No summary available.
ጥቅምት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሰንሻይን ኮንስትራክሽን - አልቀረበም መልስ ሰጭ፡- 1. አቶ ፍቃደ ገቢሣ - አልቀረቡም 2. አቶ ታዬ ዋሚ - ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች የታች ተከሣሽ ሲሆን የአሁን መ/ሰጭ የታች ከሣሾች ነበሩ። መ/ሰጭ በታች ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በመቀጠር በአናፂነት ሙያ ሲያገለግለ ቆይተው ላላ ሣይት (ቦታ) ሥራ እያለው ሥራው አልቋል በማለት ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሥራ ውላችንን አቋርጦብናል ስለዚህ የአገልግልት ክፍያ የማስጠንቀቂያ የሁለት ወር የዘገየበት የስንብት የስድስት (6) ወር ክፍያ እና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዱወሰንልን በማለት ጠይቋል።
ተከሣሽ (የአሁን አመልካች) ጥቅምት 27 ቀን 1999 ዓ.ም በጽሁፍ ባቀረበው መልስ ከሣሽ (መልስ ሰጭ) ደመወዝ የሚከፈላቸው በቀን ታስቦ እንደሆነና ከአመልካች ድርጅት ጋር የፈፀሙት ጊዜያዊነት ያለው የሥራ ውል የተመደቡበት የአናፂነት ሥራ በሚኖርበት ጊዜ ብቻ የሚከፈላቸው መሆኑን ገልጾ የስራ ውለ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24(1) መሰረት በሕጋዊ መንገድ እንደተቋረጠ በመግለጽ ተከራክሮ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የመልስ ሰጭ የሥራ ውል መቋረጡ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ጭብጥ ይዞ መዝገቡን መርምሮታል። በዚህም መሰረት በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 10(1) (ሰ) መሰረት ሥራው ምንም እንኳ የአሰሪው ቋሚ ሥራ ቢሆንም አልፍ አልፍ የአናፂነት ሥራው ሲኖር የሚሰራ መሆኑን ተረድቻለሁ በማለት አመልካች መልስ ሰጭን ማሰናበቱ በአዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 10(1)(ሀ) መሰረት በአግባቡ ነው ሲል ወስኗል።
መልስ ሰጭም በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የታች ፍ/ቤት ማስረጃ ሣያጣራ ወሰነብን በማለት ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቤቱታቸውን አቅርቧል።
የከፍተኛው ፍ/ቤትም በቀረበለት አቤቱታ መሰረት የአሁን አመልካች መልስ እንዱሰጥበት ካደረገ በኋላ ይግባኝ ባይ (የአሁን መልስ ሰጭ) የተቀጠሩት ለየትኛው ፕሮጀክት ነው? ፕሮጀክት በመጠናቀቁ ነው ወይስ አይደለም የተሰናበቱት? የሚለውን ጭብጥ መሥርቶ ከመረመረ በኋላ በቅጥር ውል ላይ “ለምን ስራ፣ እስከመቼ” የሚለውን የሚያስረዲ ባለመሆኑ የአሁን መልስ ሰጭ (የታች ከሳሽ) የተቀጠሩት በአዋጁ አንቀጽ (10) ስር በተደነገጉት መሰረት ነው ተብል የሚወሰድበት ምክንያት የለም በማለት በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ በመሻር ስንብቱ ያለ አግባብ ነው በማለት ለአሁን መልስ ሰጭ የ8 ወር ውዝፍ ደሞዝ እንዱከፈላቸውና ወደ ምድብ ስራቸው እንዱመለሱ ሲል ወስኗል።
የአሁን የሰበር አቤቱታም የቀረበው የከፍተኛው ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤትን ውሳኔ በመሻሩ ቅር ተሰኝቶ ሲሆን የጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም የጉዲዩን አመጣጥ ካጠና በኋላ የሥር ፍ/ቤት ማስረጃ መስማት እየቻለ መልስ ሰጭ የተቀጠረበት ሥራ መጠናቀቁ እየተገለፀ ወደ ሥራ ይመለሱ መባለን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩን አስቀርቦታል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ጭብጦች በመያዝ ግራ ቀኙ በጉዲዩ መልስ እና የመልስ መልስ እንዱያቀርቡ በማድረግ አከራክሯል።
በታች የተሰጡትን ውሳኔዎች ከህጉ በማገናዘብ እንዲየነው መልስ ሰጭ “በፉንጫ ለምለም” ፕሮጀክት ውስጥ በአናፂነት ሥራ ሲሰሩ እንደቆዩ በመግለጽ ሥራ በልላ ሣይት (ቦታ) እያለ ሥራ አልቋል በመባል መሰናበታቸው ከሕግ ውጭ ነው ሲለ ባቀረቡት ክስ መሰረት ፍ/ቤቱ ጉዲዩን አከራክሮ ስንብቱ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 10(1) (ሀ) መሰረት ሕጋዊ ነው ሲል ወስኗል። ይግባኝ የቀረበለትም የከፍተኛው ፍ/ቤት የመልስ ሰጭ የቅጥር ሁኔታ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 10(1)(ሰ) ከተዘረዘሩት ውጭ ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ አይደለም በማለት የተጠየቀውን ክፍያ እንዱከፍላቸውና ወደ ሥራቸው እንዱመለሱ በመወሰን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት የታች ውሳኔን ሽሮታል።
በመሰረቱ ከላይ ከተነሱት ክርክሮች መገንዘብ እንደተቻለው መልስ ሰጭ በአመልካች ድርጅት ለምን ስራ እንደተቀጠሩ በሚለው ነጥብ ቀድሞውንም አልተከራከሩም (አልተካካደም) የአናፂነት ሥራ ደግሞ በግንባታ ሥራ ውስጥ ወቅቱን ጠብቆ የሚሰራ እና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የተጀመረው ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ግልጽ ሆኖ ሳለ ለምን ስራ እና እስከመቼ ይሰራለ? የሚለውን ነጥብ ማየቱ በተያዘው ጉዲይ አግባብነት የለውም። መልስ ሰጭ ቢሆኑም በክሳቸው ውስጥ ድርጅቱ ላላ ቦታ(ሣይት) እንዲለው በመግለጽ ሥራው አላለቀም በማለት ይከራከራለ።
በመሰረቱ በልላ ቦታ ተጨማሪ (ተመሣሣይ) ሥራ መኖሩ የተባለውን የፕሮጀክት ሥራ አላለቀም የሚያስብል አይሆንም። ድርጅቱም የግድ ከአንድ ፕሮጀክት ወደ ላላው ፕሮጀክት ሰራተኞችን ይዞ እንዱዞር የሚያስገድደው የሕግ ነጥብ አይኖርም፤ ምክንያቱም ድርጅቱ የራሱ የሆነ የአሰራር ስርአት ይኖረዋል ተብል ስለሚገመት። ይህ በእንዱህ እንዲለ የሥራውን መጠናቀቅና መኖር በድጋሚ በማስረጃ ማጣራት እየተቻለ ይህ ሣይደረግ በከፍተኛው ፍ/ቤት ስንብቱ ያለ አግባብ ነው መባለና መልስ ሰጭ የጠየቁት ክፍያ ተከፍልአቸው ወደ ስራቸው ይመለሱ ተብል መወሰኑ የአዋጁን አንቀጽ 10(1) (ሰ)”ን” ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 23063 በሰኔ 6 ቀን 1999 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ ፀንቷል ይፃፍ።
በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57553 በ
No topics extracted.