No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ወ/ሮ አያልነሽ ዘገየ- ጠ/ሙለጌታ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ደምሴ- ጠ/ጌታቸው ሞላ ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው። የአመልካችና የተጠሪ ጋብቻ በፍቺ ከፈረሰ በኋላ የንብረት ክፍፍለን በተመለከተ ባለሙያ አጣርቶ ለፍ/ቤቱ ውጤቱን የገለጸ ሲሆን ፍ/ቤቱም የቀረበውን ውጤት በአብዛኛው ተቀብል በተወሰኑ ጉዲዮች ራሱ መርምሮ ውሣኔ ሰጥቷል። ፍ/ቤቱ ራሱ መርምሮ ውሣኔ ከሰጠባቸው ነጥቦች ውስጥ አንደኛው የእቁብ ገንዘብን የሚመለከት ነው። ንብረት አጣሪው በአቶ ታደሰ ተክላ የሚሰበሰብ እቁብ መኖሩን አረጋግጠው ሁለቱም የእቁብ ገንዘቡን እኩል መካፈል ስላለባቸው ተጠሪ ለአመልካች ብር 247,500(ሁለት መቶ አርባ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዱከፍለ ሲወስኑ በተጠሪ የሚሰበሰበውን እቁብ ግን ፍ/ቤቱ እንዱያጣራው አሣስበዋል።
በዚህ መሰረት ፍ/ቤቱ ጉዲዩን አጣርቶ የዚህን ገንዘብ ግማሽ ተጠሪ ለአመልካች እንዱከፍለ ሲወስን በአቶ ታደሰ ተክላ የሚሰበሰበውን እቁብ በተመለከተ ስለማጽደቁ በውሣኔው ሣይጠቅስ አልፎል።
አመልካችም ለችልቱ በአቶ ታደሰ ተክላ ዲኝነት ይሰበሰብ የነበረውን እቁብ በተመለከተ በንብረት አጣሪው የቀረበውን ውሣኔ ፍ/ቤት ሣያጸድቅ ስላለፈው ይታረምልኝ በማለት አመልከተው ፍ/ቤቱም ይህንኑ ማጽደቁን በውሳኔው ሳያሰፍር ያለፈው በዝንጋታ በመሆኑ ይህንንም እቁብ ግራ ቀኙ እንዱካፈለት የሚለው ዓረፍተ ነገር ቀደም ሲል በሰጠው ውሣኔ ውስጥ እንዱካተት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት ትእዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ በአመልካች የቀረበው ጥያቄ በይግባኝ የሚስተካከል እንጅ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት የሚስተካከል አይደለም በማለት የፍ/ቤቱን ትእዛዝ ሽሯል። በዚህ ላይ አመልካች ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ጠይቀው ይግባኛቸው ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቷል።
ከዚህ በኋላ አመልካች የስር ፍ/ቤት በአቶ ታደሰ ተክላ ሲሰበሰብ የነበረውን እቁብ አስመልክቶ አጣሪው የሰጠውን ውሣኔ ሣያጸድቅ ማለፈ ስህተት ነው በማለት ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ይግባኝ የቀረበበት ጉዲይ የይግባኝ ማቅረቢያው ጊዜ ያለፈ በመሆኑና የይግባኙ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈውም በበቂ ምክንያት ስላልሆነ ይግባኙ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጏታል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ላይ ለዚህ የሰበር ችልት አቤቱታ አቅርበዋል።
ችልቱም አመልካች ያቀረቡት ይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ነው ተብል ውድቅ የመደረጉን አግብብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጏ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በቃል አሰምተዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው የንብረት አጣሪው በአቶ ታደሰ ተክላ ከሚሰበሰበው እቁብ ተጠሪ የወሰደት 495,000 (አራት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር) ግማሽ ለአመልካች እንዱከፈላቸው ወስነዋል። ፍ/ቤቱ የንብረት አጣሪውን ውሣኔ ሲያጸድቅ ግን ይህን የእቁብ ገንዘብ በተመለከተ የተሰጠውን ውሣኔ ሣያጸድቅ አልፍታል። አመልካች ይህ የታለፈው ነጥብ እንዱታረምላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት ለፍ/ቤቱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ፍ/ቤቱ ይህን ነጥብ ሣያጸድቅ ያለፈው በዝንጋታ መሆኑን በማጤን አጣሪው የሰጡትን ውሣኔ አጽድቋል። ተጠሪ ግን ይህን ትእዛዝ ተቃውመው ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው የአመልካችዋ ጥያቄ ሉስተናገድ የሚገባው በይግባኝ እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 አይደለም በማለት ወስኗል። ይህ ውሣኔም በፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ፀድቋል። እንግዱህ ከክርክሩ ሂደት አመልካችዋ ይህን ክርክር ያስነሣውን የእቁብ ገንዘብ በተመለከተ በዲተኝነት ትተውት የተቀመጡ ሣይሆን ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበው በክርክር ሂደት ላይ ነበሩ። ሣይፀድቅ የታለፈው የእቁብ ገንዘብ እንዱታረም ተገቢ ነው ባለበት የሥነ-ሥርአት መንገድ ጥያቄ አቅረበው የነበረ ቢሆንም ጥያቄው የቀረበበት ሰርአት የሥነ-ሥርአት ሕጉን የተከተለ ነው አይደለም በሚል በተነሣ ክርክር የተወሰነ ጊዜ ማለፈን ተገንዝበናል። የመጨረሻ ፍ/ቤቱም ጥያቄው ሉስተናገድ የሚገባው በይግባኝ ነው በማለት ከወሰነ በኋላ አመልካችዋ ሣይዘገዩ ይግባኝ አቅርበዋል። በእርግጥ አመልካችዋ ይግባኙን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረቡበት ወቅት ይግባኝ የተጠየቀበት ውሣኔ ከተሰጠ የ60 ቀናት ጊዜ አልፎል። አመልካችዋ ያቀረቡት ይግባኝ ጊዜው ያለፈ መሆኑን ፍ/ቤቱ የተረዲው ዋናው ይግባኝ በሚታይበት ጊዜ በመሆኑ አመልካችዋ ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ማቅረቢያ ማስፈቀጃ አላቀረቡም። ፍ/ቤቱም ጊዜው ማለፈን እንደተረዲ የማስፈቀጃ ማመልከቻ እንዱቀርብ ማድረግ ሲገባው ይህንን ባያደርግም አመልካችዋ ይግባኝ ሣያቀርቡ ጊዜው ያለፈበትን ምክንያት ግን ተመልክቶ በቂ አይደለም በማለት ወስኗል።
No topics extracted.
አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዲ ይግባኙ እንዱቀርብ ሉፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል። በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሉመረምረው ይገባል። በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባለትን ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዲንደ ጉዲይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሉመዘኑ ይገባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካችዋ ተጠሪው ከወሰደት የእቁብ ገንዘብ ግማሹ የሚገባቸው ለመሆኑ በአጣሪው ተወስኖላቸው ይህንን ነጥብ ፍ/ቤቱ ሣያጸድቅ አልፍታል። ይህ ጉዲይ ሉታረም የሚገባው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ነው ወይስ በይግባኝ ነው የሚለው ጉዲይ ክርክር እየተደረገበት ስለነበር እንጂ ጊዜው ያለፈው አመልካች መብታቸውን ሣይጠይቁ ዲተኝነት አሣይተው አለመሆኑን በመዝገቡ ከቀረቡት ፍሬ ነገሮች መረዲት ይቻላል። በመሆኑም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈው በበቂ ምክንያት አይደለም በማለት የሰጠው ውሣኔ ከላይ የተጠቀሰውን የሥነሥርአት ሕግ በአግባቡ ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 59015 መጋቢት 4 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
አልካች ይግባኝ ሣያቀርቡ ጊዜው ያለፈባቸው በበቂ ምክንያት ነው ብለናል።
አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብል ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። የስር ፍ/ቤት መዝገብ ይመለስ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ለመ/ቤት ይመለስ።