No summary available.
ጥቅምት 13 ቀን 2ዐዐ1 ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ፀጋዬ አስማማው ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ኤፍሬም ንዋየማሪያም - ጠበቃ ቴዎድሮስ ተስፊዬ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሚያዝያ 24 ቀን 1999 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ተጠሪ ከየካቲት 29 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ በአመልካች ድርጅት ተቀጣሪ ሆነው ሲሰሩ ቆይተው ስራውን በገዛ ፈቃዲቸው ሲለቁ þሮቪደንት ፈንድን ጨምሮ የሚገባቸውን ላልች ጥቅማ ጥቅሞችን አመልካች የከፈላቸው ቢሆንም የስራ ስንብት ክፍያ ያልከፈላቸው መሆኑን ገልፀው የስራ ስንብት ክፍያ ብር 14,994.18/አስራ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ብር ከአስራ ስምንት ሣንቲም/ እና ይኸው ክፍያ ለዘገየበት ደግሞ የሦስት ወር ደመወዝ ብር 9,879.ዐዐ /ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር/ በድምሩ ብር 24,873.18 / ሃያ አራት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ሦስት ብር ከአስራ ስምንት ሣንቲም/ አመልካቹ እንዱከፍል ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው።
የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ለተጠሪ የሚገባውን ጥቅማ ጥቅም መክፈለን፣ የስራ ስንብት ክፍያ ደግሞ þሮቪደንት ፈንድ ወይም ጡረታ ላለው ሰራተኛ እንደማይከፈለው በአዋጅ ቁጥር 494/98 መደንገጉንና በዚህም ምክንያት ክፍያ ሉጠየቅ እንደማይገባ፣ የታመነ ክፍያም በወቅቱ የከፈለ በመሆኑ ክፍያ ለዘገየበት ተብል የሚቀጣበት የሕግ ምክንያት የላለ መሆኑን በመግለጽ ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ተጠሪ የþሮቪደንት ፈንድ የተከፈላቸው መሆኑን ማመናቸውን በመግለጽና አዋጅ ቁጥር 494/98 ደግሞ አንድ ሰው ሁለት ጊዜ እንዱከፈለው የሚፈቀድ አለመሆኑን በምክንያትነት በመውሰድ ተጠሪ የስንብት ክፍያ ጥያቄ አይገባቸውም በማለት ወስኗል። የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ባለመስማማትም ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍ/ቤቱ ተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ጥር 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት ያለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝሯል። ይዘቱም በአጭሩ የþሮቪደንት ፈንድ የተከፈለው ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈለው የማይገባ መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 494/1998 ተደንግጎ እያለ ከአዋጁ መንፈስ ውጪ መተርጎሙ ሉታረም ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው።
ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመመርመር ተጠሪ የþሮቪደንት ፈንድ የተከፈላቸው መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የስራ ስንብት ክፍያ እንዱከፈላቸው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለማጣራት ተጠሪን ያስቀርባል ብል ተጠሪ ሚያዝያ ዐ2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ መልሣቸውን አቅርበዋል። የመልሣቸው ይዘትም በአጭሩ፡- የአመልካች የሰበር አቤቱታ የክርክር ነጥቦች ከሕጉ ዓላማና መንፈስ ውጪ መሆናቸውን በጉዲዩ ላይ የተሰጠው የፍ/ቤቱ ትርጓሜ ግን ተገቢነት ያለው መሆኑን በመዘርዘር መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አመልካች ግንቦት ዐ6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሰበር አቤቱታው የቀረበበትን ውሣኔ፣ የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር አግባብነት ካለው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የþሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው? ወይስ የለውም?
የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
በክርክሩ ሂደት ተጠሪ በገዛ ፈቃዲቸው ስራውን መልቀቃቸውንና የþሮቪደንት ፈንድም በወቅቱ ተከፍሎቸው የተሰናበቱ መሆኑን በማመን የሚከራከሩ መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ ቢረጋገጥም የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት በሕግ የተጠበቀ መሆኑን ተጠሪ አጥብቀው የሚከራከሩ ሲሆን አመልካች የተጠሪ ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል።
እንግዱህ የግራ ቀኙን ክርክር እልባት ለመስጠት አግባብነት ያለውን የሕግ ድንጋጌ ይዘት እና መንፈስ መመልከትን የግድ ይሎል። በዚህም መሰረት አመልካች ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ /ማሻሸያ/ አዋጅ ቁጥር 494/1998 ዓ.ም ሲሆን ይህ አዋጅ ከአሻሻላቸው የአዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎች አንደ ስለስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አንደ ነው። የማሻሻያ አዋጁ በዚህ ረገድ ያስቀመጠው ድንጋጌ ሙለ ይዘቱ በሚከተለው መልኩ የተቀመጠው ነው። ይኸውም "የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ ሰራተኛ የþሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም የጡረታ መብት የላለው ሲሆንና በጡረታ ሕግ የተቀመጠው መደበኛ የጡረታ ዔድሜ ላይ ደርሶ ከስራ ሲገለል ከአሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው።" /አንቀጽ 2/ሰ/ ይመለከቷል/ የሚል ሲሆን የድንጋጌው የእንግሉዝኛ ትርጉሙም፡- "A worker who had completed his probation shall have the right to get severance pay from the employer where he has no entitlement to a provident fund or pension right and his contact of employment is terminated up on attainment of retirement age stipulated in the pension law" በሚል ይደነግጋል።
ከድንጋጌው የአማርኛና የእንግሉዝኛ ትርጉም በቀላለ መገንዘብ የሚቻለው የþሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያለው ሰራተኛ የስራ ውለ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ ከአሰሪው የማግኘት መብት የላለው መሆኑን ነው። በልላ አገላለጽ የþሮቪደንት ፈንድ እና የስራ ስንብት ክፍያዎች በተመሣሣይ ጊዜ ከአንድ ምንጭ የማግኘት መብት ላይ በሕጉ ክልከላ ተደርጓል።
እንደሚታወቀው የስራ ስንብት ክፍያ ዓይነተኛ ዓላማው በስራ ላይ የቆየ ሰራተኛ አዱስ ስራ ፍለጋ ላይ እያለ ሉደርስበት የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ችግር በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ ነው። የþሮቪደንት ፈንድ ዓላማም ከዚሁ የተለየ አይደለም። አላማቸው አንድ ዓይነት ከሆነ ሁለቱም የክፍያ ዓይነቶች በተመሣሣይ ጊዜ ከአንድ ምንጭ እንዱከፈለ ማድረግ አሰሪን ሁለት ጊዜ እንደመቅጣት ከሚቆጠር በስተቀር ፍትሐዊነት አይኖረውም። በመሆኑም ሕግ አውጪው የþሮቪንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆነ ሰራተኛ የስራ ውለ ሲቋረጥ ከአሰሪው የስራ ስንብት ክፍያ የመጠየቅ መብቱን የነፈገው ከላይ የተገለፀውን አሰሪን ሁለት ጊዜ እንዲይከፍል ለመጠበቅ ነው ተብል ከሚታሰብ ውጪ ላላ ምክንያት ሉኖር አይችልም።
ሲጠቃለልም ተጠሪ የþሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ ሆነው ክፍያም የተፈፀመላቸው መሆኑን እያመኑ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ /ማሻሻያ/ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/ሰ/ ሥር በተመለከተው አኳኋን በሕጉ የከለከለትን የመብት ጥያቄ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተቀብል ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል።
በዚህም ምክንያት የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 57691 ታኀሣሥ 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ ሉከፈላቸው ይገባል ሲል የሰጠው የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር 494/1998 ዓ.ም አንቀጽ 2/ሰ/ ስር በተደነገገው መሰረት የþሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ያለው ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የለውም ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቄራ ምድብ 2ኛ የስራ ክርክር ችልት በመ/ቁ. 26971 ሰኔ 2ዐ ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻቻለ ብለናል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.