No summary available.
ጥቅምት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢት/ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ግርማ ማርቆስ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሰለፈች ደስታ ቀረቡ
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ ተጠሪ በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረቡት የሥራ ክርክር ክስ ነው።
ተጠሪ ለፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አመልካች ያለአግባብ የወሰደባቸው የዱሲፕሉን እርምጃ እንዱሻር፣ ተጠሪ ወደ ቀድሞ የስራ መደብ እንዱመልሳቸው እና የተቋረጠውን የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዱሰጣቸው ጠይቀዋል። አመልካች በሰጠው መልስ የዱሲፕሉን እርምጃ የተወሰደባቸው ጥፊተኛነታቸው ተረጋግጦ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል ብሎል። ፍ/ቤቱም አመልካች የወሰደውን እርምጃ አሻሽል ተጠሪ በ4 ቀን ደመወዝ እንዱቀጡና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዱመለሱ፤ በደመወዝ ላይ የተደረገው ጭማሪም ተስተካክል እንዱሰጣቸው ወስኗል። አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የአመልካችን ይግባኝ ሣይቀበል ቀርቷል።
የአሁኑ ሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ በህብረት ስምምነቱ የጥፊት አይነቶችና የቅጣት ደረጃዎች ተዘርዝረዋል። አንድ ሰራተኛ ጥፊት ሲፈጽም እርምጃ የሚወሰድበት ስለጥፊት አይነቶች እና ስለ ቅጣት በሚያስረዲው ሰንጠረዥ መሰረት ሲሆን የጥፊቱን ክብደት ከሚያሳዩት ደረጃዎች ለጥፊቱ ተመጣጣኝ የሆነውን ቅጣት መቅጣት ይቻላል። የጥፊት አይነቶች እና የቅጣት ደረጃዎች የተቀመጡት የተፈፀመውን ጥፊት ክብደት ለመመዘን እንዱያመች እንጂ የጥፊት ቅደም ተከተልን ለመወሰን አይደለም የሚል ነው።
ተጠሪም ቀርበው በሰጡት መልስ ስህተቱ የተፈጠረው በእርሣቸው ስህተት ባለመሆኑና ከድርጅቱ የውስጥ አሰራርና አመራር ጉድለት በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት እንደላለው ተከራክረዋል።
ይህ ችልትም መዝገቡን መርምሯል። የሥር ፍ/ቤት በህ/ስምምነት ውስጥ ከተዘረዘሩት የቅጣት አይነቶች ቅደም ተከተል ሣይጠበቅ በአንድ ጥፊት በ4ኛ ደረጃ የተቀመጠውን ቅጣት እንዱቀጡ መወሰኑ ሕጋዊ አይደለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በበኩለ የቅጣት ደረጃው ቅደም ተከተልን የሚያሣይ ሣይሆን በተፈፀመው ጥፊት ክብደት ተገቢውን ቅጣት ለመወሰን የተቀመጡ ናቸው በማለት ተከራክሯል።
ከመዝገቡ ለመረዲት እንደተቻለው የሥር ፍ/ቤት የአመልካችን ጥፊተኛነት ተቀብል ወደ ቅጣት ውሣኔው ትክክለኛነት አምርቷል። አመልካች ጥፊተኛ ሆነው ከተገኙ ሉቀጡ የሚገባው የህ/ስምምነቱ ከዘረዘረው ቅጣቶች በቅደም ተከተል ነው ወይስ ህ/ስምምነቱ እንደጥፊቱ ክብደት ቅደም ተከተል ሣይጠበቅ ቅጣቱ ይጣል የሚለው ነ1ው፤ አከራካሪ የሆነው። ተጠሪ በዚህ ፍ/ቤትም በሰጡት መልስ ምንም የፈፀሙት ጥፊት የላለ ከመሆኑ ውጪ ቅጣቱ በምን ሁኔታ መፈፀም እንዲለበት ያቀረቡት ክርክር የለም። የሥር ፍ/ቤቶች የተጠሪን ጥፊተኛነት አረጋግጠው በሰጡት ውሣኔ ላይም የቀረበ አቤቱታ ባለመኖሩ ተጠሪ ጥፊተኛ ናቸው አይደለም ወደሚለው ነጥብ መግባት አስፈላጊ አይሆንም። አንድ ሰራተኛ ጥፊተኛ ሆኖ ከተገኘ ቅጣቱ እንዳት ነው ሉወሰን የሚገባው የሚለውን ስንመለከት የአመልካች መ/ቤት ህብረት ስምምነት እንደሚያሣየው ለተለያዩ የጥፊት አይነቶች የተለያዩ ቅጣቶች ተመልክተዋል። ተጠሪ ጥፊተኛ ሆነው የተገኙበት የተመደቡበትን ስራ በቸልተኛነት አለመስራት ጥፊት ለምሣላ በ5 የተለያዩ የቅጣት ደረጃዎች ሉያስቀጣ እንደሚችል ተመልክቷል። እንዱሁም በመ/ቤቱ የሕብረት ስምምነት አንቀጽ 22(12)(ሀ) ሥር በአንድ ሰራተኛ ላይ የዱሲፒሉን እርምጃ ሲወሰድ የሚወሰነው ቅጣት ስለጥፊትና ስለቅጣት አይነት በሚያስረዲው ሰንጠረዥ መሰረት ሆኖ የጥፊቱን ክብደት ከሚያሣዩት ደረጃዎች ለጥፊቱ ተመጣጣኝ በሆነ የቅጣት ደረጃ ሉቀጣ እንደሚችል ተመልክቷል። ስለጥፊትና ስለቅጣት አይነት በሚያሣየው ሰንጠረዥ ግርጌም የቅጣት ደረጃው የሚያመለክተው እንደጥፊቱ ክብደትና ቀላልነት የጥፊቱን ደረጃና ለደረጃውም የሚወሰነውን ቅጣት እንጂ የጥፊት ቅደም ተከተልን እንዲልሆነ በማሳሰቢያነት ተቀምጧል። በመሆኑም ከህ/ስምምነቱ አንድ ሰራተኛ ጥፊተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቅጣቱ የሚጣልበት በሰንጠረዡ ላይ በሰፈረው ደረጃ ቅደም ተከተል ሣይሆን የጥፊቱ ክብደት ታይቶ ተመጣጣኝ ነው ተብል በሚገመተው የቅጣት ደረጃ እንደሆነ ተገንዝበናል።
በተያዘው ጉዲይም አመልካች ተጠሪ በቸልተኛነት ሥራ ባለመስራት በመ/ቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዲት በማድረሣቸው የጥፊታቸው ክብደት በደረጃ አራት ላይ የተመለከተውን የቅጣት አይነት ያስቀጣቸዋል በማለት በዚሁ መሰረት እርምጃ ወስዶል። የጥፊቱን ክብደት በመመዘን ይመጥናል የሚለውን ቅጣት የመወሰን ተግባር ደግሞ ለአሰሪው ሉተው የሚገባ አስተዲደራዊ ስራ መሆኑን እናምናለን። ሰለሆነም አመልካች ተጠሪ ጥፊተኛ ለሆነበት ድርጊት የተመለከተውን ቅጣት መወሰኑ ህገ ወጥ ነው ለማለት አይቻልም። የስር ፍ/ቤቶችም የህብረት ስምምነቱን በአግባቡ ሣያጤኑ ቅጣቱ ሉወሰን የሚገባው በቅደም ተከተል ነው በማለት የሰጡት ውሣኔም ከላይ በሰፈሩት ምክንያቶች ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 21035 በሐምል 2 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 58454 በየካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽረዋል።
አመልካች በተጠሪ ላይ የወሰደው እርምጃ የህ/ስምምነቱን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የተጠሪ ክስ ተቀባይነት የለውም ።
ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻለ መዝገቡ ተዘግቷል። ለመ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.