No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ልዐልሰገድ ቦኔ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ኢትዮ - ላዘር ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግል ማህበር - የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ሕግን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም የአሁኑ አመልካች ታኀሣሥ 23 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት የክስ ማመልከቻ ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ያቋቋሙት የስራ ቅጥር ውል ያላግባብ መቋረጡን ዘርዝረው የስድስት ወር ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነቱ ቀርቦ አመልካች ከስራ የተሰናበቱት የማታለልና የማጭበርበር ተግባር መፈፀማቸው በማጣራት ተረጋግጦ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም አመልካች ከስራ የተሰናበቱበት መንገድ በሕጉ አግባብ አለመሆኑን ዘርዝሮ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ካለ በኋላ ወደ ስራ ልመለስ ጥያቄን በተመለተ ግን የስራ ግንኙነቱ መልካም አይሆንም በሚል ምክንያት ባለመቀበል በምትኩ አመልካች የስድስት ወር ደመወዝ በካሣነት ተከፍሎቸው ከስራ እንዱሰናበቱ ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ በስር ፍ/ቤት አመልካች ካሣ ተከፍሎቸው ከስራ እንዱሰናበቱ የተሰጠው ውሣኔ የስራ ዋስትናን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑ በምክንያትነት ይዞ በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ ከሻረ የአመልካችን ወደ ስራ ልመለስ ጥያቄ አስመልክቶ ግን በግልጽ ዲኝነት አላሳረፈበትም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለማሻሻል ነው።
አመልካች ሐምል ዐ8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በፃፈት 2 /ሁለት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ የዲኝነት አሰጣጥ ተፈፀመ የሚለትን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔን ሲለውጥ ለአመልካች የሚገባውን ዲኝነት በግልጽ ያልጠቀሰ በመሆኑ ይኸው ታርሞ የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍልኝ ወደ ስራ እንድመለስ ይወሰንልኝ በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም ለሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርቦ መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል። ተጠሪ የአመልካች ጥያቄ ለሰበር ችልቱ ላቀርብ የማይገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 2ዐ8 መሰረት ውሣኔው በሰጠው ፍ/ቤት ሉስተናገድ ይገባ የነበረ ነው በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የአመልካች ጥያቄ ለሰበር ችልቱ መቅረቡ ሥነ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ነው?፣ሥነ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ነው ከተባለስ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ከሻረው በኋላ በአመልካች ወደ ስራ እንድመለስ ይወሰንልኝ የዲኝነት ጥያቄ ላይ ግልጽ ውሣኔ ሣያሣርፍ ማለፈ ተገቢነት አለውን? የሚለት ነጥቦች በጭብጥነት ሉታዩ የሚገባ ሁነው አግኝተናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ፡- ጉዲዩ መሰረት ያደረገው አዋጅ ቁጥር 377/96 ዓ.ም ሲሆን ይህንኑ አዋጅ መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ክርክሮች የሚመሩት በ1958ቱ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ እና በአዋጁ በተመለከቱ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የስራ ክርክርን የማየት የዲኝነት የሥረ ነገር ሥልጣን ከተሰጣቸው አካላት አንደ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን በቁጥር 138 መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማየት የጀመረው የስራ ክርክር ውሣኔ ካገኘ በኋላ በይግባኝ የሚታየው በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ችልት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 139 ድንጋጌ ያሣያል። ይህ የሥራ ክርክር ይግባኝ ሰሚው ችልት በጉዲዩ ላይ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ አንቀጽ 139 በንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስር አስቀምጧል። የስራ ክርክር ይግባኝ ሰሚ ችልት በሚሰጠው ውሣኔ ላይ ቅሬታ ያለበት ወገን አቤቱታውን ሉያቀርብ የሚችለው በሰበር ሥርዓት ነው።በመሆኑም በስራ ክርክር ችልት የተሰጠ ውሣኔ ሉፀና፣ ሉለወጥ ወይም ሉሻሻል የሚችልበት ሥርዓት ይኸው ስለመሆኑ በቀላለ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ከዚህ አጠቃላይ የይግባኝ ቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት ወጪ ጉዲዩን የተመለከተው ፍ/ቤት ጉዲዩን እንደገና የሚያስተናግድበት ሥርዓት በሥነ-ሥርዓት ሕጋችን ተመልክቷል።
ከእነዚህ ሰርዓቶች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 2ዐ8 ሥር የተመለከተው ስህተት የሚታረምበት ሥርዓት ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አቤቱታ የቀረበለት ውሣኔው የሰጠው ፍ/ቤት ሉያርም ወይም ሉያስተካክል የሚችለው በሰጠው ውሣኔ እና ትእዛዝ ላይ የአፃፃፍ ስህተት፣የቁጥር አፃፃፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት መኖሩን ካረጋገጠ ብቻ ነው ስለሆነም በክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ላይ አከራክሮ የሰጠውን ውሣኔ ስህተትን ማረም ወይም ማስተካከል በሚል መነሻ ውሣኔውን ሉያሻሽል ወይም ሉለወጥ አይችልም። የክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ላይ ክርክር ተካሂድ ውሣኔ ከተሰጠ እና በዚሁ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን አቤቱታ ሉያቀርብ የሚገባው ለበላይ ፍ/ቤት ነው። በያዝነው ጉዲይም አመልካች ቅሬታ አድሮባቸው ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡት የስር ፍ/ቤት ወደ ስራ ልመለስ ጥያቄአቸውን ሣይቀበለው ቀርቶ በሕጉ በአማራጭ የተቀመጠውን መፍትሕ /relief/ በመወሰኑ ሁኖ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የስር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ሽሮታል።ሆኖም በአመልካች የተጠየቀውን ዲኝነት በግልጽ አልጠቀሰም። ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 2ዐ8 መሰረት ሉታረም ወይም ሉስተካከል ይገባ የነበረ ለማለት የሚቻል አይደለም። ይልቁንም በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠበት በፋ/ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 1ዐ/1/ መሰረት ለሰበር ችልቱ ቀርቦ ሉስተናገድ የሚገባ መሰረታዊ የክርክር ነጥብ ነው ስለሆነም የተጠሪ ጠበቃ በዚህ ረገድ ያቀረቡት መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው ሆኖ ባለማግኘታችን አልፈነዋል።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ፡- ፍርደ የክርክሩን ሂደት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮችን ባጭሩ መያዝ እንደአለበት፣ ለአፈፃፀም የማያስቸግር መሆን የአለበት ስለመሆኑ ስለፍርድ አሰጣጥ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተመለከቱት ድንጋጌዎች መንፈስ የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው። ፍርደ የሚፈፀመውን ክፍል በግልጽ ካላመለከተ በፍርድ መፍትሕ /relief/ የመሰጠቱን ዓላማ የሚያጓድለው ይሆናል። ስለሆነም አንድ ፍርድ ሲሰጥ የውሣኔ አፃፃፍ ይዘትና ቅደም ተከተልን መሰረት ያደረገ ከክርክሩ ሂደት እስከመደምደሚያው የያዘው ነገር ግልጽ መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ ያለው የፍርድ አፈፃፀም አካሄድ የተሟላ ነው ለማለት አይቻልም። በያዝነው ጉዲይም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ ተገቢ አለመሆኑን በምክንያት አስደግፍ ከሻረው በኋላ በይግባኝ ደረጃ እንዱወሰን በአመልካች የተጠየቀውን ዲኝነት በግልጽ ሣያሰፍር ማለፈ በፍርድ መፍትሕ የመስጠቱን ዓላማ ያጓደለና የውሣኔውን አፈፃፀም አስቸጋሪ የሚያደርገው ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በፍርደ ላሰጥ የሚገባውን መፍትሕ በተመለከተ በግልጽ አለመጥቀሱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ ስለተገኘ ሉታረም የሚገባው ነው። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 6ዐ794 ሚያዝያ 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል። ይፃፍ።
በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43/5/ መሰረት ተጠሪ ለአመልካች የአንድ ዓመት ደመወዝ ከፍል ወደ ስራው ይመልስ ብለን ወስነናል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.