No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- መሐመድ ሰዓዲይ ረጃ - ጠበቃ አበራ ጣሰው ቀርበዋል ተጠሪዎች፡- 1/ አቶ ዓብደልቃድር መሐመድ ፈረጅ - ቀርበዋል 2/ የህፃን ፉልሚያጀላኒ ሞግዚት ሻ/ሸዋነሽ አሰጋኸኝ - አልቀረቡም 3/ አቶ ሙክታር መሐመድ ፈረጅ - አልቀረቡም 4/ የአቶ ማሕሙድ መሐመድ ፈረጅ ወራሾች - አልቀረቡም 5/ ወ/ሮ ጀሚላ ጁሃር መሐመድ - አልቀረቡም 6/ ወ/ሮ ዘምዘም መሐመድ ፈረጅ - አልቀረቡም 7/ ወ/ሮ አለማ መሐመድ ፈረጅ - አልቀረቡም ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥቷል።
ይህ የሰበር ክርክር ላቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታቸው የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሰ/መ/ቁ. 22ዐ79፣ ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይሻርልኝ በማለታቸው ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በመቀላ ከተማ፣ የደቡብ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍ/ቤት በተካሄደው ክርክር የአሁኑ ተጠሪዎች ከሣሾች የአሁኑ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ የነበሩ ሲሆን ስር ከሣሾቹ ጥቅምት 28 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ ክስ ያቀረቡ ሲሆን አጭር ይዘቱም ሰኔ 15 ቀን 1998 ዓ.ም የተደረገው ውል ሕጋዊ ስላልሆነ እንዱፈርስና በተከሣሾቹ እጅ በዚሁ ምክንያት የገቡትን ቤቶች ይመለሱልን የሚል ነው።
ተከሣሹም ባቀረቡት ተቃውሞ እርሣቸውም ሆነ ከሣሾቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልልች እንዱሁም በውጭ አገር የምንኖር ስለሆነ በአዋጅ 25/88 ዓንቀፅ 5/2/ መሰረት ክርክሩን የመዲኘት ስልጣን ያለው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንጂ የከተማው ወረዲ ፍ/ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም ብለዋል።
ከሣሾችም በጠበቃቸው በኩል ከላይ ለሰፈረው ተቃውሞ ታህሣሥ 23 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ መልስ የሰጡበት ሲሆን ይዘቱም ምንም እንኳ ከሣሾች በተለያዩ ክልልች የሚኖሩ ቢሆንም ውለ የተፈፀመው እና አከራካሪው የማይንቀሣቀስ ንብረት የሚገኘው በመቀላ ከተማ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን አለው፤ አዋጅ ቁ. 25/1988 ዓንቀፅ 5/2/ በውል ላይ በተመሰረተ ክርክር አይደለም፤ ተቃውሞው ውድቅ ላሆን ይገባል የሚል ነው።
የሥር ወረዲ ፍርድ ቤቱም የቀረበው ተቃውሞና መልስ ከላይ ከተመለከተው የአዋጁ ይዘት በማገናዘብ ጉዲዩ የፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ስለሆነ ክርክሩን የማካሄድ ስልጣን የለኝም በማለት ጥር 14 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችልት ብይን ሰጥቷል።
ስር ከሣሾቹ ከላይ በሰፈረው ብይን ቅሬታ በማሣደር ወደ መቀላ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ክርክር ከተካሄደ በኋላ ፍ/ቤቱ ሚያዚያ ዐ5 ቀን 1999 ዓ.ም በሰጠው ብይን ክርክር የተነሣበት ቤት በመቀላ ከተማ የሚገኝ በመሆኑ እንዱሁም ውለ የተፈፀመው በዚሁ ከተማ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 24/1/ እና 25/1/ሀ/ መሰረት ስልጣን አለው በማለት የስር ፍ/ቤት ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
ጉዲዩ በስር ተከሣሹ ይግባኝ አቅራቢነት በትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የታየ ሲሆን ይህ ፍ/ቤትም በፍ/ይ/መ/ቁ. 2ዐ127፣ ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ የወረዲ ፍ/ቤቱ ስልጣን የለኝም የሚል ብይን ከሰጠ በኋላ ስር ከሣሾቹ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 245/3/ መሰረት ክሣቸውን አሻሽለው ወደ ወሰነው ፍ/ቤት ወይም ወደላላ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚፈቅድ ሆኖ እያለ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ የወረዲውን ብይን መሻሩ ተገቢነት የለውም በማለት የወረዲ ፍ/ቤቱ የሰጠውን ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ሽሮታል።
በዚህ የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ ቅሬታ በማሣደርም ስር ከሣሾቹ ጉዲዩን ወደ ትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ያቀረቡት ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከረ በኋላ በመ.ቁ. 22ዐ79፣ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም በሰጠው ፍርድ ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ብይን ለመሻር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 245/3/ አጣቅሶ ከሣሾቹ ክሣቸውን አስተካክለው ለሚመለከተው ፍ/ቤት ያቀርባለ እንጂ ይግባኝ ማለት አልነበረባቸውም ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደሆነና ስር ከሣሾቹ ይግባኝ ከማቅረብ በሕግ አይከለከለም በማለት የጠቅላይ ፍ/ቤቱን ውሣኔ ሙለ በሙለ በመሻር የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ብይን አጽንቷል።
የአሁኑ አመልካችም ከላይ የሰፈረውን የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይታረምልን በማለት መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ አቅርበዋል፤
መሰረታዊ ይዘቱም የቀረበው ክስና ተቃውሞ በአዋጅ ቁ. 25/1988፣ ዓንቀጽ 5/2/ መሰረት በፋዳራል ፍ/ቤቶች የሚታይ እንጂ በክልል ፍ/ቤት አይደለም፤ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 245 አተረጓጎም ረገድ የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ይግባኝ ችልት ስህተት ፈጽሟል ብል ማረም ቢችልም ለመሰረታዊ የክርክራችን ነጥብ የሰጠው መልስ የለም፤ ስለሆነም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል የሚል ነው።
ተጠሪዎችም ሐምል 29 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል፤ ይዘቱ ሲታይም እየተከራከሩበት ከመጡት ክርክር ያልተለየ በመሆኑ ደግሞ መዘርዘር ሣያስፈልግ ታልፎል።
ይህ ፍርድ ቤትም የግራና ቀኙ ወገኖች ክርክር አመጣጥ ከላይ እየተዘረዘረ በመጣው መልኩ በመገንዘብ ፣ በክሱ የተመለከተውን ጭብጥ የመዲኘት ስልጣን ያለው የትኛው ፍርድ ቤት ነው? የክልለ ፍርድ ቤት ወይስ የፋዳራል ፍ/ቤት? የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል።
ከክርክሩ መረዲት እንደተቻለው ተከራካሪ ወገኖች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በተለያዩ ክልልች እንዱሁም ከኢትዮጵያ ውጭ እንደሚኖሩ ነው፤ ግራ ቀኙ ወገኖችም በዚህ ነጥብ የሚካካደ አይደለም። አመልካቹ እያቀረቡት ያለው ክርክር ነዋሪነታቸው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልልች በሆኑ ሰዎች መካከል የሚደረግ ክርክር በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 ዓንቀጽ 5/2/ መሰረት ጉዲዩን የመዲኘት ስልጣን ያላቸው የፋዳራል ፍርድ ቤቶች ናቸው የሚል ሲሆን ተጠሪዎቹ ደግሞ አከራካሪው ጉዲይ በመቀላ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ቤት የሚካሄድ ስለሆነና ውለም የተፈፀመው በዚሁ ከተማ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 24/1/ እና 25/1/ሀ/ መሰረት ክርክሩን የመዲኘት ስልጣን ያለው አራካሪው ቤት ባለበት የተቋቋመው የመቀላ ደቡብ ወረዲ ፍርድ ቤት እንጂ የፋዳራል ፍርድ ቤት አይደለም ባይ ናቸው። አዋጅ ቁጥር 25/1988 የፋዳራል ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም ብቻ ሚናው የታጠረ አይመስልም፤ከዚህም አልፍ በፋዳራል ፍርድ ቤቶችና በክልለ ፍርድ ቤቶች መካከል ስልጣን የሚደለድል መሰረታዊ ሕግ ነው። በዚህ አዋጅ ዓንቀጽ 5/2/ መሰረት ነዋሪነታቸው በተለያዩ የክልል መስተዲድሮች በሆኑ ሰዎች መካከል የሚካሄድ ክርክር የሚስተናገድው በፋዳራል ፍርድ ቤቶች ነው በማለት በግልጽ ያስቀምጣል። ይህ መሰረታዊ ይዘት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ውስጥ በዓንቀጽ 24/1/ እና 25/1/ሀ/ እንደተመለከተው አከራካሪው የማይንቀሣቀስ ንብረት በአንድ ክልል ስለተገኘ ብቻ ወይም ውለ የተፈፀመው በአንድ ክልል በመሆኑ ብቻ ጉዲዩ የክልል ፍርድ ቤቶች ተፈጥሯዊ ስልጣን እንዱኖራቸው የሚያደርጋቸው አይደለም፤ ስለሆነም በመጀመሪያ ከስረ -ነገር ስልጣን አኳያ አከራካሪው ጉዲይ ሲታይ የፋዳራል ፍርድ ቤት ስልጣን መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፤ ፋዳራል ፍርድ ቤቶችም ስልጣናቸው በሆኑ ጉዲዮች በእያንዲንደ ክልል በቀጥታ መዋቅራቸውን ዘርግተው ወይም ደግሞ ለሚመለከተው የክልል ፍ/ቤት ውክልና በመስጠት ዲኝነት እንደሚሰጡ ነው። ስለሆነም የመቀላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱሁም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አከራካሪው ቤት በመቀላ ከተማ በደቡብ ወረዲ በመገኘቱ ብቻ ወይም ውለ በዚሁ አካባቢ በመደረጉ ወይም የሚፈፀም መሆኑን ብቻ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአዋጅ ቁጥር 25/88 ዓንቀጽ 5/2/ የተመለከተውን ድንጋጌ ተፈፃሚ እንዲይሆን ስለሚያደርግ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆነው ተገኝተዋል፤ ስለሆነም የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. ዐ4156፣ ሚያዝያ ዐ5 ቀን 1999 የሰጠው ብይን እንዱሁም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ. 22ዐ79 ጥር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል፤ ይፃፍ።
በመቀላ ከተማ፣ የደቡብ ወረዲ ፍ/ቤት
No topics extracted.