No summary available.
ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብልደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ዓለሙ መግራ - ቀረበ ተጠሪ፡- እምነቴ እንደሻው ህንፃ ተቋራጭ - ነ/ፈጅ ግርማ ወርቁ ቀረቡ መዝገቡን መርመረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የተጀመረው ፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካች ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር ጉዲዩ የስራ ክርክር ሆኖ መጀመሪያ አመልካች ባቀረበው ክስ መነሻ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ በ5/10/99 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች የስራ መሪ እንጂ ሰራተኛ አይደለም በማለት ክሱ በብይን ውድቅ ሲደረግ ይግባኝ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በሆነው ኀዲር 11 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ብይንን መሻር አመልካች የስራ መሪ ሳይሆን ሰራተኛ ነው በማለት በፍሬ ነገር ላይ ውሳኔ እንዱሰጥት በማዘዝ ለመጀመሪያ ፍ/ቤት ጉዲዩ ተመለሰ። ከዚህ በኋላ ክርክሩ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲካሄድ ሐምል 13/99 ዓ.ም በተፃፈ መቃወሚያ የግዛት ክልል ስልጣን የለም የሚለውን መቃወሚያ ቀርቦ ፍ/ቤቱ በማለፍ በፍሬ ነገር ላይ የስራ ውል የተቋረጠው አለአግባብ ነው የ6 ወር ካሳና የ2 ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና የየካቲት ወር ደመወዝ እዱከፈላቸው ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለመዲኝት የግዛት ክልል ስልጣን የለውም ተጠሪ ዋና መ/ቤቱ አዋሳ ነው በማለት ውሳኔው በመሻሩ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ሐምል 2 ቀን 2000 ዓ.ም ጽፍ ያቀረበው ቅሬታ፡የተጠሪ ቅርንጫፍ ቢሮ አዱስ አበባ ከተማ ያለ ስለመሆኑ በማረጋገጥ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ገጽ 8 የቅጥር ማስታወቂያ ላይ አድራሻ አ.አ መሆኑን የገለጸ ከመሆኑም በላይ በተመሳሳይ የስራ ክርክር በመ/ቁ. 29465 ፣37317 በየካ ምድብ ችልት በመ/ቁ. 21206 በቄራ ምድብ ችልት ጉዲዮች የታዩ መሆኑን በመግለጽ የግዛት ክልል ስልጣን የለም የተባለው ስህተት በመሆኑ ውሳኔው እንዱሻር የሚጠይቅ ነው።
ይህ ችልት የግዛት ክልል ስልጣን የለም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ያስቀርባል ተብል ግራ ቀኙ የቃል ክርክር አካሄደዋል። የተጠሪ የቃል ክርክር አዱስ አበባ ያለው የእቃ ገዥ እና የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እንጅ ዋና መ/ቤቱ አዋሳ ነው በማለት ውሳኔው እንዱፀና ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመዘገበው ሲሆን እኛም እንደሚከተለው መርምረናል።
በተያዘው ጉዲይ አስቀድሞ አመልካች የስራ መሪ ነው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ጉዲዩ አይታይም ተብል ክሱ በብይን ውድቅ ተደርጏ በይግኝ ታይቶ እንደገና እንዱታይ ተወስኖ ሲመለስ የአሁኑ ተጠሪ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን እንደገና ሉያይ የሚችልበት የግዛት ክልል ስልጣን የለውም ስልጣን ለላለው ፍ/ቤት ነው ጉዲዩ እንዱታይ እንዱመለስ የተደረገው በማለት በይግባኝ እንዱታረምለት አልጠየቀም። በውሳኔው ተስማምቶ በፍሬ ጉዲይ ላይ ለመሟገት ከመለሰ በኋላ እንደገና የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር የሚያነሳበት የሕግ አግባብ የላለ ከመሆኑም በላይ ይልቁንም የድርጅቱ ቅ/ጽ/ቤት አ/አበባ ከተማ ለም ሆቴል አካባቢ ኃይላ ገ/ስላሴ መንገድ እንደሆነ አመልካች በቅሬታው የጠቀሰውን የተጠሪ ጠበቃ በክርክራቸው የእቃ ግዥ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ የተከራከረ በመሆኑ የግዛት ክልል ስልጣን የለውም በማለት የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሳኔ ነው ብለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 6 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ፍ/ቤቱ የግዛት ክልል ስልጣን አለው ብለናል። በመሆኑም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍሬ ጉዲዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ በሕጉ አግባብ መሆን አለመሆኑን ከሕግና ከማስረጃ አንፃር በማገናዘብ ተገቢውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341 መሰረት ለከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱመለስ ወስነናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ
No topics extracted.
መዝገቡን ዘግተናል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
መ/ በመጣበት ሁኔታ ይመለስ።