No summary available.
ሰኔ 11 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአ.አ ከተማ ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ አቶ ተስፊዬ ዘመድኩን - ቀርበዋል ተጠሪ፡- አቶ ዓለም ገብሩ - ጠበቃ አቶ አታክልት ኃ/ስላሴ ቀርበዋል ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
አቤቱታው የቀረበው አመልካች ሰኔ 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ.
59626 ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም እንዱሁም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/ቁ. 72799 ሰኔ 11 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጧቸው ፍርድች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው ስለሆኑ ይሻሩልኝ በማለቱ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ከሣሽ፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ በስር ፍ/ቤቱ ተከሣሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን፣ ስር ከሣሹ ሚያዚያ ዐ9/1999 ዓ.ም ያቀረቡት የተሻሻለ ክስ መሰረታዊ ይዘቱ ተከሣሹ የሚያስተዲድራቸውን ቤቶች ለመሸጥ ጨረታ ባወጣው መሰረት በ6ኛ ዙር የጨረታ ሂደት በመሣተፍ በኮልፋ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በቀበላ 15/16 በአስኮ ሣይት የሚገኙትን ቁጥራቸው AS-B7-ዐዐ193 እና AS-B8 -ዐዐ243 የሆኑትን ሁለት ቤቶች እያንዲንዲቸውን በብር 81,33ዐ /ሰማንያ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሰላሣ ብር/ ዋጋ በማሸነፍ የካቲት 21 ቀን 1998 እና መጋቢት ዐ4 ቀን 1998 ዓ.ም የተፃፈ የሽያጭ ውል በማሰር የቤቶቹን ዋጋ ለተከሣሹ የከፈልኩ ብሆንም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቤቶቹን ሉያስረክበኝ ስላልቻለ ቤቶቹን እንዱያስረክበኝ፣ የባለቤትነት ማስረጃም እንዱሰጠኝ በማለት ጠይቀዋል። የሥር ፍርድ ቤቱም ስር ተከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ትእዛዝ ደርሶት ስላልቀረበና ክርክሩን ለማካሄድ በተቀጠረበት ቀንም በመቅረቱ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ አዟል። ዋናውን ጉዲይ በተመለከተም ተከሣሹ በክስ የተጠቀሱትን ቤቶች በጨረታ ለከሣሹ እንደሸጣቸውና ዋጋቸውንም ተቀብል ውል እንዲሰረ በመግለጽ ቤቶቹን ለከሣሹ ማስረከብ እንዲለበት ወስኗል።
በአሁኑ አመልካች ይግባኝ ባይነት ጉዲዩ ወደ ፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢቀርብም ፍ/ቤቱ በመ/ቁ. 59626፣ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
ከላይ የሰፈረውን ፍርድ በመቃወምም አመልካቹ ሰኔ 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም አከራካሪው ጉዲይ ማለትም ቤቶቹ በአመልካቹ የሚተዲደሩ በመሆናቸው እንዱሁም የአዱስ አበባ አስተዲደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት ከሚዋዋሎቸው ውልች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41 መሰረት የዲኝነት ስልጣኑ የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች እንጂ የፋዳራል ፍ/ቤት ስልጣን አይደለም፤ የስር ፍ/ቤቶቹ ስልጣን ሣይኖራቸው የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤
እንዱሁም ተጠሪው ቤቶቹን የገዛቸው ለጨረታ በተቀመጠው መነሻ ዋጋ ነው፤ ሆኖም የከተማው አስተዲደር ያወጣው የጨረታ መመሪያ የጨረታ አሸናፉ ለመሆን ከጨረታው መነሻ ዋጋ በላይ መሸጥ እንዲለበት ስለሚያመለክት ሽያጩ ሕጋዊ ባልሆነበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶቹ የሽያጭ ውል አለ በማለት የሰጡት ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ ስለሆነም ውሣኔው ይሻርልን የሚል ነው።
ተጠሪም ሚያዚያ 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ መልሣቸው አመልካቹ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ጠቅሰው የተከራከሩበት አዋጅ ቁ.
362/95 አንቀጽ 41 የሚል እንጂ አዋጅ ቁ. 361/95 አንቀጽ 41 የሚል አይደለም ስለሆነም በስር ፍ/ቤት ያልተጠቀሰውን በዚህ ሰበር ችልት መከራከሪያ ሉያደርጉት አይችለም፤ ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶቹ የፈፀሙት የሕግ ስህተት ስለላለ ውሣኔያቸው ይጽደቅልኝ ብለዋል።
ይህ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ በሰፈረው መልክ በመገንዘብ፣ ይህን ጉዲይ የማየት ስልጣን ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው? በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል በሕግ የሚፀና የቤት ሽያጭ ውል አለ ወይስ የለም?
የሚለትን ጭብጦች በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካቹ ባቀረበው ክርክር ይህንን ጉዲይ የማየት ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር እንጂ የፋዳራል ፍ/ቤቶች መሆን የለባቸውም፤ ይህንንም የስልጣን ጉዲይ የስር ፍ/ቤቶቹ በራሣቸው አነሣሽነት ስልጣን እንደላላቸው መበየን ሲገባቸው ወደ ዋናው ክርክር ገብተው ውሣኔ መስጠታቸው ተገቢነት የለውም ሲለ ተጠሪው ግን ከላይ የቀረበውን ክርክር ባለመቀበል አከራካሪውን ጉዲይ በተመለከተ የስር ፍ/ቤቶቹ ስልጣን የላቸውም ሉባለ አይገባም ብለዋል።
እንደሚታወቀው አመልካቹ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አካል ሲሆን የክርክሩ መነሻም እሱ የሚያስተዲድራቸውን ቤቶች አስመልክቶ የተደረገ የሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ነው። የተሻሻለው የአዱስ አበባ ከተማ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 እንዲሰፈረው ደግሞ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር አስፈፃሚ አካላት ወይም በስሩ ያለ ላልች አካላት የሚገቧቸውን ውልች በተመለከተ እንዱሁም የከተማው አስተዲደር ከሚያስተዲድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ክርክሮች የመዲኘት ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች መሆናቸውን በግልጽ አስፍሯል። ተጠሪው ባቀረቡት ክርክር አመልካቹ በስር ፍ/ቤት የጠቀሰው አዋጅ ላላ ነው ከማለት ውጭ ከላይ የሰፈረውን የዲኝነት ስልጣን በቀጥታ አላስተባበለትም። የስር ፍ/ቤቶቹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 9/2/ መሰረት ስልጣን የላላቸው መሆናቸውን በራሣቸው አነሣሽነትም ቢሆን ጉዲዩን አንስተው ተገቢውን ብይን መስጠት ማለትም የክሱ ማመልከቻ ተቀባይነት የለውም ብለው መዝጋት ሲገባቸው አከራካሪውን ጉዲይ የማየት ስልጣን እንዲላቸው አድርገው በክርክሩ ዋና ነጥብ ውሣኔ መስጠታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ 1/ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 59626፣ጥር 21/2ዐዐዐ ዓ.ም እንዱሁም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/ቁ. 72799፣ ሰኔ 11/1999 ዓ.ም የሰጧቸው ፍርድች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
2/ የፋዳራል ፍርድ ቤቶች አከራካሪውን ጉዲይ የማየት ስልጣን የላቸውም፤ ጉዲዩን የማየት ስልጣን ያላቸው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤቶች ናቸው ብለናል።
3/ ሰኔ 12/2ዐዐዐ ዓ.ም እና ሐምል 28/2ዐዐዐ ዓ.ም የተላለፈት እግድች ተነስተዋል፤ ለሚመለከተው ይፃፍ።
4/ ግራ ቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ ብለናል።
ጉዲዩ ያለቀ በመሆኑ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.