥ ሳያስገባ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 61(1) ለመባል ከፈለገው አላማ ጋር በቅጡ ሳያገናዝብ የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ በሚገድብ መልኩ በሣምንት ተጠሪዎች 48 ሰዓት መሥራታቸውን እየገለፀ ከአዋጁ መንፈስ ውጭ 8 ሰዓት ብቻ ለተጠሪ ይመቻችላቸው ብል የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ በማሻሻል መወሰኑ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11276 በቀን ሰኔ 4 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በከፍተኛው ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57620 በጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ ተሽሯል። ተጠሪዎች ምንም አይነት ክፍያ ሉጠይቁ አይገባም ብለናል።
ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ኪሳራ ይቻለ።
No topics extracted.