No summary available.
ጥቅምት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብድልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ሥላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግልት ድርጅት ነገረፈጅ ፊሲካ በለጠ - ቀረበ ተጠሪ፡- ተስፊዬ መኯንን - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ የሚታይ የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በተጀመረበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ሲሆን፣ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ከሐምል 1 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ለድርጅቱ ሰራተኞች በሙለ የአንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ ተደርጎአል። እኔም የድርጅቱ ሰራተኛ በመሆኔ ጭማሪው ሉሰጠኝ ሲገባ አለአግባብ ተከልክያለሁ። ስለዚህም ጭማሪ እንዱሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሽ ሦስት አራተኛውን ጊዜ በስራ ላይ ስላልነበረ ጭማሪውን ሉያገኝ አይችልም በማለት ተከራክሮአል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር የመረመረ ሲሆን፣ በመጨረሻም የአመልካችን ክርክር ባለመቀበል ተጠሪ በጠየቀው መሰረት የደመወዝ ጭማሪው ይሰጠው በማለት ወስኖአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በተመሣሣይ ሁኔታ ወስኖአል /የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶአል/። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በድርጅቱ ፀንቶ ያለው በሕብረት ስምምነት ጭማሪው የማይደረግበትን ምክንያት አስቀምጦአል እየተባለ አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ሕጋዊ የሚሆንበት አግባብ ምንድነው? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ነጥቡን ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሁለቱ ወገኖች ክርክር እና በሥር ፍ/ቤቶች ከተሰጡት ውሣኔዎች ይዘት መገንዘብ እንዱቻል ነው ተጠሪ በተባለው የበጀት ዓመት ውስጥ የዓመቱን 3/4 /ሦስት አራተኛ/ ጊዜ በስራ ላይ አልነበረም። በወቅቱ ፀንቶ በነበረው /ባለው/ የህብረት ስምምነት አንቀጽ 29/5/ እንደተመለከተው ይህን ያህል ጊዜ በስራው ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ ጭማሪው እንደማይሰጠው ደግሞ አላከራከረም። የስር ፍ/ቤቶች ይህንኑ በሚገባ ስለመገንዘባቸው በውሣኔዎቻቸው ላይ የገለፁ ሲሆን፣ ጭማሪው መሰጠት አለበት በማለት የወሰኑት ግን በሕብረት ስምምነቱ የላለን ምክንያት መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተገንዝበናል። ይህ ተጠሪ አመልካች በወሰደው የስራ ውል ማቋረጥ እርምጃ ምክንያት በክርክር ስለመቆየቱ የሚገልጽ ነው።
በእርግጥም አመልካች የስራ ውለን አቋርጦ ስለነበር ተጠሪ ለፍ/ቤት ባቀረበው ክስ መሰረት ክርክር ከተደረገ በኋላ ወደስራው እንዱመለስ ተወስኖለታል። የሥር ፍ/ቤቶች ይህንኑ ሁኔታ ለእርከን ጭማሪው እንደበቂ ምክንያት አድርገው የወሰደት ተጠሪ በስራው ላይ ሉገኝ ያልቻለው አመልካች በወሰደው ሕገ ወጥ የስራ ውል ማቋረጥ ምክንያት ነው። ይህንኑም በፍ/ቤት ተረጋግጦ ተወስኖአል በማለት ነው። በበኩላችን እንደምናየው የእርከን ጭማሪ አሰጣጥን በተመለከተ የተደነገገው የሕብረት ስምምነቱ አንቀጽ 29/5/ በግልጽ የሚያመለክተው በበጀት ዓመቱ ውስጥ 3/4ኛው ጊዜ በስራ ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ የእርከን ጭማሪ የማይሰጠው እንደሆነ ነው። ድንጋጌው ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ ትርጉም የሚያስፈልገው አይሆንም። አመልካች የስራ ውለን ያቋረጠው ሕገወጥ በሆነ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም?
በሚል ጭብጥ ላይ ተመስርቶ ተሰጥቶ የነበረው ውሣኔም ለተያዘው ክርክር አወሳሰን ተገቢነት ያለው አይደለም።
በመሆኑም ተጠሪ የጠየቀውን የእርከን ጭማሪ ሉያገኝ ይገባል ብል ለመወሰን የሚያስችል የሕግ ምክንያት የለም። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
አቤቱታ የቀረበበት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 34178 በታህሣሥ 14 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተሰጥቶ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 63ዐ56 የካቲት 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
ተጠሪ በክሱ የጠየቀውን የአንድ እርከን የደመወዝ ጭማሪ እንዱያገኝ የሚደረግበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ወስነናል።
No topics extracted.
ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ። መዝገቡ ይመለስ።