No summary available.
ሚያዝያ 6 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካቾች፡-
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሣውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር አመልካቾች ከሣሾች የነበሩ ሲሆን፣በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት የስራ ውላቸው ከሕግ ውጪ መቋረጡን በመግለጽ ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዱከፍላቸው በመጠየቅ ነው። ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ ከክፍያዎቹ አንደ የሆነው የፕሮቪደንት ፈንድ የተጠየቀው በሕጉ የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና ላልች የስረ-ነገር ክርክሮች በማንሳት ክሱ ይሰረዝ ዘንድ ጠይቆአል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ፣የስራ ውለ የተቋረጠው በአግባቡ ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል። በመቀጠልም ለከሣሾች ሉከፈል የሚገባው የስንብት ክፍያ ብቻ ነው፤ የካሣ እና የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያዎች ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም የበኩለን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ውሳኔውን አጽንቷል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካቾች ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ተጠሪ ቀደም ሲል ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ የፕሮቪደንት ፈንድ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኑ ወይም ማመኑ ተገልፆ እያለ የስር ፍ/ቤቶች የፕሮቪደንት ፈንድ አይከፈልም በማለት የሰጡትን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከስር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር በዝርዝር ተመልክተናል። ከዚህም መጀመሪያ የአሁኖቹ አመልካቾችን ጨምሮ 53 ሰራተኞች በተጠሪ ላይ ክስ እንደመሰረቱ እና ተጠሪ የበኩለን የመከላከያ መልስ ከሰጠ በኋላ የአሁኖቹ አመልካቾች ክስ ለብቻው ተነጥል እንዱታይ ስለታዘዘ በዚሁ መሰረት አመልካቾች ላላ ክስ ማቅረባቸውን ተገንዝበናል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ለመጀመሪያው ክስ በሰጠው መልስ(ሚያዝያ 7 ቀን 1997 ዓ.ም በተፃፈው) የፕሮቪደንት ፈንድ እና ላልች ክፍያዎች ለከሣሾች ሉከፈል እንደሚገባ እንደሚያምን በግልጽ ያመለከተ ሲሆን፣አመልካቾች ተነጥለው ለመሰረቱት ክስ በሰጠው መልስ ግን የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል መቃወሚያ ማቅረቡን ተመልክተናል።
ከፍ ሲል እንደተገለጸው የአመልካቾች ክስ ተነጥል እንዱቀርብ የታዘዘው በፍ/ቤቱ ነው። ፍ/ቤቱ ይህን ትእዛዝ ላሰጥ የቻለው የሁለቱ ሰራተኞች የስራ ውል የተቋረጠው ከላልች ሰራተኞች በተለየ ሁኔታ ነው በመባለ እንደሆነ ጠበቃ ሻምበል ተሾመ ደምሴ ቀረቡ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር ለመረዲት ችለናል። በአጠቃላይ ሲታይ ግን የፕሮቪደንት ፈንድ እና የላልች ክፍያዎች ጥያቄ የቀረበው በሁለም ሰራተኞች ነው። ተጠሪ በመልሱ ላይ ያመነውም ይህንኑ በአጠቃላይ ነው። በመሆኑም በስነ-ስርአት ሕጉ መሰረት ክርክሩን ለመለወጥ ይችል ዘንድ ጥያቄ አቅርቦ ሳይፈቀድለት እግረ መንገድ ባነሳው የይርጋ መቃወሚያ ተጠቃሚ ላሆን አይችልም። ለዚህ ሰበር ችልት ባቀረበው ክርክርም የይርጋ መቃወሚያ በአግባቡ አቅርቤአለሁ አላለም።
አጥብቆ የተከራከረው አመልካቾች የፕሮቪደንት ክፍያ ሉከፈላቸው ይገባል ብዬ መልስ አልሰጠሁም በማለት ነው። ይህ አባባለ ደግሞ ሚያዝያ 7 ቀን 97 ዓ.ም የሰጠውን ግልጽ የመከላከያ መልስ የሚቃረን ነው። ስለዚህም አመልካቾች የጠየቁት የፕሮቪደንት ፈንድ የማይከፈልበት የሕግ ምክንያት የለም። በዚህ ረገድ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
348/1/ መሰረት ተሻሽልአል።
አመልካቾች የጠየቁትን የፕሮቪደንት ፈንድም ተጠሪ ሉከፍል ይገባል ብለናል።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ይመለስ።