No summary available.
ሚያዝያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሸራተን አዱስ- አቶ ኃይለ ንጋቱ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- እነ አቶ እያሱ- መገርሣ ቀረቡ በዚህ መዝገብና በሰበር መዝገብ የተያዘው ክርክር ተጣምረው መታየታቸው የበታች ፍርድ ቤት በሁለት የተለያዩ መዝገቦች የሰጠውን ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው መሆኑን ለመመርመርና ተገቢውን ውሣኔ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው በዚህ መዝገብ የቀረበውን ክርክር በሰበር መዝገብ ከቀረበው ክርክር ጋር መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የከፍተኛው ፍ/ቤት ላላ ችልት በመዝገብ ሰኔ 4 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው በመሆኑ በሰበር ታይተው ይታረሙልኝ በማለት ነሐሴ 13 ቀን 2000 ዓ.ም እና ነሐሴ 3 ቀን 2000 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታዎች በማቅረብ ሁለቱን መዝገቦች በማስከፈቱ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በከሳሽነት ቀርበው ተከሳሽ (የአሁን አመልካች) 1996 ዓ.ም ጀምሮ በዲቦና ኬክ አዘጋጅነት ቀጥሮ ሲያሰራን ቆይቶ ነሐሴ 19 ቀን 1999 ዓ.ም የስራ ውላችንን ያላንዲች ምክንያት ያቋረጠብን በመሆኑ የስራ ውለን አላግባብ በማቋረጡ የካሣና የስራ ስንብት ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት፣የሰርቪስ ቻርጅ ብር 2000(ሁለት ሺህ ብር)፣ በላሉት የሰራንበት፣ ቅዲሜና እሁድ የሰራንበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና የዓመት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ ከስድስት ወር ደመወዛችን ጋር ይከፈለን የሚል ክስ አቅርበዋል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ከስድስት ወር በፉት ያቀረቧቸው የተለያዩ የክፍያ ጥያቄዎች በይርጋ ይታገዲለ፤ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል የተረጋገጠ መብት የላቸውም ተብል ክሱ ውድቅ ይደረግልን በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ጉዲይ ረገድም ከሳሾች (ተጠሪዎች) የተቀጠሩት ለተወሰነ ጊዜ ነው፤ ስብሰባና ሰርግ ሲኖር እየተጠሩ ለተወሰነ ጊዜ የሰሩ ቢሆንም በተከታታይ ለሶስት ዓመት አልሰሩም፤ የሰርቪስ ቻርጅ እና የአዲሪ ክፍያ የሚከፈለው ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ስለሆነ ሉጠይቁ አይገባም፤ ቅዲሜና እሁድ ለመስራታቸው ማስረጃ አላቀረቡም በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ የሰማ ሲሆን አመልካች አንድ ምስክር አቅርቦ ምስክሩ ተጠሪዎች ስራ ሲበዛ ለማቃለል የተቀጠሩና ደካማ የስራ ውጤት በማሣየታቸው የተሰናበቱ መሆኑን የመሰከረ ሲሆን ተጠሪዎች ራሳቸው በምስክርነት ቀርበው ላልተወሰነ ጊዜ መቀጠራቸውንና በተከታታይ መስራታቸውን መስክረዋል። የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ መዝኖ የስራ ውለ የተደረገው ለተወሰነ ጊዜ ነው፤ ከሳሾች (ተጠሪዎች) ያቀረቡት የስራ ስንብት ክፍያ፣ የካሣ ክፍያና የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ተፈፃሚነት የለውም፤ ትርፍ ሰዓት መስራታቸውን ባለማስረዲታቸው ጥያቄቸው ተቀባይነት የለውም፤ የሰርቪስ ቻርጅ ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠረ ሰራተኛ ብቻ የሚከፈል መሆኑን ተከሳሽ (አመልካች) አላስረዲም፣ ይክፈል፤ የሁለት ዓመት ፈቃድ በገንዘብ ቀይሮ ይክፈል፤ የተለያዩ ክፍያዎች ከስድስት ወር በፉት ያለት በይርጋ ቀሪ ይሆናለ፤ የቅዲሜና እሁድ ክፍያ በይርጋ የማይታገደውን ይክፈል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች የራሱን የይግባኝ ቅሬታ ተጠሪዎች ደግሞ የራሳቸውን የይግባኝ ቅሬታ በማቅረብ ሁለት የይግባኝ መዝገቦች በማስከፈት ክርክር አድርገዋል። በመጀመሪያ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን የይግባኝ ቅሬታና የአመልካችን ክርክር በከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰማው ችልት ተጠሪዎች የተቀጠሩት ላልተወሰነ ጊዜ ነው፤ ስለሆነም የስራ ስንብት ክፍያ የካሣ ክፍያና የማስጠንቀቂያ ለእያንዲንዲቸው የሁለት ወር ክፍያ በሕጉ መሰረት ተሰርቶ እንዱከፈላቸው በማለት ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ወስኗል። አመልካች ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታና ተጠሪዎች ለይግባኙ የሰጡትን መልስ በመዝገብ ሰምቶ የወሰነው ላላው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ችልት ቅዲሜና እሁድ የሰሩ መሆኑን ተጠሪዎች ያላስረደ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ቅዲሜና እሁድ ለሰሩበት ይከፈላቸው ማለቱ ተገቢ አይደለም በማለት የቅዲሜና እሁድ ክፍያ ብቻ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ሰኔ 4 ቀን 2000 ዓ.ም ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልቶች በሁለቱም መዝገብ የሰጧቸው ውሳኔዎች መሰረታዊ ስህተት እንዲለባቸው በመግለጽ እነዚህን ሁለት የሰበር መዝገቦች አስከፍቷል። አመልካች በዚህ መዝገብ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠሩ ይቆጠራል በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት፤ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል ካሣና ላልች ክፍያዎች መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ያመለከተ ሲሆን፤ አመልካች በሰበር መዝገብ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የሰርቪስ ቻርጅ የሚከፈለው ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች ብቻ ሆኖ እያለ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) ይክፈል መባለ ተገቢ አይደለም፤ ስለዚህ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪዎች አመልካች በሁለቱም መዝገቦች ያቀረባቸውን የሰበር አቤቱታዎች በመቃወም መልስ ሰጥተዋል።
ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩና በተከታታይ ያለማቋረጥ ሲሰሩ እንደነበር የአመልካች ምስክር ገልጿል፤ ምስክሩ በስራ ድክመት ተባረሩ የሚል ቃል የሰጠ ቢሆንም ይህንን የሚደግፍ ማስረጃ አልቀረበም፤ የሰርቪስ ቻርጅ እንዱከፈለን መወሰኑ በአግባቡ ነው፤ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት በጽሐፍ ባቀረቧቸው መልሶች ተከራክረዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥ፣ የከፍተኛ ፍ/ቤት ሁለት የተለያዩ ችልቶች የተጠሪዎችንና የአመልካችን ይግባኝ መርምረው የሰጡት ውሣኔና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዲዩ ታይቶ የተወሰነበት ስርዓት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውና ይግባኝ ባዮች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ስለሆኑ የካሣ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ክፍያ እና ላልች ክፍያዎች እንዱከፈለ የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለት ጭብጦች እልባት ማግኘት ያለባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
ሆኖም የከፍተኛው ፍርድ ቤት በአመልካች ቅሬታ አቅራቢነት ከተከፈተው የይግባኝ መዝገብ በተጠሪዎች ቅሬታ አቅራቢነት ከተከፈተው የይግባኝ መ/ ጋር በፍትሀብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 11 ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት በማጣመር እንዱታይ ማድረግ ሲገባው ከአንድ ውሣኔ የተነሱ ሁለት ይግባኞች በሁለት የተለያዩ ችልቶች እንዱታዩ በመደረጋቸው እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና አንድ ላይ ሉፈፀሙ የማይችለ ሁለት ውሣኔዎች ተሰጥተዋል። የስነ- ስርአት ሕጉ በአንድ ዘንግ ከሚመደቡ ተከራካሪዎችና በአንድ ጭብጥ ላይ የሚቀርቡ ክርክሮች ተጣምረው እንዱታዩ የሚደነግገው በተመሣሣይ ጉዲይ እና ጭብጥ የተለያዩ ችልቶች የተለያየ ውሣኔ እንዲይሰጡ ለመከላከልና የስራ ቅልጥፍና እና የውሣኔ ወጥነትን ለማረጋገጥ ነው። በዚህ ጉዲይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለቱ የይግባኝ መዝገቦች ተጣምረው እንዱታዩ ባለማድረጉ ተጠሪዎች ይግባኝ ባለበት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽል የፍርድ ባለመብት የሆኑበት፣ አመልካች ይግባኝ ባለበት መዝገብ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽል ፍርድ ያገኘበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
የሁለቱን ችልቶች ውሣኔዎች በጋራ አይቶ ማስተካከያ ካልተደረገ በስተቀር እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና በአንድ ላይ ሉፈጸሙ የማይችለ ናቸው። ስለሆነም ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሥነ-ሥርአት ግድፈት ያለበት ነው።
አመልካች ለተጠሪዎች መክፈል የሚገባቸውን ክፍያዎች በተመለከተም የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የስራ ስንብት ክፍያ የካሣ ክፍያና የማስጠንቀቂያ ለእያንዲንዲቸው የሁለት ወር ደመወዝ በሕጉ መሰረት እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተጠሪዎች እንዱከፍል የወሰነውን የቅዲሜና እሁድ ክፍያ ብቻ በመሻር አመልካች ለተጠሪዎች ከመጋቢት 29 ቀን 1999 እስከ መስከረም 29 ቀን 2000 በወር ብር 2000(ሁለት ሺህ ብር) የሚታሰብ የሰርቪስ ቻርጅ ክፍያ፣ የሁለት ዓመት የዓመት ፈቃድ በገንዘብ ቀይሮ እንዱከፍል የሰጠውን ውሣኔ በራሱ ብቻውን ሲታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ ጉዲዩ በፍትሀብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 11 ንኡስ አንቀጽ 5 መሰረት ተጠቃልል ባለመታየቱ በሁለቱ መዝገቦች የተሰጡ ውሣኔዎች የተለያዩና እርስ በርስ የሚቃረኑ ከመሆናቸው ውጭ በይዘታቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለባቸው ናቸው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ከሰጠው ውሣኔ ጋር ተጣጥሞ ተፈፃሚ ላሆን በሚችልበት ሁኔታ በማጣመር አጽንተናል። ይፃፍ።
ተጠሪዎች የተቀጠሩት ላልተወሰነ ጊዜ ነው ብለናል። አመልካች የተጠሪዎችን የስራ ውል ያቋረጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎችን ሣይከተል ከሕግ ውጭ በሆነ መንገድ ነው ብለናል።
አመልካች የተጠሪዎችን ውል ከሕግ ውጭ በማቋረጡ፣
የዚህ ፍርድ ግልባጭ ተገልብጦ ከመዝገብ ጋር ይያያዝ። ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ሚያዝያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.