No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ቤዛ አማካሪ መሀንዱሶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ ግርማ ኃ/መስቀል ቀረቡ ተጠሪ፡- ሚስተር ሸሬሃሪ ብራማቫሪ ጏፓል - ጠበቃ አቶ ሀይልዬ ሣህለ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 3 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከተ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በከሳሽነት ቀርቦ ተከሳሽ(የአሁን አመልካች) አላግባብ ከሥራ ያሰናበተኝ ስለሆነ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት መብቴ እንዱጠበቅልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች በበኩለ በተከሳሽነት ቀርቦ ከሳሽ (ተጠሪ) የድርጅቱ ክፍለሀጉራዊ ሥራ አስኪያጅ በመሆናቸው የሥራ መሪ ናቸው፤ ጉዲያቸው በአሰሪና ሰራተኛ ችልት መታየት የለበትም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት ክሱን ዘግቶታል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች ተጠሪ የሥራ መሪ ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም። ስለዚህ ተጠሪ የያዘውን የሥራ መደብ ስያሜ በመመልከት ብቻ የሥራ መሪ ነው ማለት ስለማይቻ ስልጣን የለኝም ያልከው አላግባብ ነው። በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት አከራክረህ ወሰን በማለት ጉዲዩን ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መልሶለታል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በመሰረቱ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማከራከር ስልጣን የለኝም በማለት ያዘጋው በአግባቡ ነው። ከተጠሪ ጋር የተደረገው የሥራ ውል እና ከኢትዮጵያ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስትር በአመልካች ተጠያቂነት ለተጠሪ የተሰጣቸው የሥራ ፈቃድ ማስረጃ ተጠሪ ሪጅናል ማኔጀር እንደሆኑ የሚያረጋግጡ ናቸው። ይህንን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ በፍታብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 መሰረት አስቀርቦ እንዱመለከትልን ጠይቀናል። ፍርድ ቤቱ የጠየቅነውን ማስረጃ አስቀርቦ ሣይመለከት ተጠሪ ሰራተኛ ናቸው ጉዲያቸው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ይታያል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረት የሚገባ ስለመሆኑ በውለ አንቀፅ 7 እና አንቀጽ 12 የተመለከቱትን ሀይለ ቃልች በማየት ለመረዲት ይቻላል። አመልካች የተጠሪን የሥራ ዝርዝርና የድርጅቱን መዋቅር በማቅረበ ተጠሪ ሥራ መሪ መሆናቸውን አላስረዲም። ይህ ከሆነ “ክፍለሀጉራዊ ሥራ አስኪያጅ” የሚለውን ስያሜ በማየት ብቻ ሥራ መሪ ናቸው ልባል ስለማይገባ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም ስለዚህ የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያሰናብተኝ በማለት በፅሐፍ መልስ ሰጠተዋል። አመልካች የመልስ መልስ አቀርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና አመልካችና ተጠሪ በፅሐፍ በሰበር ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪው የሥራ መሪ መሆኑን በመግለፅ ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል መዝገቡን ዘግቶታል። በልላ በኩል የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ የሥራ መሪ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረበም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሯል። አመልካች ተጠሪን እንድቀጥር የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስትር ያቀረብኩት አቤቱታ መነሻ ለተጠሪ የውጭ አገር ዜጋ በመሆናቸው ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስትር የተሰጣቸው የሥራ ፈቃድ በፍታብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 145 መሰረት ፍርድ ቤቱ አስቀርቦ እንዲይላቸው ጠይቀው ፍርድ ቤቱ ይህንን ማስረጃ ሣያስቀርብ ተጠሪ የሥራ መሪ አይደለም በማለት ውሣኔ እንደሰጠባቸው በመግለፅ በሰበር ተከራክረዋል።
አመልካች ተጠሪ የሥራ መሪ መሆናቸውን የሥራ ፈቃድም ያገኙት በዚሁ የሥራ ሀላፉነት ለመሰማራት መሆኑን ያስረደልኛል በማለት እንዱቀርብ የጠየቁት ማስረጃ የሥር ፍርድ ቤት ያላስቀረበው በመሆኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ከመስጠቱ በፉት በፍታብሕር ሥነ-ሥርዓት ህግ ቁጥር 345 ንዐስ አንቀፅ 1(ሀ) መሰረት ማስረጃውን በማስቀረብ ውሣኔ መስጠት ነበረበት። የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች እንዱቀርብላቸው የጠየቁት ማስረጃ ሣያስቀርብ መወሰኑ ከላይ የተጠቀሰውን የህግ ድንጋጌ የሚተላለፍ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስኗል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስትር እንዱቀርብላቸው የጠየቁትን ማስረጃ በማስቀረብና ጉዲዩን በማጣራት ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩን በፍታብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መልሰን ልከንለታል።
ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.