No summary available.
ሰኔ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ መኯንን ዘውዳ- ቀረቡ ተጠሪ፡-
ይህ ጉዲይ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዲ ፍ/ቤት ነው።
የጉዲዩ አመጣጥም ሲታይ ሦስተኛ ተጠሪ በገንዘብ እዲ ምክንያት አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎችን በደራ ወረዲ ፍ/ቤት ከሰው ካስፈረደ በኋላ ንብረትነቱ የፍርድ ባለእዲዎቹ /የአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች/ የሆነ ቤት በፍርድ አፈፃፀም ተሸጦ እዲው እንዱከፈል ተብል የአፈፃፀም ትእዛዝ ተሰጥቶ ይሄው ቤት ለአመልካች ተሸጦ እዲው እንደተከፈለ መዝገቡ ያስረዲል። ከዚህ በኋላም የፍርድ ባለእዲዎች የይግባኝ ቅሬታ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ ይግባኝ ባዮች ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ለመ/ሰጭ /ለስር ከሳሹ/ ይክፈለ ተብል የተሰጠውን ዋናውን ውሳኔ በመሻር በነፃ አሰናብቷቸዋል። ከዚህ ውሳኔ በኋላም ፍርደን ያስፈጸመው የወረዲ ፍ/ቤት ዋናው ውሳኔ የተሻረ መሆኑን መሰረት በማድረግ የተሸጠውን ቤት ተከሳሾች እንዱረከቡት በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል። ይህንኑ ቤት በፍርድ አፈፃፀም በኩል በተደረገ ሽያጭ ገዝቼዋለሁ የሚለት የአሁን አመልካች ይህንኑ የወረዲውን ፍ/ቤት ትእዛዝ በመቃወም የይግባኝ ቅሬታቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ትእዛዝ ጉድለት የላለው ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 337 መሰረት ይግባኙን ሰርዟል።
ከዚህም በመቀጠል የይግባኝ ቅሬታቸውን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ ዋናው ውሳኔ ከተሻረ ተከራካሪ ወገኖች ቀድሞ ወደ ነበሩበት ሁኔታ ለመመለስ ጥያቄ ካቀረቡ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 349/1/ መሰረት ወደነበሩበት እንዱመለሱ መደረግ አለበት፤ ነገር ግን በዚህ ጉዲይ ተሸጧል የተባለው ቤት ለስር ተከሳሾች እንዱመለስ ሲታዘዝ የሽያጩን ገንዘብ የስር ከሳሽ እንዱመልሱ መደረግ ሲገባው ይህ ያልተከናወነ ስለሆነ በዚሁ መሰረት የሸያጩን ገንዘብ የስር ከሳሹ ለአመልካች እንዱመልሱ በማለት የስር ፍ/ቤትን ትእዛዝ በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልትም መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት ወሳኔውን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህም ችልት አቤቱታውን መርምሮ ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪዎችን በመጥራት እንደዚሁም የስር ከሳሹ በተጠሪነት ተጣምረው ባለመገኘታቸው እሳቸውን ሦስተኛ ተጠሪ በማድረግ ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የሰበር አቤታታውም እንደሚከተው ተመርምሯል።
በአንድ ፍ/ቤት የተሰጠ ፍርድ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የተለወጠ ወይም የተሻሻለ እንደሆነ ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ነገሩን በመጀመሪያ ለተመለከተው ፍ/ቤት ሲያመለከት የተወሰደው ገንዘብ ወይም ንብረት እንዱመለስ ተስማሚ መስል የታየውን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 349/1/ ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ ንብረትነቱ የአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች የሆነው ቤት በፍርድ አፈፃፀም ለአሁን አመልካች ተሸጦ የሽያጩም ገንዘብ የፍርድ ባለመብት ለነበሩት ለአሁን ሦስተኛ ተጠሪ ተከፍሎል። የአሁን አመልካችም ይህንኑ በፍርድ አፈፃፀም በሽያጭ ያገኙትን ቤት አሳልፈው ለላላ ወገን መሸጣቸውን ከመዝገቡ ተረድተናል። ከፍ ብል በተጠቀሰው የሰነ-ስርአት ሕጉ ድንጋጌ መሰረት ፍርደ በይግባኝ በተለወጠ ጊዜ በዚሁ መሰረት ተከራካሪ ወገኖች ፍርደ ከመፈጸሙ በፉት ወደነበሩበት እንዱመለሱ ትእዛዝ መስጠት የሚቻል ሲሆን ነገር ግን በዚህ ጉዲይ ቤቱ በፍርድ አፈጻጻም ለአመልካች ከተሸጠ በቤቱ ላይም ለውጥ ከተደረገበት በኋላ እንደገና ለላላ ወገን የተሸጠ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ ቤቱ ለስር ተከሳሾች /ለአሁን አንደኛ ተጠሪዎች/ ይመለስ መባለ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። የድንጋጌውም ይዘት ሲታይ ፍ/ቤቱ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ተገቢ መስል የታየውን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል የሚያሳይ ፈቃጅ ድንጋጌ እንጂ አስገዲጅ ድንጋጌ አይደለም።
ስለሆነም ከፍ ብል በተጠቀሰው አኳኋን ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ሉመለሱ ይገባል ተብል እስከ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ድረስ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 48176 በ4/9/2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 42032 በ17/5/99 የሰጠው ውሳኔ፣የሰሜን ሸዋ ዞን ከ/ፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 11335 በ28/9/98 የሰጠው ትእዛዝ እንደዚሁም የደራ ወረዲ ፍ/ቤት በ24/8/98 የሰጠው ትእዛዝ ተሽረዋል።
አመልካች በፍርድ አፈፃፀም የገዙትን ቤት ለአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች ሉመልሱ አይገባም ብለናል።
የቤቱን የሐራጅ ሽያጭ ገንዘብ የስር የፍርድ ባለመብት የነበሩት የአሁን ሦስተኛ ተጠሪ አቶ ጌታቸው መንገሻ ለአንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች ሉመልሱ ይገባል ብለናል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።
በዚህ ችልት ውሳኔ መሰረት እንዱፈጸም ግልባጩ ለደራ ወረዲ ፍ/ቤት ይተላለፍ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል።
No topics extracted.