No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 25 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ላየን ሴኩሪቲ ኩባንያ - አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ጥላሁን ገ/እግዚአብሕር -ቀርቧል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የሥር ተከሳሽ ተጠሪ የሥር ከሣሽ ነበሩ። ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በጥበቃ ሰራተኛነት በአመልካች ድርጅት ሳገለግል ቆይቼ ምንም ሳላጠፊ ከሥራ አሰናብቶኛል ስለዚህ ወደ ሥራ ይመልሰኝ ይህ ካለሆነ የአንድ ወር ደሞዝና ላልች የስንብት ክፍያ ይከፈለኝ በማለት ጠይቋል።
አመልካችም በሰጠው መልስ ተጠሪ መጠጥ ጠጥተው ወደ ሥራ በመግባት አምቧጋሮ ይፈጥራለ፣ ከባልደረባቸው አይግባቡም በዚህም መሰረት የማስጠንቀቅያ ጽሐፍ ቢሰጣቸውም ሉታረሙ ባለመቻላቸው የ10 ቀን ደሞዝ ተቀጥተዋል ስለዚህ ስንብታቸው በአግባቡ ነው በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ መርምሮ ውሣኔ ሰጥቷል። በውሣኔውም አመልካች ተጠሪን ለማሰናበት ምክንያት ናቸው ሲል የገለፀው ወይም ያቀረበው ማስረጃ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው በተለይም በ8/7/2000 እና በ11/8/2000 ለተጠሪ የተፃፈት ማስጠንቀቂያ የሚጣረስ በመሆኑ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ የሕግ ድጋፍ የለውም። ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በመሆኑም የተጠሪ የ1 (አንድ) ወር ደሞዝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ክፍያን አስመልክቶ በተጠሪ ጥያቄ መሰረት እንዱከፈለው ሲል ወደ ሥራ የመመለስ ጥያቄን አልተቀበልኩም ሲል ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካችም በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኙን አቅርቧል። መዝገቡ የቀረበለት ፍ/ቤት የሥር ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሣይቀበለው ቀርቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው። አመልካች ጥር 13/2001 ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጡት ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው በማለት እንዱታረምለት ጠይቋል።
በዚህም መሰረት የሰበር ችልትም ተጠሪን በማስቀረብ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰምቷል። ጉዲዩ እንዱታይ የተወሰነውም አመልካች ክሱን ለማስተባበል ያቀረባቸው ምስክሮች ሣይሰሙ ውሳኔ የመሰጠቱን አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ የግራ ቀኙ ወገኖች ካሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ሲታይ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በጥበቃ ሥራ ተቀጥሮ በመስራት ላይ እያለ አመልካች ያለ ጥፊት አሰናበተኝ ስለዚህ ወደ ሥራ ይመልሰኝ ካልሆነም በሕግ የተቀመጠውን ይክፈለኝ ሲለ በጠየቁት መሰረት አመልካችም ተጠሪ ጥፊት በመፈፀማቸው ነው ያሰናበትኳቸው ሲል ተከራክሮ፤ ጉዲዩን ያየው የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ተጠሪ የፈፀሙትን ጥፊት አላስረዲም በማለት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ሲል ወደሥራ የመመለስ ጥያቄን ውድቅ በማድረግ የተለያዩ ክፍያ ለተጠሪ እንዱከፈለው ውሣኔ ሰጥቷል፤ የከፍተኛው ፍ/ቤትም ውሣኔውን ጉድለት የለበትም በማለት አፅንቷል።
እኛም ከላይ የተጠቀሰውን የውሣኔ አሰጣጥ መሰረት በማድረግ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሰምተናል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለውሣኔው መሰረት ያደረገው አመልካች ያቀረበው ማስረጃ በተለያዩ ጊዜ ለተጠሪ የተፃፈ ማስጠንቀቂያ የስንብቱን ምክንያት በአግባቡ የማያረጋግጥና የተጣረሰ (የሚጋጭ) ነው በማለት ነው። ስለ አመልካች የሰው ማስረጃም ቢሆን በውሣኔው ላይ የጠቀሰው ነገር የላለ እና መስማት የማያስፈልገው እንኳ ቢሆን የገለፀው ነጥብ የለም አመልካች በመከላከያው መልስ የሰው ምስክር እስከቆጠረ ድረስና የቀረበው የሰነድ ፅሁፍ በአግባቡ የተጠሪን ጥፊተኝነት የሚያረጋግጥለት ከሆነ አግባብነት ያለው ውሣኔ ለመስጠት ሲባል የአመልካችን ምስክር መስማትና ወደ ውሣኔ ሉመጣ ይገባ ነበር። ምክንያቱም የአመልካች የቀረበበትን ክስ የመከላከል መብቱ ሉታለፍ የማይገባው ህጋዊ ነጥብ ነው።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የቀረቡትን የሰው ምስክር ሣይሰማ ወደ ውሣኔ መድረሱ እና የከፍተኛው ፍ/ቤት ሣያርመው ማለፈ አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
በቀን 12/5/2001 የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን የሰው ምስክር በመስማት ይወሰን በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት መዝገቡን መልሰናል።
No topics extracted.
በዚህ ፍ/ቤት በመዝገብ ላይ ተላልፍ የነበረው የዔግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ለሚመለከተው ይጻፍ።
የግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።