No summary available.
መጋቢት 03 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ ወኪል - ክብሮም አስመላሽ - ጠበቃ ካላዩ መሃሪ -ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የአቶ ገ/ኪዲን እንግዲ - ወኪል ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዲን - ጠበቃ ገ/አምላክ - ገ/ጊዮርጊስ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የሥነ-ሥርዓት ሕግን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ አመልካች መጋቢት 01 ቀን 1995 ዓ.ም በፃፈት የክስ ማመልከቻ ግምቱ ብር 1500.00 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ የሆነ በመቀላ ከተማ ደቡብ ወረዲ ጣቢያ አድነት ውስጥ የሚገኝ በምስራቅ 533፣በምዔራብ አደባባይ፣ በሰሜን 530፣ በደቡብ 534 የሚያዋስነው ፣ ስፊቱ በካሬ 600/ስድስት መቶ/ የሆነ የሟች አባታቸው ባሻይ አብርሃ ኪዲኑ ይዞታ በመሆን ከ1960 ዓ.ም ግብር የገበረበት ቦታ መኖሩን በዚህ ቦታ የአሁኑ ተጠሪ በነባር ይዞታነት ይገባኛል ብለው በቓልህ ትግራይ ጋዜጣ በ15/04/1995 ዓ.ም ተራ ቁጥር 755 በስማቸው ተጠንቶ መውጣቱን አመልካች ቦታውን በተመለከተ የይገባኛል ጥያቄ ለሚመለከተው የአስተደደር አካል ቢያቀርበም በመቐለ ዞን ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ /354/94 በቀን 22/5/1995 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ጉዲዩን በፍርድ ጨርሰው አንዱቀርቡ ማዘዙንና የሟች አባታቸው ወራሽ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ዘርዝረው የቦታው ግማሽ 300 ካ.ሜ እንዱሰጣቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ ተጠሪ ላይ በመቀላ ደቡብ ወረዲ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ ተጠሪም በተከሣሽነታቸው ቀርበው በሰጡት መልስ በከሣሽ ክስ የተቀመጠው በመቓልሕ ትግራይ ጋዜጣ ከወጣው ጋር የማይገናኝ እና በጉዲዮ ላይ ተከራክረውበት ውሣኔ ተሰጥቶ ተከፊፍለው በየግል ይዘው እንደሚገኙ ገልፀው በክሱ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው ተከራክረዋል ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በቃል በሰማበት ወቅት ከሣሽ እየጠየቁ ያለት ስለተከፊፈለት ሣይሆን ስለነባር ይዞታ መሆኑን መግለፃቸውን ተቀብል ተገቢውን ማጣራት ከአደረገ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በመቓልሕ ትግራይ ጋዜጣ ተራ ቁጥር 755 በቀን 15/04/1995 ዓ.ም በአሁኑ ተጠሪ ስም ተጠንቶ የወጣ ቦታ ለአመልካችም በአባተቸው ድርሻ ግማሽ 300 ካ.ሜ ሉደርሳቸው ይገባል በማለት ወስኗል በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለመቀላ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ይኸው ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ ሲያፀና ተጠሪ ጉዲዩን በድጋሚ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ይኸው ፍ/ቤትም የወረዲውን ፍ/ቤት ውሳኔ በማጽናት ይግባኙን ሰርዞታል። ከዚህ በኋላ ተጠሪ አቤቱታቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ችልቱ የበታች ፍ/ቤቶች በተጠሪ በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያለፈት ከሥነሥርዓት ውጪ መሆኑን በምክንያትነት በመያዝ ጉዲዩ በፍርድ ያለቀ ነው ሲል የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ሽሯል የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የሰበር ችልት ውሣኔ ባለመስማማት በመቃወም ነው።
የአሁኗ አመልካች መጋቢት 24 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 5/አምስት / ገጽ የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ውሣኔ መሰታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቦታ በፍ/መ/ቁ 2/90 አዋሣኙ ከተጠቀሰው የተለየ ስለመሆኑ የዞኑ እና የወረዲ ፍ/ቤቶች አጣርተው በወሰኑት ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 ከሚደነግገው ውጭ ጉዲዮ በፍርድ ያለቀ ነው ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ነው በማለት ዘርዝረው የክልለ ሰበር ችልት ውሣኔ ተሽሮ ላልች ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ እንዱፀናላቸው ዲኝነት መጠየቃቸቸውን የሚያሣይ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቅሬታ ነጥቦች ተቀባይነት የላላቸው የክልለ የሰበር ችልት ውሣኔ አግባብነት ያለው ስለመሆኑ ዘርዝረው ውሣኔው ሉፀና ይገባል ሲለ በ22/01/2001 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ ማመልከቻ ተከራክረዋል። አመልካች በበኩላቸው ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የፃፈት የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዮ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የፁሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው ዓብይ ጭብጥ ለክሱ መሰረት የሆነው ጉዲይ በመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች መጋቢት 01 ቀን 1995 ዓ.ም በፃፈት ክስ አዋሣኙንና ስፊቱን የገለፁበት ቦታ ቀደም ሲል በወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ ከተጠቀሰውና እኩል እንዱካፈለ በ07/05/1991 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ከወሰነው ቦታ ጋር ተመሣሣይ ስለመሆኑ ነው። ይህ ስለመሆኑም የወረዲው እና የዞኑ ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ሲሆን ፍ/ቤቶች የተጠሪን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ያደረጉበት ምክንያት አመልካች በክስ ማመልከቻ ላይ የጠቀሱት አዋሣኝና ስፊት በመ/ቁ 2/90 የተወሰነውን የሚመለከት ቢሆንም ክሱ ሲሰማ በጋዜጣው ላይ የወጣውን ቦታ ስለመሆኑ በመግለፃቸውና በፍሬ ነገር ክርክር ወቅትም በማስረጃ ተጣርቷል በሚል ነው።
በመሰረቱ የፍትሐብሕር የክርክር አመራር ሥርዓት ዓይነተኛ ዓላማ የክርክርን ሂደት ለማቀላጠፍና አንድ ደረጃ ላይ ሉደርስ መቋጫ ለማበጀት መሆኑ ይታመናል። የፍትሐብሕርን ክርክር አንድ ደረጃ ላይ ሲደርስ እልባት እንዱደረግበት በማቀድ ከተደነገጉት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ጽንሰ ሐሣቦች አንድ የመጨሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች /Res judicata/ የሚለው ሲሆን ይህ ጽንሰ ሀሣብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 5 ስር በግልጽ ተቀምጧል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዲዮች ማለት በማናቸውም መልክ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ቀርበው የመጨረሻ ውጤት ያገኙ ጉዲዮችን የሚሸፍን መሆናቸውንና በፍርድ፣ በብይን፣በውሣኔ፣ በትእዛዝ፣ ወይም በጊዜያዊ አገልግልት ባለው ትእዛዝ የመጨረሻ ውጤት አግኝተው በልላ መልክ ለመንቀሣቀስ የማይችለ የክርክር ነጥቦችን ሁለ የሚያጠቃልል ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 ስር በተመለከተው አኳኋን አንድ ጉዲይ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት መረጋገጥ ካለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ቀደም ሲል ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የነበሩ ጉዲዮች በድጋሚ በቀረበው ክስም ላይ በቀጥታ በፍሬ ነገር ጭብጥ ሆነው መቅረባቸው፣ ቀደም ሲል የነበረውን ክርክር አሁን በክርክር ተሣታፉ በሆኑ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወይም ተላልፍላቸው በነበረ ወገኖች መሆኑንና እነዚህ ጉዲዮች ቀደም ሲል በተካሄደው ሙግት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈባቸው መሆኑን ነው።
ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመጨረሻ ፍርድ መቃወሚያነት ሲቀርብ ተቀባይነት የሚኖረው ይኸው ጉዲይ በድጋሚ በቀረበው ክርክር ላይ መቅረቡ ሲረጋገጥ ነው ቀጥተኛ የፍሬ ነገር ጭብጥ የሚለው ሐረግ አጠቃላይ ይዘቱ ሲታይም በመጀመሪያው ክርክር ላይ ከአንደኛው ወገን ተጠይቆ በልላኛው ወገን የተካደ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታመነና በዚሁ ላይ የፍርድ ውሣኔ ያረፈበት የክርክር ነጥብ መሆኑን መገንዘብ አያዲግትም በመሆኑም በድጋሚ በቀረበው ክስ በቀድሞው ክርክር ተሣታፉ በነበሩ ወገኖች ወይም ከእነሱ መብት በተላለፈላቸው ወገኖች የሚካሄድ መሆኑና በሁለተኛው ክስም የተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመጀመሪያው ጋር ተመሣሣይ ሆኖ የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት መሆኑ ከተረጋገጠ እንዱሁም ጉዲዩ የመጨረሻ ፍርድ አርፍበታል የሚል ተቃውሞ በተከራካሪ ወገን ከተነሣ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 እና 244(2) ድንጋጌዎች የምንገነዘበው ነጥብ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች በ01/07/1995 ዓ.ም ለወረዲው ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አዋሣኙና ስፊቱ የተጠቀሰው ቦታ በመ/ቁ 2/90 በፍርድ ያለቀ በፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረትም ግራ ቀኙ ተከፊፍለው በየግላቸው የያዙት መሆኑን በሁለቱም የበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው ከወረዲ ፍ/ቤት እስከ ክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተቀባይነት ያጣው አመልካች በክሱ ላይ አዋሣኙን የጠቀሱት ቦታ በፍርድ ያለቀ መሆኑ ቢረጋገጥም በቃል ክርክር ወቅት በጋዜጣው የወጣውን ይዞታ የሚመለከት መሆኑን ስለገለፁና ይህም ቀደም ሲል በፍርድ ካለቀ ጉዲይ የተለየ መሆኑን በተደረገው ማጣራት ተረጋግጧል በማለት መሆኑን ከላይ ገልፀናል እንግዱህ አመልካች በአቤቱታ ፁሐፊቸው አዋሣኙን የጠቀሱት ቦታ ውሣኔ ያገኘ መሆኑ አከራካሪ አይደለም አከራካሪው ነጥብ በክሱ መሰማት ወቅት በአቤቱታ ጽሐፍቸው የጠቀሱት ሣይሆን በጋዜጣው የወጣው መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል በሚል ተቀባይነት ማግኘቱ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን ያለመሆኑ ነው።
እንደሚታወቀው የአቤቱታ ፁሐፍች የሚመሩት በሥነ-ሥርዓቱ በተመለከተው ሥርአት መሰረት ነው። ህጉ ይህን ያደረገበት መሰረታዊ ዓላማም የፍርድ ሂደቱን ለማቀላጠፍ በተቻለ ፍጥነት እልባት ለመስጠት ነው ። የአቤቱታ ጸሐፉዎች የሚመሩበት ሥርአት መኖር ተከራካሪ ወገኖች ክስ በቀረበበት ጉዲይ ላይ በሚያዘው ጭብጥ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ብቻ እንዱያተኩሩ የሚረዲቸው ይሆናል። በልላ በኩል የአቤቱታ ጽሐፈች ሥርአት ባለው መልክ እንዱቀርቡ ማድረግ ፍ/ቤቱ የክርክሩን ጭብጥ ለመመሥረትም ያግዘዋል፤ በመሆኑም በአቤቱታ ጽሁፍ ላይ ያልተገለፀ ፍሬ ነገር ፍርድ ቤቱ ጭብጥ የሚመሰርትበት አይሆንም። ጭብጥ ባልተመሰረተባቸው የክርክር ነጥቦች ላይ ደግሞ ክርክሩ በሚሰማበት ወቅት ማስረጃ ላቀርብባቸው አይችልም። ምክንያቱም ማስረጃ የሚሰማው በተጠየቀው ጥያቄ ወይም በቀረበው የመከላከያ መልስ ላይ በግልጽና በዝርዝር በቀረቡት ነጥቦት ላይ ብቻ ነው፤ ሆኖም ፍ/ቤቱ የነገሩን ሁኔታ መርምሮ ላላኛው ወገን ክሱን ወይም መልሱን እንዱያሻሽል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 91 እና 251 ድንጋጌዎች በተመለከተው መሰረት ሉያዝ ይችል ይሆናል።
ከዚህ የሥነ-ሥርዓት አካሄድ ውጪ በአቤቱታ ፁሐፍ የተገለፁትን ፍሬ ነገሮች በመተው በቃል ክርክር ወቅት የተገለፀውን ፍሬ ነገር መሰረት በማድረግ በልላ ተከራካሪ ወገን የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ማድረግ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ ነው የሚባልበት የክርክር አመራር ሥርዓት ምክንያት የለውም በተያዘው ጉዲይም አመልካች በአቤቱታ ጽሐፊቸው ላይ የጠቀሱትን ነገር በቃል ክርክር ወቅት አለመሆኑን ገልፀዋል ተብል የክስ አቤቱታውን ባላሻሻለበት ሁኔታ ተቀባይነት ማግኘቱ፤ የአቤቱታ ጸሐፉዎች የሚመሩበትን ሥርዓት ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ ተገኝቷል፤ በመሆኑም አመልካች በአቤቱታ ጽሐፊቸው የገለፁትና የዘረዘሩት ፍሬ ነገር ከመ/ቁ 2/90 ከቀረበውና የመጨረሻ ፍርድ ካረፈበት ጉዲይ የተለየ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት ግራ ቀኙ የሚከራከርበት ጉዲይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 5 መሰረት የመጨረሻ ፍርድ ያረፈበት ጉዲይ ነው ሲል የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ መሻሩ በአግባቡ ስለሆነ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
የትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ/ ታህሣስ 25 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት በአብላጫ ድምጽ ፀንቷል።
አመልካች መጋቢት 01 ቀን 1995 ዓ.ም በፃፈት የአቤቱታ ጽሐፍ አዋሣኙንና ስፊቱን የጠቀሱት ቦታ በመ/ቁ 2/90 የመጨረሻ ፍርድ ያገኘ ጉዲይ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ሐምል 14 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ
የ ል ዩ ነ ት ሐ ሳ ብ እኛ ስማችን በሶስተኛው እና በአምስተኛው ተራ ቁጥር የተሰየምነው ዳኞች አብላጫው ድምጽ በሰጠው ውሣኔ ባለመስማማታችን የልዩነት ሀሳባችንና ምክንያታችንን ከዚህ በታች በዝርዝር ገልፀናል።
ይህንን የአመልካች የክስ አቀራረብ ከሥነሥርአት ሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ስንመለከተው ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዲይ የተለየ ነገር በሚሆንበት ጊዜ ነገሩን በመለየት በሚያስችል ሁኔታ ክሱን አብራርቶ የማቅረብ ግዳታ አንዲለበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 225 ንዐጽ አንቀጽ 1 ይደነግጋል በተለይም የከሳሽ ክስ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የተመለከተ በሆነ ጊዜ ከሳሽ በክስ ማመልከቻው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለይቶ ለማወቅ የሚያስችለ ምልክቶችን በክስ ማመልከቻው መግለጽ ያለበት መሆኑንና ይህንንም ግዳታውን የሚወጣው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት የሚለየው የአካባቢ ወሰን በሆነ ጊዜ የአካባቢ የወሰን ምልክቶችን በክሱ ውስጥ በመግለጽ የክስ ማመልከቻው ማቅረብ እንዲለበት ወይም ከዚህ በአማራጭም፣ የማይንቀሣቀሰው ንብረት በዔርስት መዝገብ የተመዘገበ በሆነ ጊዜ ንብረቱ በዔርስት መመዝገቢያ መዝገብ ላይ የተሰጠውን ቁጥር በመጥቀስ ክሱን ማቅረብ እንዲለበት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 225 ንዐስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል። አመልካች ለወረዲው ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 225 ንዐስ አንቀጽ 2 ከተደነገጉት የማይንቀሣቀሥ ንብረት መለያ መንገድች አንደኛውን አማራጭም ብቻ ሣይሆን ሁለቱንም አማራጮች በመጠቀም የክስ ማመልከታቸውን ገልፀዋል። አመልካች በክሳቸው ቦታውን ለመለየት የሚያስችለ የወሰን ምልክቶችን የገለፁ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የመቀላ ከተማ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ ታህሳስ 15 ቀን 1995 ዓ.ም በመቓልሕ ትግራይ ጋዜጣ በተራ ቁጥር 755 ተጠሪ እንዱያካፍላቸው ተጠይቀዋል።
አመልካች በክስ ማመልከቻቸው ውስጥ የቦታ መለያ የወሰን መልክቶችን በመጥቀስ የገለፁት ቦታውና የመቀላ ከተማ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በተራ ቁጥር 755 የገለፀው ቦታ በአንድ መልዔካ ምድር ላይ የሚገኝ አንድ ቦታ አይደለም። አመልካች የወሰን ምልክቶችን በመጥቀስ የጠየቁት ቦታና የመቀላ ከተማ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በመቀልሕ ትግራይ ጋዜጣ በተራ ቀጥር 755 የወጣው ቦታ በተለያየ መልዔካ ምድር የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች ናቸው። የሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በቁጥር 755 በመቓልሕ ትግራይ ጋዜጣ ያወጣው ቦታ በወሰን ምልክቶች ሲገለጽ በምሥራቅ አቶ ኪዲኑ ፈቃደ በምዔራብ አቶ አብርሀ ኪዲኑ በሰሜን መንገድ በደቡብ አቶ ግደይ ገብሩ የሚያዋስኑት 600 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሆነ፣ በመቓልሕ ትግራይ ጋዜጣ በዝርዝር የተገለፀ መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመረዲት ይቻላል።
በእኛ እምነት አመልካች በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁርር 225 ንዐስ አንቀጽ 2 የተደነገጉትን ሁለንም አማራጭዎች በመጠቀም በክስ ማመልከቻቸው የጠየቁት ቦታ ሁለት የተለያዩ ቦታችን ነው። የአመልካች ክስ ግልጽነት የጏደለው መሆኑ አከራካሪ ባይሆንም አመልካች ክስ ያቀረበችው በመቀላ ከተማ ደቡብ ወረዲ ሐድነት ጣቢያ ሚገኘው በምስራቅ 533፣ በምዔራብ አደባባይ፣ በሰሜን 530 በደቡብ 534 የሚገኘውንና ከዚህ በፉት አመልካችና ተጠሪ በመዝገብ ቁጥር 1/90 በወረዲው ፍርድ ቤት ተከራክረው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘውን ቦታ ነው የሚለው መደምደሚያ አመልካች የመቀላ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ በተራ ቁጥር 755 አመልካች ተጠሪ እንዱያካፍላት በክስ ማመልከቻዋ ያቀረበችውን ጥያቄ ተጠሪ አመልካች ክስ እንዲላቀረበችበት ተደርጏ የተሰጠ በመሆኑ ተገቢ ነው የሚል እምነት የለንም። በእኛ እምነት አመልካች የወሰን ምልክቶችን በመግለጽ የጠየቀችው ቦታና ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ ተራ ቁጥር 755 የገለፀውን ቦታ ተጠሪ እንዱያካፍላት ያቀረበችው ጥያቄ ሁለት የተለያዩ ራሳቸውን የቻለ ቦታዎች ናቸው። ስለዚህ አመልካች በክስ ማመልከቻዋ ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ተጠሪ እንዱያካፍላት ጠይቃለች ከሚባል በስተቀር አመልካች በመቐለሕ ትግራይ በተራ ቁጥር 755 ዝርዝሩ የተገለፀን ቦታ ተጠሪ እንዱያካፍላት ክስ አላቀረበችም በማለት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትና አብላጫው ድምጽ የደረሱበት መደምደሚያ በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 225 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት የመቀላ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ አመልካችና ተጠሪ ለሚከራከሩበት ቦታ ያሰጠውን የቦታ መዝገብ ቁጥር በመጥቀስ የቀረበችውን ጥያቄ እንደ ትክክለኛ የክስ አቀራረብ አማረጭ ባለመውሰድ የተሰጠና የማይንቀሣቀሥ ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብ ትክክለኛው እና ብቸኛው የክስ አቀራረብ ሥርዓት የወሰን መለያ ምልክቶችን በመጥቀስ ክስን ማቅረብ እንደሆነ በመቁጠር የተሰጠ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የወረዲው ፍርድ ቤት በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት ባደረገው የቃል ምርመራ አመልካች ተጠሪ እንዱያካፍላት የጠየቀችውና በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ 755 ዝርዝሩና አዋሳኝ የድንበር ምልክቶቹ የተገለፀው ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ አመልካችና ተጠሪ ከዚህ በፉት ያልተከራከሩበትና ውሣኔ ያላገኘ መሆኑን አረጋግጧል።
ስለሆነም ፍረድ ቤቱ አመልካች በመቀልሕ ትግራይ ጋዜጣ በተራ ቁጥር 755 ዝርዝሩና አዋሳኝ ድንበሮቹ የተገለፁት ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የይዞታ መብት አላት ወይስ የላትም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ በመስማትና በመመዘን ከዚህ ቦታ አመልካች ግማሹ ማለትም ሶስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ በይዞታነት ይገባታል በማለት ወስኗል። በእኛ እምነት የወረዲው ፍርድ ቤት በአመልካች ክስ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ተገልፀው መቅረባቸውን በመረዲትና አመልካች በዲኝነት ታይቶ እንዱወሰንላቸው የሚፈልጉት በክሳቸው ከገለፁት ውስጥ በየትኛው ቦታ ላይ እንደሆነ በፍታብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት ተገቢውን የቃል ምርመራ በማድረግ የክርክሩን መሰረተዊ የፍሬ ጉዲይ ጭብጥ መሥርቷል ይኸም የወረዲው ፍርድ ቤት የተከተለው የጭብጥ አመሰራረት ሥርዓት ፍርድ ቤት ጭብጥ ሉመሰርት ስለሚችልባቸው መንገድች በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 428 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገና የሥነ-ሥርዓት ጉድለት የላለበት ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት የጉዲዮን መሰታዊ ጭብጥ የያዘው በፍታብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 428 (ሀ)መሰረት አመልካች በክስ ማመልበቻዋ ያቀረበችውን ጥያቄ የተጠሪ መልስ ፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 428 (ሐ) በተደነገገው መሰረት የቃል ምርመራ ሲያደርግ አመልካችና ተጠሪ የሰጡትን መልስና ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ነው። ከዚህ አንፃር ስንመዝነው የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልትና አብላጫው ድምጽ የወረዲው ፍርድ ቤት በጭብጥ ሲመሰረት የሥነሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎችን እንዲልከተልና መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ሕግ ጥሰት እንደተፈፀመ አድርገው የሰወጡት ትርጓሜና የደረሱበት መደምደሚያ አሳማኝ ሆኖ አላገኘነውም።
የወረዲው ፍርድ ቤት የፍትሐብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 428(ሀ) እና የፍታብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 428(ሐ) ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ከጭብጥነት የያዘውና የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ በመስማትና በመመዘን ውሣኔ የሰጠው የመቀላ ሥራና ከተማ ልማት መምሪያ ታህሣሥ 15 ቀን 1995 በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ በተራ ቁጥር 755 የገለፀው ቦታ ነው። ቦታው በአዋሳኝ ምልክቶች በሚያሳየው በምስራቅ አቶ ኪዲኑ ፈቃደ፣ በምዔራብ አቶ አብርሀ ኪዲኑ በሰሜን አደባባይ በደቡብ አቶ ግደይ ገብሩ የሚያዋስኑት ስድስት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠውምና የዚህ ቦታ ግማሽ የአመልካች ግማሹ ደግሞ የተጠሪ ይዞታ ቦታ ነው በማለት ነው፡ የሥር ፍርድ ቤት የክርክሩ ጭብጥ አድርጏ በያዘው በዚህ ቦታ ላይ አመልካችና ተጠሪ ከዚህ በፉት ተከራክረው አያውቁም። ይኸ ቦታ አመልካችና ተጠሪ በመዝገብ ቁጥር 1/90 ተከራክረው ውሣኔ ካገኘው ቦታ የተለየና ራሱን የቻለ ቦታ ነው። ይህንን መሰረታዊ ፍሬ ጉዲይ የወረዲው ፍርድ ቤት ብቻ ሣይሆን የወረዲው ፍርድ ቤት ውምኔ በይግባኝ ያቀረበላቸው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 272 በሚደነግገው መሰረት በአካል ከቦታው በመገኘትና ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ውሣኔ የሰጡ መሆኑን ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ለመረዲት ይቻላል።
በመሆኑም አመልካች የሰበር አቤቱታ አቅርበውበት በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር አመልካችና ተጠሪ ከዚህ በፉት በመዝገብ ቁጥር 1/90 ተከራክረው የመጨረሻ ውሣኔ ካገኘው ቦታ የተለያየና ራሱን የቻለ ቦታ ነው። የወረዲው ፍርድ ቤት የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ አድርጏ የመሰረተውና የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሣኔ የሰጠበትና ጉዲዩ መጀመሪያ በይግባኝ ያየው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ማጣራት በማድረግ ውሳኔ ሰጥቶበት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የፀና ውሳኔ ከዚህ በፉት አመልካችና ተጠሪ ያልተከራከሩበትና ውሳኔ ያላገኘ ጉዲይ ነው። አመልካችና ተጠሪ ከዚህ በፉት ተከራክረው በመዝገብ ቁጥር 2/90 ውሳኔ ያገኘ ቦታ የወረዲው ፍርድ ቤት የክርክሩ መሰረታዊ ጭብጥ አድርጏ፣ ከያዘው የአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሳኔ ከሰጠበትና ጉዲዩንም በይግባኝ አይተው ያፀደቁት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ ከሰጡበት ጉዲይ የተለየ ነው።
አመልካችና ተጠሪ ከዚህ በፉት ተከራክረው ውሳኔ ያገኘው ቦታና በዚህ ጉዲይ የመቀላ ወረዲ ፍርድ ቤት የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በጭብጥነት ይዘው ውሳኔ የሰጡበት ቦታ የተለያዩ መሆናቸውን የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ በግልጽ እያሳየ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አላግባብ የፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5 ንዐስ አንቀጽ በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትና በዚህ ችልት ሉሻርና ሉታረም የሚገባው ነው የሚል እምነት አለን። በያዝነው ጉዲይ በጭብጥነት የተያዘውና በየደረጃው ያለ የትግራይ ፍርድ ቤቶች አጣርተው ውሳኔ የሰጡበት ቦታ ከዚህ በፉት አመልካችና ተጠሪ ተከራክረው በውሣኔ ካለቀው ቦታ የተለየ በሆነበት ሁኔታ የፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5 ንዐስ አንቀጽ 1 ተፈፃሚነት እና አግባብነት የላለው በመሆኑ በድንጋጌው መንፈስና ዓላማ እንዱሁም ይዘት ጋር የማይጣጣም ትርጉም የመስጠት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሳኔ አብላጫ ድምጽ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ማጽናቱ አግባብነት ያለው ነው ብለን ባለማመናችን በሐሳብ ተለይተናል።
ስለሆነም በአመልካች በክስ ውስጥ የወሰን መለያ ምልክቶችን በመጥቀስ ያቀረበችውን የክስ ክፍል ሙለ በሙለ በማውጣት በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ ተራ ቁጥር 755 የተጠቀሰውን ቦታ አዋሻኝ የድንበር መለያ ምልከቶች በመግለጽ ክሷን አሻሽላ እንድትቀርብ በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 91 ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት በራሱ አነሳሽነት ትእዛዝ በመሰጠት ጉዲዮን ለክርክር ክፍተት በማይፈጥርበት ሁኔታ አይቶ መወሰን እየቻለ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሥርዓት አልተጠቀመበትም። በልላ በኩል ተጠሪ ፍርድ ቤቱ አመልካች ክሷን እንድታሻሽል ሣያደርግ ክርክሩን ማስቀጠለ የመከላከል መብቴን የሚያጣብብና የሥነ ሥረዓት ጉድለት ያለበት ነው የሚል እምነት ካለው በወቅቱ የወረዲው ፍርድ ቤት ይህንን የሥነ ሥርዓት ጉድለት እንዱያርመው በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 207 መሰረት አቤቱታ የማቅረብ መብት የነበራቸው ቢሆንም ተጠሪ ይህንን መብታቸውን ያልተጠቀሙበት መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ ለመገንዘብ ይቻላል።
የወረዲው ፍርድ ቤት በአመልካችንና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ውሣኔ የሰጠው በመቐልሕ ትግራይ ጋዜጣ ተራ ቁጥር 755 በሥራና ከተማ ልማት መምሪያ በተጠሪ ስም የወጣው ነባር የይዛታ ቦታ ላይ አመልካች መብት አላት ወይስ የላትም የሚለው ጭብጥ በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ድንጋጌዎች መሰረት በመመሥረት በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ክሷን ሳታሻሽል የአመልካችንና የተጠሪን ክርክር ሰምቶ ውሳኔ መስጠቱ የተጠሪን የመከላከል መብትና የፍትህ መጓደልን ያስከተለ መሰረታዊ የሥነ ሥርዓት ጉድለት ነው ብል ለመደምደም የሚያስችለን ሆኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም ይኸ የወረዲው ፍርድ ቤት የሥነ ሥርዓት ጉለት የፈፀመበት የወረዲው ፍርድ ቤት ውሣኔ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ቀርቦበት የከፍተኛው ፍርድ ቤትም የበኩለን ተጨማሪ ማጣራት ካደረገ በኋለ አጽድቶታል። ውሣኔ ድጋሚ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦበት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ፀድቋል።
አንድ ጉዲይ በሚታይበት ጊዜ ቀላል ሥነ-ሥርዓት ጉድለት የተፈፀመ ሲሆንና የሥን ሥርዓት ጉድለት የፈፀመው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ይግባኝ ቀርቦበት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የፀደቀ ከሆነ ውሣኔው በተፈፀመው ቀላል ሥነ ሥርዓት ጉድለት ምክንያት ብቻ ውድቅ እንደማይሆን በፍታብሕር ሥነ ሥርዓት 212 ተደንግጓል። ስለሆነም የወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ክሷን እንድታሻሽል ሣያደርግ አመልካቹንና ተጠሪን አከራክሮ መወሰኑ እንደ መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚቆጠርና ውሳኔውን ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ምክንያት ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር በገለጽናቸው ምክንያቶች የወረዲው ፍርድ ቤት ውሣኔና በይግባኝ ቀርቦላቸው ያዩት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም። የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የበታች ፍርድ ቤቶች ጭብጥ አድርገው ያልያዙትንና ውሣኔ ያልሰጡበትን ጉዲይ አግባብ በመጥቀስ የፍታብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5 ንዐስ አንቀጽ 1 አላግባብ በመተርጏም የሰጠው ውሣኔ የሥር ፍርድ ቤቶች ጭብጥ አድርገው በመያዝ ውሣኔ የሰጡበትን ፍሬ ጉዲይ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ይኸ የሰበር ችልት ሉሽረውና የተፈፀመውን መሰረታዊ የህግ ስህተት ሉያርመው ይገባል በማለት የልዩነት የውሣኔ ሀሳባችንና ምክንየታችንን ገልፀናል።
No topics extracted.