No summary available.
ሰኔ 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ ስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፊፈያ ድርጅት- ነ/ፈጅ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሳህለ ወ/ማሪያም- ከጠበቃ ጋር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ከግንቦት 5 ቀን 1991 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 7 ቀን 1996 ዓ.ም ድረስ ተከሳሽ በከሳሽ ድርጅት በገንዘብ ያዥነት ሲሰሩ በኃላፉነት ከተረከቡት ገንዘብ ላይ ብር 72,710.48 (ሰባሁለት ሺህ ሰባት መቶ አስር ብር ከአርባ ስምንት ሣንቲም) በጉድለት እንደሚፈለግ በኦዱት ምርመራ የተረጋገጠ ስለሆነ ይህንኑ ገንዘብ ከወለድ ከወጭና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንልን በማለት ጠይቋል።
ተከሳሽም ቀርበው በከሳሽ ድርጅት በገንዘብ ያዥነት መስራታቸውን አምነው ነገር ግን በኃላፉነት ሲያንቀሳቅሱት የነበረው ሂሳብ በየወቅቱ ኦዱት እየተደረገ በጉድለት የሚፈለግ ገንዘብ እንዲልነበር ከግንቦት 5 ቀን 1991 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 7 ቀን 1996 ዓ.ም ድረስ በከሳሽ መ/ቤት በገንዘብ ያዥነት በሰሩበት ጊዜ ገንዘብ ስለማጉደላቸው በኦዱት እንዲልተረጋገጠ ገልጸው ክሱ ከኪሳራ ጋር ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ጉዲዩን መርምሮ ተከሳሽ በክስ የተጠየቀውን ገንዘብ ስለማጉደላቸው ከሳሽ በማስረጃነት ባቀረበው የኦዱት ሪፖርት ላይ ያልተረጋገጠ ስለሆነ ክሱ የማስረጃ ድጋፍ የላለው ነው በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት ይግባኙን በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ሰርዟል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ክሱን ያስረደልኛል በማለት የቆጠራቸውን የባለሙያ ምስክሮች የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሳይሰማ ውሳኔ መስጠቱ ለሰበር ቀርቦ መመርመር እንዲለበት በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን አቤቱታው ለሰበር ላቀርብ ይገባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ የሰበር አቤቱታው እንደሚከተለው ተመርምሯል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ ተጠሪ በኃላፉነት ሲያነቀሳቅሱት የነበረውን ሂሳብ መርምረው ጉድለት መኖሩን ያረጋገጡት ኦዱተሮች ቀርበው የሙያ ምስክርነት ቃላቸውን እንዱሰጡ አመልካች በማስረጃነት የቆጠራቸው መሆኑን ተገንዘበናል።
አንድ ተከራካሪ ወገን በማስረጃነት የሚጠቅሳቸው ምስክሮች፣ሰነድች ወይም ላላ አስረጂዎች እንዱቀርቡ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ ከመስጠቱ በፉት ማስረጃው በጭብጥ ተይዞ ከሚፈታው ፍሬ ነገር ጋር አግባብነት(Relevance) ያለው ስለመሆኑና በሕግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ (Admissible Evidence) ስለመሆኑ ማጣራት እንደሚገባው ከማስረጃ አቀራረብና አቀባበል መርህ አኳያ መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች የጠቀሳቸው ምስክሮች ከላይ እንደተመለከተው ተጠሪ በኃላፉነት ሲያንቀሳቅሱት የነበረውን ሂሳብ መርምረው ጉድለት መኖሩን በኦዱት ያረጋገጡ መሆኑን አመልካች በማስረጃ ዝርዝሩ ላይ ጠቅሷል። እነዚህ የሙያ ምስክሮች ጉድለት ስለመኖሩ የሚያረጋግጡ ናቸው ከተባለ ተጠሪ የገንዘብ ጉድለት ፈጽመዋል ወይንስ አልፈጸሙም? ተብል በጭብጥነት ከሚያዘው ፍሬ ነገር ጋር የተያያዘና አግባብነት ያለው የምስክርነት ቃል እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ከዚህም ላላ በምስክሮቹ የሚሰጥ የሙያ ምስክርነት ቃል በሕግ ተቀባይነት የላለው (Inadmissible) አይደለም። አመልካች በዚህ መልኩ የቆጠራቸው ምስክሮች ቀርበው መሰማታቸው ክርክሩ ከሚመራበት የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 111፣249 እና 257 አኳያ እንደዚሁም ከማስረጃ አቀራረብና አቀባበል አኳያ ተገቢነት ያለው ሆኖ ሳለ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እነዚህን ምስክሮች ሳይሰማ ለዚህ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነውን ውሳኔ መስጠቱ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ጉድለት በይግባኝ ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
No topics extracted.
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22762 በ7/4/2000 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የፋዳራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 62605 በ21/8/2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች የቆጠራቸውን የሙያ ምስክሮች በመስማት ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።