No summary available.
ሰኔ 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ አበባ መንገድች ባለሥልጣን- ነገረ ፈጅ ፊሲል በለጠ ተጠሪ፡- ጋድ ቢዝነስ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር- አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሀብሕር ይግባኝ ችልት በመዝገብ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሰኔ 25 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቹ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ለአመልካች አንድ ሺ ቶን አስፊልት በዘጠና ቀን ውስጥ ለማቅረብ የተስማማ መሆኑንና አመልካች በበኩለ ብር 3,565,000 (ሦስት ሚሉዮን አምስት መቶ ስልሣ አምስት ሺህ) ለመክፈል ተስማምቷል፤ ሆኖም
ከሳሽ (ተጠሪ) አስፓልቱን በወቅቱ ያላደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን ለተከሳሽ (አመልካች) ያሣወቀና ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም ተከሳሽ (አመልካች) አላግባብ አስፓልቱ ለዘገየበት በሚል ምክንያት ብር 356,000(ሦስት መቶ ሃምሣ ስድስት ሺ ብር) ከዋጋው ቀንሶ ያስቀረ በመሆኑ ይህንን ገንዘብ ከነወለደ ብር 420,670 (አራት መቶ ሐያ ሺ ስድስት መቶ ሰባ ብር) እንዱከፍል ይወስንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች በበኩለ በውላቸው መሰረት ከሳሽ(ተጠሪ) ባለማቅረቡ በውለ መሰረት በቅጣት መልክ መቀነስ ያለበትን ገንዘብ የቀነሰ መሆኑን፤ በአሜሪካና ኢራቅ ጦርነት አስፓልቱን የጫነችው መርከብ መተላለፉያ አጥታ መቆሟን የሚያሣይ ማስረጃ ተጠሪ ያላቀረበ መሆኑን፤ በጅቡቲ ወደብም አስፓልቱን በማራገፍ ሑደት የገጠመ ችግር የነበረ ስለመሆኑ ከወደቡ አስተዲደር ያቀረበው ማስረጃ የላለ በመሆኑና ተጠሪ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር የገጠመው መሆኑን በውላችን አንቀጽ 10 መሰረት ለተከሳሽ (አመልካች) ያላሳወቀ በመሆኑ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሳያጋጥመው ከሳሽ (ተጠሪ) እቃውን በማዘግየቱ በውለ መሰረት በቅጣት መልክ ያስቀረነውን ክፍያ ለከሳሽ (ተጠሪ) የምንመልስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት ተከራክሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የከሳሽንና(ተጠሪን) ተከሳሽን (አመልካችን) ክርክርና ማስረጃ በመመርመር ተጠሪ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር አስፓልቱን ያላቀረበ መሆኑን ለማስረዲት ያቀረባቸው ማስረጃዎች አዱስ ዘመን ጋዜጣ ሚያዚያ 25 ቀን 1995 ዓ.ም ስለስዊዝ ቦይ እና የአሜሪካና የኢራቅ ጦርነት ይዞት የወጣውን ዜና እና ዩንቨርሳል የተባለ የእቃ አስተላለፉ ድርጅት አስፊልቱን የጫነው መርከብ በጅቡቲ ወደብ አስራ ስምንት ቀን ቆሟል በማለት የፃፈውን ደብዲቤ ነው፤ እነዚህ ማስረጃዎች አስፓልቱን የጫነው መርከብ በስዊዝ ቦይ መተላለፉያ በማጣቱም ሆነ የጅቡቲ ወደብ በመጨናነቁ የዘገየ መሆኑን የሚያስረደ አይደለም፤ ስለዚህ ከሳሽ (ተጠሪ) አስፖልቱን በውለ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ያላደረሱት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት መሆኑን ያላስረደ ስለሆነ ተከሳሽ (አመልካች) በቅጣት መልክ ቀንሶ ያስቀረውን ገንዘብ ለከሳሽ (ተጠሪ) የሚከፍልበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርቧል። የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪን ይግባኝና የአመልካችን መልስ ከተቀበለ በኋላ ቅሬታውንና መልሱን እንደመረመርነው ምላሽ ማግኘት ያለበት ጭብጥ ይግባኝ ባይ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አለ ያለው ነገር መኖሩ በማስረጃ ተረጋግጧል ወይስ አልተረጋገጠም? ከአቅም በላይ የተባለት ምክንያቶች በሕጉ ይካተታለ ወይስ አይካተቱም? በመሆኑም እነዚህን ምክንያቶችን በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793/ሀ/ እና (መ) የሚሸፈኑ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ገንዘቡ ለይግባኝ ባይ ሉከፈል አይገባም በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብ አይደለም” በማለት አመልካች ብር 356,500 (ሦስት መቶ ሐምሣ ስድስት ሺ አምስት መቶ ብር) ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቷል። ተጠሪ አስፓልቱን ማቅረብ ከነበረበት በሰማኒያ ሶስት ቀን ዘግይቶ አቅርቧል፤ ተጠሪ መዘግየቱ የተፈጠረው ከአቅም በላይ መሆኑን የሚያስረዲ የሕጉን መስፈርት የሚያሟላ ምክንያትና ማስረጃ አላቀረበም፤ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማስረጃውን መርምሮ የሕግ ድንጋጌዎችን አገናዝቦ የሰጠውን ውሣኔ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ማስረጃውን ሣይመረምርና ሣይመዝን ከተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ሣያገናዝብ በጭብጥነት የያዛቸውን ጭብጦች ሣያይ የፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793(ሀ) እና (መ)”ን” በመጥቀስ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ ማጽናቱ ተገቢ ባለመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ በአሜሪካና በኢራቅ ጦርነት ምክንያት በስዊዝ ቦይ መርከቦች እንዲይተላለፈ በመከልከለና በጅቡቲ ወደብ በነበረው መጨናነቅ እቃውን በወቅቱ ለአመልካች ያላስረከብኩ መሆኑንና ይህም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት መሆኑን በማገናዘብ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የላለበት ስለሆነ የአመልካች የሰበር አቤቱታ እንዱሰረዝልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካችም የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ያደረጉት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል።
መዝገቡን እንደመረመርነው የከፍተኛው ፍ/ቤት ተጠሪ አስፓልቱን ሣያቀርብ የቀረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በማለት የሰጠው ውሣኔና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህንን ውሣኔ በማጽናት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ መፈታት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በውለ መሰረት ለመፈጸም የገደበው ከአቅም በላይ የሆነ ነገር አላጋጠመውም ከሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው በአሜሪካን እና ኢራቅ ጦርነት ምክንያት የስዊዝ መተላለፉያ ቦይ የተዘጋ መሆኑንና ለዚህ ጊዜም አስፓልቱን የጫነችው መርከብ ታግዲ የነበረች ስለመሆኗ በቂ ማስረጃ አልቀረበም፤ በማስረጃነት የቀረበው በጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ዜና ይህንን አያስረዲም፤ አስፓልቱን የጫነችው መርከብ የጅቡቲ ወደብ በመጨናነቁ ምክንያት ለማራገፍ ባለመቻሎ ነው ለሚለው ፍሬ ጉዲይ ከጅቡቲ ወደብ አስተዲደር የቀረበ ማስረጃ የለም፤ ከግል እቃ አስተላላፉ ድርጅት የተፃፈው ደብዲቤ ታአማኒነትና ክብደት የለውም በማለት ነው።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በይግባኝ መወሰን ያለባቸውን ሁለት ጭብጦች ከያዘ በኋላ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ የቀረቡትን ማስረጃዎች ተአማኒነትና ክብደት ከፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793 ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የሰጠውን ምክንያትና ማብራሪያ የማይቀበልበትን ምክንያት ሳይገልጽ ማስረጃዎቹን ሳይመዝንና ከሕጉ ጋር ያላቸውን ተዛማጅነት ሣያብራራ በአንድ መስመር ተጠሪ እቃውን ያላቀረበው በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793(ሀ) እና(መ) መሰረት ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ስለ ውሣኔ አሰጣጥ በፍትሀብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 182 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገገውን የሚጥስ፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በግልጽ በተቀመጠ ምክንያት ሣይሆን የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔን የመሻር ስልጣን ስላለው ብቻ የሻረው መሆኑን የሚያሣይ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ያጋጠመው መሆኑን ለማስረዲት በወቅቱ በአሜሪካና በኢራቅ መካከል ጦርነት መኖሩንና በዚህ ምክንያት በስዊዝ ቦይ መተላለፉያ ችግር የነበረ መሆኑን በጋዜጣ የተዘገበ ዜና ማቅረቡ ብቻውን በቂ አይደለም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ትርጉም ከፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 ንኡስ አንቀጽ 1 ጋር የሚጣጣም ነው። ተጠሪ በዚያን ወቅት አስፓልቱ በመርከብ ተጭኖ የነበረ መሆኑን፣ አስፓልቱን የጫነችው መርከብ ጉዞዋን ጀምራ ስዊዝ መተላለፉያ ቦይ ስትደርስ በጦርነቱ ምክንያት መተላለፉያ በመዘጋቱ ስንት ቀን እንደቆመች እና በዚህ ምክንያት በውለ የተገለፀው የጊዜ ገደብ ያለፈ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅባቸዋል። ተጠሪ እነዚህን ዝርዝር ሁኔታዎች የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረቡም። ተጠሪ የተፈጠረው ጠቅላላ ሁኔታ እሳቸው ውለን ለመፈጸም ባደረጉት ጥረት ላይ የፈጠረውን እርግጠኛ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ባላስረደበት ሁኔታ በአዱስ ዘመን ጋዜጣ ስለ ጦርነቱ ሁኔታ የተዘገበ ዜና ለስር ፍርድ ቤት በማቅረብ ውለን ያልፈጸምኩት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን አስረድቻለሁ በማለት ያቀረቡት ክርክርና የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪን ክርክር በመቀበል የሰጡት ውሣኔ የፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 ንኡስ አንቀጽ (1)”ን” መሰረታዊ መርህ የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል ተጠሪ በሁለተኛ ምክንያትነት ያነሱት የጅቡቲ ወደብ መጨናነቅ ስለ ወደቡ አስተዲደርና ወደቡ መርከቦችን በማስተናገድ በኩል ስለገጠመው ችግር ማስረጃ የመስጠት ስልጣንና ሐላፉነት ካለው የጅቡቲ ወደብ አስተዲደር የተሰጠ አይደለም። ተጠሪ ወደቡ በመጨናነቁ አስፓልቱን የጫነችው መርከብ ቆማ የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሳል የተባለ እቃ አስተላላፉ ድርጅት የፃፈውን ደብዲቤ በማስረጃነት ያቀረበ ቢሆንም ይህ ማስረጃ ተጠሪ በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 ንኡስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ አስፓልቱን ለአመልካች ሣያቀርብ የቀረ መሆኑን የማስረዲት ብቃትና ተአማኒነት የላለው መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ከበቂ ምክንያት ጋር አስቀምጧል። በልላ በኩል ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት ፍርድ ቤቶች ይህ ማስረጃ በምን ምክንያት ተአማኒነት ሉሰጠው እንደማይገባና ተጠሪ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ያጋጠመው ስለመሆኑ በቂ አስረጂ አድርገው እንደወሰደት አልገለፁም።
በአጠቃላይ ሲታይ ተጠሪ ውለን በወቅቱ ያልፈጸመው በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 እና በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793 የተደነገጉት ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ያጋጠመው መሆኑን ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክሙን በአግባቡ ያልተወጣ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ማስረጃዎቹን ከሕጉ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ የወሰነ ሲሆን ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት ፍርድ ቤቶች የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽረናል ከሚለ በስተቀር ተጠሪ እርግጠኛ በሆነ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ምክንያት ውለን ሣይፈጽም የቀረ ስለመሆኑ የሰጡት ምክንያትም ሆነ ማብራሪያ የለም።
በእኛም በኩል ተጠሪ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ስላጋጠመው ውለን በጊዜው ሣይፈጽም የቀረ መሆኑን ለመደምደም የሚያስችለ በፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 እና 1793 ድንጋጌዎች የሚሸፈኑ ሁኔታዎች በመዝገቡ በተደረገው ክርክር የላለ መሆኑን ተገንዝበናል። ስለሆነም ጉዲዩን በይግባኝ ያዩት ፍርድ ቤቶች የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በአግባቡ ሣይመረምሩ እና ለውሣኔአቸው በቂ ምክንያት ሣይሰጡ ተጠሪ እቃውን በወቅቱ ያላቀረበው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሣኔ መሻራቸው የፍትሀብሕር ስነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 182 ንኡስ አንቀጽ 1 የፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1792 እና የፍትሀብሕር ሕግ ቁጥር 1793 ድንጋጌዎችን የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
ይፃፍ።
ተጠሪ እቃውን በውለ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያላቀረበው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት አይደለም ብለናል።
አመልካች ተጠሪ በውለ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ አስፓልቱን ባለማቅረቡ ለተጠሪ ከሚከፍለው ክፍያ በመቀጫ መልክ ቀንሶ ያስቀረውን ገንዘብ የመመለስ ግዳታ የለበትም። ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.