No summary available.
ሐምል ዐ8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ሰላም የሕዝብ ማመላለሻ አ/ማ - ጠ/ረዲይ ባራኪ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ኒያላ ኢንሹራንስ አ/ማ - አልቀረቡም።
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው ተጠሪ በመልካችና በልላ ግለሰብ ላይ በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የመሰረተው ክስ ነው። በክሱም ተጠሪ የመድን ሽፊን የሰጠውን መኪና ንብረትነቱ የአመልካች የሆነ መኪና በሥር ሁለተኛ ተከሣሽ ሲሽከረከር ገጭቶ ጉዲት በማድረሱ ጉዲቱን ለማስጠገን ያወጣውን ወጪ ተከሣሾች እንዱተኩለት ጠይቋል።
የአሁኑ አመልካች ጉዲት አደረሰ የተባለውን መኪና በጨረታ አቶ ተክለ አስፊው ለተባለ ግለሰብ ስለተሰጠ ተጠያቂነት የለብኝም መኪናውን የገዙት ግለሰብ በክሱ ውስጥ እንዱገቡ ተደርጎ እኔ ልሰናበት በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍ/ቤት ግን አመልካች መኪናው ለላላ ግለሰብ ሸጥኩ ይበለ እንጂ የባለቤትነት ስሙ በገዢው ያልተዛወረና መኪናው አሁንም በአመልካች ስም ስለሚታወቅ ለጉዲቱ ኃላፉነት አለበት በማለት በክሱ የተጠየቀውን ገንዘብ እንዱከፈል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ የሰበር ችልትም መኪናውን ገዝተዋል የተባለት ግለሰብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 መሰረት ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ተጠይቆ የሥር ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ሣይቀበል ማለፈ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ግራ ቀኙም ቀርበው የቃል ክርክሩ ተሰምቷል። በመሆኑም ይህ ችልት መኪናውን ገዙ የተባለት ግለሰብ ወደ ክርክሩ ሉገቡ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ ከሚመለከተው ሕግ አኳያ መርምሯል።
በተጠሪ መኪና ላይ ጉዲት አደረሰ የተባለው መኪና የአመልካች የነበረ ሲሆን አመልካች መኪናዋን ለላላ 3ኛ ወገን ቢሸጡም የባለቤትነት ስሙ በገዢው ስም አልተዛወረም። የመኪና ባለቤትነት የሚተላለፈው እንደላለ ማንኛውም ተንቀሣቃሽ ንብረት ንብረቱን ገዝቶ ወይም በልላ መንገድ አግኝቶ በእጅ በማድረግ አይደለም። መኪና ላይ ተንቀሣቃሽ ንብረት በመሆኑ ባለቤትነት የሚተላለፍበት መንገድ በልዩ በሕግ ተደንግጓል። በዚህም መሰረት የንብረቱ ባለሃብትነት የሚታለፈው የባለቤትንት ስሙ በገዢው ስም ሲዛወር ነው። ይህን በተመለከተ የሰበር ችልት በመ/ቁ ትርጉም ሰጥቶበታል። በተያዘው ጉዲይም አመልካች መኪናውን ለላላ ሰው ቢሸጡም የመኪናው የባለቤትነት ስም በአመልካቹ በመሆኑ በባላቤትነት የሚታወቀው አመልካች ነው። የመኪና ባለቤት ደግሞ መኪናው በደረሰው ጉዲት ያለጥፊት ኃላፉ መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ81/1/ ተመልክቷል።
በልላ በኩል ግን አመልካች መኪናውን ለ3ኛ ወገን ሸጦ ገዢው መኪናውን መረከቡንና ጉዲቱ በደረሰ ጊዜም መኪናዋ በገዢው ይዞታ ሥር ነበር በማለት ተከራክሯል። የመኪናው ባለቤት ባይሆንም እንኳን መኪናውን ለግል ጥቅሙ ሲገለገልበትና ሲጠቀምበት የነበው ሰው መኪናው በይዞታው ሥር በነበረበት ጊዜ ለደረሰው ጉዲት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2ዐ82/1/ መሰረት ኃላፉ ነው። በአጠቃላይ የመኪናው ባለቤትም ሆነ ጉዲቱ በደረሰ ጊዜ መኪናውን ሲጠቀምበት የነበረ ሰው ሁለቱም ኃላፉነት አለባቸው። የመኪናው ባለቤትም ያለው መብት ተጎጂውን ከካሰ በኋላ በአደጋው ጊዜ መኪናውን ይዞ ሲገለገልበት የነበረውን ሰው የካሰውን የገንዘብ መጠን እንዱተካለት መጠየቅ ነው /የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2983/1/ ስለሆነም አመልካች መኪናውን ሸጦ ለላላ ሰው ያስረከበ ቢሆንም የባለቤትነት ስሙ በገዢው ስም ባለመዛወሩ በሕግ የመኪናው ባለቤት ሆኖ የሚወሰደው እሱ ነው። ባለቤት በመሆኑም ለጉዲቱ ኃላፉ ነው።
የአመልካች ኃላፉነት እንዲለ ቢሆንም ግን የመጨረሻው የመካስ ኃላፉነት የሚወድቀው መኪናውን ይዞ ሲገለገልበት የነበረው ሰው ላይ ነው። ከፍ ሲል እንደገለጽነው የመኪናው ባለቤት ተጎጂውን ከካሰ በኋላ ይህንን ካሣ የሚተካው መኪናውን ሲጠቀምበት የነበረው ሰው ነው። ተከሣሽ የሆነ ሰውም በክሱ ውስጥ የላለ ሦስተኛ ወገን ከክሱ ጋር ድርሻ ካሣውን መክፈል አለበት በሚል ይኸው ሰው ወደ ክሱ እንዱገባለት መጠየቅ የሚችል መሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 ተመልክቷል። በእርግጥ በክሱ እንዱገባ የሚጠየቀው ሰው ካሣውን የሚከፍልበት ምክንያትና የድርሻውም ልክ መገለጽ እንዲለበት ይኸው የሥነ-ሥርዓት ሕግ ያስገድዲል። እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟለ ግን ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ የሚያደርግበት ምክንያት አይኖርም። ሦስተኛ ወገኖች ወደ ክሱ እንዱገቡ የሚዲረጉት በአንድ ጉዲይ ሉነሱ የሚችለትን የመብት ጥያቄዎች በሙለ በአንድ ክስ መወሰን እንዱችልና በተመሣሣይ ጉዲይ ሉቀርቡ የሚችለ የተነጣጠለ ክሶችን ለማስቀረት ነው። በመሆኑም ተከሣሹ ጣልቃ እንዱገባ በሚጠይቀው ሰው ላይ የሚያነሣውን ጥያቄ ላላ የተነጠለ ክስ ማቅረብ ሣያስፈልገው በተጀመረው ክስ ሉወሰን ይችላል። ስለሆነም ተከሣሹ ለክሱ ኃላፉነት ካለበት ጣልቃ ገቡ በቀጥታ ለከሣሽ ሉከፈል ሉወሰን ይችላል ከዚህም በተጨማሪ ጣልቃ ገቡ በክሱ ውስጥ ከገባ በኋላ በክሱ ውስጥ እንዲለ የሚቆጠር በመሆኑ /የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 43/2// ለቀረበው ክስ ያለውን መከላከያ የማቅረብ እድል ይኖረዋል።
በአጠቃላይ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 43 አላማ ከአንድ ግንኙነት የሚመነጩ ጥያቄዎች በሙለ ተጠቃለው በአንድ ክስ እንዱያልቁ እና የተነጣጠለ ክስ ማስቀረት በመሆኑ ፍ/ቤቶች በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት መስፈርቶች እስከተሟለ ድረስ ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ የሚችለበት የሕግ መሰረት የለም።
በተያዘው ጉዲይ ጉዲት ያደረሰው መኪና ጉዲቱን ባደረሰበት ጊዜ ጣልቃ እንዱገቡ በተጠየቁት ግለሰብ ይዞታ ሥር በመሆኑ ግለሰቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ82/1/ መሰረት ኃላፉ ሉሆኑ የሚችለ ስለሆነና የደረሰውን ጉዲት በሙለም የመካስ ግዳታ ሉወድቅባቸው የሚችል በመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2ዐ83/1/ ሥር መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 መሰረት ወደ ክርክሩ ጣልቃ ሉገቡ የሚገባቸው ናቸው። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ጣልቃ እንዱገቡ የተጠየቁት ግለሰብ ያለባቸውን ኃላፉነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 43 መሰረት ጣልቃ ሣያስገባ መወሰኑ የሥነ ሥርዓቱን ድንጋጌ ያልተከተለና የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 56353 መጋቢት 5/2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል።
አደጋው በደረሰ ጊዜ አደጋውን ያደረሰው መኪና ሲጠቀሙበት የነበሩት ግለሰብ በክሱ ውስጥ ጣልቃ ገብተው ተከራክረው ተገቢው ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1/ መሰረት ጉዲዩን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት መልሰናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.