No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 345ዐ4 ሚያዝያ 6 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- አቶ አበባው የሺድንበር አልቀረቡም።
ተጠሪ፡- አቶ ካሣ በቀለ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የጉዲዩ መነሻ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዲ ፍ/ቤት መስከረም 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 14/95 በሆነው በ1ዐ/7/99 ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው እግድ ትዕዛዝ ስላልተነሳ በመዝገቡ ላይ ክርክር መቀጠል አልተቻለም ሲል መዝገቡን ዘግቷል። ይግባኝ የቀረበለት ከፍተኛ ፍ/ቤትም በመ/ በሆነው ጥቅምት 11 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት ብይኑን አጽንቶታል። እንደገና በይግባኝ የመረመረው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 44/2ዐዐዐ በሆነው መዝገብ ኀዲር 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት መልስ ሰጭ የሆነውን የአሁኑን አመልካችን ሳይጠራውና ሳያከራክር “ምንም እንኳን ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ባይፈቅድም” በማለት ተጠሪ ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከር የተሰጠ ውሣኔ የላለ በመሆኑ የመጀመሪያው ክስ ቢዘጋለትም እንደ ገና እንዱንቀሳቀስለት በተወሰነው መሰረት ክርክሩ እንዱቀጥል የተፈጠረው ስህተት ተስተካክሎል በማለት ውሣኔውን በመለወጡ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ታህሣሥ 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጽፍ ያቀረበው ቅሬታ ለተጠሪ ደርሶት ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
የተፃፈ መልስ አቅርቧል። አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
እኛም የግራ ቀኙን ክርክር በሕግ ረገድ በአጭሩ እንደሚከተለው መርምረናል።
በመሰረቱ በፍ/ቤቶች የተከራካሪ ወገኖች ማንኛቸውም አቤቱታና ቅሬታ በዲኝነት ላታይ የሚችለው በሕግ በተመለከቱ ሥርዓቶች ብቻ ነው። በተያዘው ጉዲይ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ምንም እንኳን የሥነ-ሥርዓት ሕጉ ባይፈቅድም በማለት በበታች ፍ/ቤቶች የተፈጠረውን ስህተት ለማረም የአሁኑን አመልካች ሳይጠራውና ሳያከራክረው የአንደኛውን ወገን ቅሬታና ክርክር ብቻ በመስማት ውሣኔ ላይ መድረሱ የአንደኛውን ወገን የመሰማት መበት የተጋፊና ከሥነ - ሥርዓት ሕግ ውጪ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 338/1/ ሥር በግልጽ እንደተመለከተው ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ያልሰረዘ እንደሆነ ይግባኙ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ መልስ ሰጭው ቀርቦ እንዱከራከር መደረግ እንዲለበት ተደንግጓል። ይህን በሕግ የተመለከተውን የመሰማት ሕገ-መንግሥታዊ መብት /the right to be heard/ ባልጠበቀ መልኩ የተሰጠው ውሣኔ በየትኛውም መመዘኛ ፍትሐዊና የሕግ መሰረት አለው ለማለት የሚቻልበት አግባብ የላለ በመሆኑ አንደኛውን ወገን ሳይጠራና ሳያከራክር የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 44/2ዐዐዐ በ13/3/2ዐዐዐ ዓ.ም. በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል። ይፃፍ።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 338/1/ መሰረት ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዱመለስ ብለናል። ይፃፍ።
ወጪና ኪሣራ የዚህ ፍ/ቤትን ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
የውሣኔው ግልባጭ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይተላለፍ ብለን መዝገቡን ዘግተናል።
No topics extracted.