No summary available.
ግንቦት 4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢት/መንገድች ባለሥልጣን - ነ/ፈጅ ጌታቸው አካሣ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ ትዔግሥት ወንድይፍራው - ጠ/ላቀ ቀረቡ።
አቶ ባህሩ አህመድ - በላለበት
በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ ክስ በሚሰማበት ቀጠሮ የከሣሽ /የይግባኝ ባይ/ አለመቅረብ የሚያስከትለውን ውጤት የሚመለከት ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች ከሣሽ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሣሾች ነበሩ።
በክሱም የአንደኛ ተጠሪ ንብረት የሆነውን መኪና ሁለተኛ ተጠሪ ሲያሽከረክሩ በግልገል ግቤ ወንዝ ላይ የተሰራው ድልድይ ላይ ጉዲት በማድረሣቸው ተጠሪዎች ለደረሰው ጉዲት ካሣ እንዱከፍለ ጠይቋል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ የከሣሽን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ አመልካች በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ ሲሆን የይግባኝ ቅሬታው መልስ ሰጪዎች ባለበት የሚጣራ ነጥብ በማግኘቱ ይግባኙን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ይግባኙ በሚሰማበት ዔለትም አመልካች ባለመቅረቡና የአንደኛ ተጠሪ ጠበቃም መዝገቡ እንዱዘጋላቸው ስለጠየቁ ፍ/ቤት መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት ዘግቷል። አመልካች የተዘጋው መዝገብ እንዱንቀሳቀስ እንዱፈቀድ አመልክቶ ፍ/ቤቱ በቂ ምክንያት አልቀረበም በሚል ጥያቄውን ሣይቀበለው ቀርቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። በቅሬታውም አንደኛ ተጠሪ የተከሰሰበትን ነገር ሣይክድ መዝገቡ እንዱዘጋ በመጠየቁ ብቻ መዘጋቱ ስህተት ነው፤ ለሁለተኛ ተጠሪ መጥሪያ መስጠት እንዲልተቻለ ለፍ/ቤቱ ተገልፆ የርሣቸው ጥሪ ጉዲይ በእንጥልጥል ላይ እያለ ጉዲዩን ለመስማት የሚያስችል ሁኔታ ሣይኖርና ሁለተኛ ተጠሪ በምትክ መጥሪያ ሣይጠሩ መዝገቡ መዘጋቱ ስህተት ነው፤ በቀጠሮው እለት ያልቀረብንበት በቂ ምክንያት እያለ መታለፈ ስህተት ነው፤ በማለት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ተሽሮ መዝገቡ ተከፍቶ እንዱታይ አመልክቷል።
ይህ ችልትም መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት የመዘጋቱን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ተጠሪዎች እንዱቀርቡ ታዘው ሁለተኛ ተጠሪ አልቀረቡም። አንደኛ ተጠሪ ቀርበው የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል። ከፍ ሲል የተገለፀው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል። በዚህ ጉዲይ ሉመለስ የሚገባው የይግባኝ ቅሬታው በሚሰማበት ቀን ይግባኝ ባይ /የአሁን አመልካች/ ያልቀረበ ቢሆንም አንደኛ ተጠሪ የይግባኝ ቅሬታውን ክደው ሣይከራከሩ መዝገቡ መዘጋቱ በአግባቡ ነው አይደለም?
የሚለው ነጥብ ነው።
ስለ ባለጉዲዮች ፍ/ቤት መቅረብና ሣይቀርቡ መቅረት በሚናገረው ምዔራፍ ውስጥ የሚገኘው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ቁጥር 73 ባንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንዱሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሣይቀርብ የቀረ እንደሆነ ተከሣሹ ቀርቦ የተከሰሰበትን ነገር በሙለ ወይም በከፉል ያመነ እንደሆነ ከሣሹ በላለበትም ቢሆን ፍ/ቤቱ ተከሣሽ ላመነው ጉዲይ ውሣኔ መስጠት እንደሚችል ተከሳሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን እንደሚዘጋውና ተከሣሹን እንደሚያሰናብት ይደነግጋል። በእርግጥ ይህ ድንጋጌ ከሣሽና ተከሣሽ እያለ የሚናገር ይሁን እንጂ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ በይግባኝ የሚቀርቡትንም ክርክሮች አጠቃል ስለሚይዝ እንደነገሩ አግባብ ከሣሽ የሚለው ቃል ይግባኝ ባይን ተከሣሽ የሚለው ደግሞ መ/ሰጪን የሚተካ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ ቁጥር 32/2/ ሥር ተመልክቷል። በመሆኑም የይግባኝ ቅሬታው በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ ይግባኝ ባይ ካልቀረበ ተፈፃሚነት ያለው ይኸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 ነው። በዚህ የሥነ ሥርዓቱ ድንጋጌ ደግሞ ይግባኙ በሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ ይግባኝ ባይ ያልቀረበ ከሆነ መ/ሰጪው ይግባኝ የቀረበበትን ነጥብ በከፉል ወይም በሙለ ካመነ በእምነቱ መሰረት ፍ/ቤቱ ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን ነገር ግን ይግባኙን ክድ የተከራከረ ከሆነ መዝገቡን መዝጋት እንዲለበት ተመልክቷል። በዚህም መሰረት የይግባኙ መዝገብ መዘጋት የሚወሰነው መ/ሰጪው ለቀረበበት የይግባኝ ቅሬታ ከሚሰጠው መልስ አኳያ ታይቶ ነው ማለት ነው። በመሆኑም መ/ሰጪ የቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ መካድ ማመኑ ሣይረጋገጥ መዝገቡ እንዱዘጋ በመጠየቁ ብቻ መዝገቡ ሉዘጋ የሚችልበትን ሁኔታ ድንጌጋው አያመለክትም። በመሆኑም የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአንደኛ መልስ ሰጪን መልስ ሣይመለከት መዝገቡን መዝጋቱ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
በልላ በኩል ከአመልካች አቤቱታ እንደተመለከትነው ሁለተኛ ተጠሪ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እንዱቀርቡ የተላከላቸውን መጥሪያ መ/ሰጪውን አግኝቶ መስጠት አለመቻለ ለፍ/ቤቱ ተገልፆለት ሁለተኛ ተጠሪ እንዱቀርቡ ምትክ መጥሪያ ሳይላክ በእንጥልጥል ላይ የነበረ መሆኑን ተረድተናል። ሁለተኛ ተጠሪ በዚህ ፍ/ቤትም ተጠርተው ያልቀረቡ በመሆኑ በዚህ ነጥብ ላይ የቀረበ ማስተባበያ የለም። በመሆኑም ሁለተኛ ተጠሪ በምትክ መጥሪያ እንዱጠሩ ፍ/ቤት ትዕዛዝ ሣይሰጥ አመልካች ይግባኝ በሚሰማበት ቀን አልቀረበም በማለት በሁለተኛ ተጠሪ ላይ የቀረበውን ይግባኝም አብሮ መዘጋቱ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት መዝገብ የሚዘጋው ይግባኝ ባዩ የይግባኝ ቅሬታውን ክድ ከተከራከረ በመሆኑ የአንደኛ ይግባኝ ባይ መልስ ተጠይቆ ሳይረጋገጥ መዝገቡ መዘጋቱም ሆነ ለሁለተኛ ተጠሪ መድረስ አለመቻለ ተገልፆ ሳለ በምትክ መጥሪያ እንዱቀርብ ሣይታዘዝ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሰረት መዘጋቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
የተዘጋው መዝገብ ተከፍቶ ነገሩ እንዱቀጥል ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል። ለመዝገብ ቤት ይመለስ።