No summary available.
ሚያዝያ 2ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- ገብረመስቀል ንጉሴ- ጠበቃው ቀርቧል ተጠሪ፡- አዱስ ልብስ ስፋት አ/ማ- ጠበቃው ቀርቧል።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የውል ግንኙነትን መሰረት የደረገ የገንዘብ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በመሐከላችን በተደረገው የመኪና ጥገና ውል መሰረት መኪናዬን ለጥገና ተረክቦ የነበረ ቢሆንም በአግባቡ ያልጠገነ በመሆኑ የከፈልኩትን የጥገና ስራ ዋጋ ይመልስልኝ፤ መኪናው ቶል ተጠግኖ ባለመመለሱ ለሰራተኞች ትራንስፖርት ወጪ ያደረግኩትንም ይተካልኝ በማለት ነው።
አመልካችም ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ በተገባው ውል መሰረት መኪናውን ጠግኜ በአግባቡ አስረክቤአለሁ፤
ከሣሽ መኪናውን ፈትሾ ከተረከበና ዋጋውንም ከከፈለ በኋላ ሲገለገልበት ቆይቶ ዋጋውን መልስ ሉለኝ አይችልም፤
ለሰራተኞች ትራንስፖርት ወጣ የተባለው ገንዘብም እኔን አይመለከትም በማለት በአንድ በኩል የተከራከረ ሲሆን፤ በልላ በኩል ደግሞ በውለ መሰረት መኪናውን በድጋሚ ተረክቤ የመለዋወጫ ዔቃዎችን ከውጪ ሐገር በመግዛት የሰራሁ ስለሆነና ከሣሽም በዚሁ ስለተስማማ ለመለዋወጫ ዔቃዎች ያወጣሁትን ገንዘብ ይተካልኝ በማለት የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ መሥርቷል።
ክሱን የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሁለቱን ወገኖች ካከራከረ በኋላ የተጠሪን ክስ ሙለ በሙለ ውድቅ በማድረግ አመልካች ያቀረበውን የክፍያ ጥያቄ ተቀብሎል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ባለመስማማቱ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም የተጠሪን ክስ በተመለከተ የተሰጠውን ውሣኔ ሲያፀና አመልካች ባቀረበው የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ መሰረት የተሰጠውን ውሣኔ ሽሯል። በዚህም አመልካች ለመለዋወጫ ዔቃዎች አወጣሁት ያለው ገንዘብ ሉከፈለው አይገባም ብሎል። በመጨረሻም አመልካች ይህን ውሣኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ውሣኔው ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዟል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ግንቦት 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች የተጠሪን መኪና /አውቶቡስ/ ሲጠግን ለመለዋወጫ ዔቃዎች ያወጣው ገንዘብ ሉከፈለው አይገባም የመባለን አግባብነት ለመመርመር ነው።
በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከላይ እንደተገለፀው የተከራካሪዎቹ ግንኙነት የተመሰረተው በውል ላይ ነው። አመልካች በውለ የገባው ግዳታ የተጠሪን አውቶቡስ /መኪና/ በጋራዡ ጠግኖ ለማስረከብ ነው። በዚህ መሰረትም ጠግኖ ለተጠሪ ከማስረከቡም በላይ፤
በውለ የተመለከተውን የጥገና ዋጋውንም ወስዶል። በልላ በኩል ደግሞ የአውቶቡሱ ርክክብ ከተፈፀመ በኋላም ተመልሶ ወደ ጋራዥ ገብቷል። አመልካችም በውለ በገባው የዋስትና ግዳታ መሰረት ነፃ የቴክኒክ አገልግልት በመስጠት መኪናውን ጠግኖ ለተጠሪ አስረክቧል። የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ የመሰረተውም በዚህ ጊዜ ለገጠማቸው የመለዋወጫ ዔቃዎች መግዣ ያወጣው ወጪ እንዱተካለት ነው።
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በተደረገው ውል የአመልካች ግዳታ የመለዋወጫ ዔቃዎችን በራሱ ወጪ ገዝቶ መግጠምን አያጠቃልልም። የመለዋወጫ ዔቃ ወጪ የሚሸፈነው በተጠሪ ነው። በእርግጥ ከብር 1ዐዐዐ /አንደ ሺህ ብር/ በላይ የሚያወጣ የመለዋወጫ ዔቃ ሲገዛ ተጠሪ መፍቀድ እንዲለበት በውለ ተመልክቷል። ይሁንና ተጠሪ አመልካች ላቀረበው የተከሣሽ ከሣሽነት ክስ በሰጠው መልስ የመለዋወጫ ዔቃዎቹ እንዱገዙ አልፈቀድኩም የሚል ክርክር እንዲላቀረበ በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ በግልጽ ተመልክቷል። የተባለት የመለዋወጫ ዔቃዎች በመኪናው ላይ አልተገጠሙም የሚል ክርክርም የለውም። ይልቁንም መኪናው ለሁለተኛ ጊዜ ጥገና ወደ ጋራዡ እንደገባ የክፍያ ጥያቄ እንደሚነሣ ያወቀና ይህንም ለአመልካች በፃፈው ደብዲቤ ገልጾ እንደነበር በፍ/ቤቱ ውሣኔ ላይ ተመልክቷል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ገንዘቡ ለአመልካች እንዱከፈል የወሰነው እነዚህን ምክንያቶች እግምት ውስጥ በማግባት እንደሆነም ተገንዝበናል።
No topics extracted.
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ እንዲየነው ፍ/ቤቱ አመልካች የመለዋወጫ ዔቃዎቹን አልገዛም ወይም ለመኪናው ጥገና አላዋላቸውም እሚል ድምዲሜ ላይ አልደረሰም። ገንዘቡ አይከፈልም ያለው ዔቃዎቹ የተገዙት ከተጠሪ ዔውቅና ውጪ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ብቻ ነው። ከላይ እንዲመለከትነው ተጠሪ ከኔ እውቅና ውጪ የተገዙ ናቸው የሚል ክርክር አላቀረበም። ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው ክርክርም በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ብቻ ሣይሆን፣ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በተደረገው ክርክርም የመለዋወጫ ዔቃዎቹ ከኔ እውቅና ውጪ የተገዙ ናቸው የሚል የመከራከሪያ ነጥብ አለማቅረቡን ነው ያረጋገጠው። በሰበር ችልት የተከራከረው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩ ባይቀርብለትም በይግባኝ ሰሚነት ስልጣኑ ትክክል የመሰለውን የመከራከሪያ ነጥብ በመያዝ አከራክሮ መወሰኑ ትክክል ነው በማለት ነው።
እንደምንመለከተው ተጠሪ የሚከራከረው ከአመልካች ጋር ያለውን የውል ግንኙነት መሰረት በማድረግ እንደመሆኑ ውለን መሰረት በማድረግ የሚቀርቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች አንስቶ ሉከራከር ይገባል። በራሱ በተጠሪም እንደታመነው የመከራከሪያ ነጥቡን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አላቀረበውም እንጂ ቢያቀርበውም ኖሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 329/1/ እንደተመለከተው ተቀባይነት የሚኖረው አልነበረም። በእርግጥ ፍ/ቤቱ የተባለውን ነጥብ በራሱ ማለትም በፍ/ቤቱ የተነሣ ሣይሆን፣ ተጠሪ በይግባኝ ማመልከቻው ገልጾት የነበረ እንደሆነ ነው በውሣኔው ላይ ያመለከተው።
ይህም የሚያሣየው ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 182/2/ በተደነገገው መሰረት የሰጠው ውሣኔ አለመሆኑን ነው።
ከሁለም በላይ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 329/1/ የተመለከተውን ክልክላ በማለፍ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያልተነሣን ክርክር መሰረት በማድረግ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወሣኔ የሚሰጥበት የሕግ አግባብ የለም። በያዝነው ጉዲይ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሉወስን ሲገባው ያልወሰነው ጉዲይ የለም። ከዚህ የተነሣም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.182/2/ አኳያ የሚያይበት የሕግ ምክንያት ነበር የሚባልም አይደለም። ስናጠቃልለው አመልካች ለመለዋወጫ ዔቃዎች መግዣ ያወጣው ገንዘብ ሉከፈለው አይገባም በሚል የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ የሕግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ