No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ታፈሰ ይርጋ ፀጋዬ አስማማው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ናስ ፈድስ የድ/ዲ/ጨ/ጨ/ፊብሪካ ተከራይ - ጠበቃ ወንድዬ ግርማ ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ስንደ ደጀኔ (93 ሰዎች) መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች የካቲት 18 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የክስ ማመልከቻ በአመልካች ድርጅት ለረዥም ዘመናት በተለያዩ የስራ ዘርፍች ተቀጥረው ሲሰሩ ቆይተው መስከረም 30 ቀን 2000 ዓ.ም የስራ ውላቸው መቋረጡን፣እንዱህ ሲደረግም ሉከፍላቸው የሚገባ የስራ ስንብት ክፍያ፣የ60 ቀን ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ያልተወሰደ የአመት እረፍት ክፍያ ሣይከፈላቸው መቅረቱን ዘርዝረው በህብረት ስምምነቱ መሰረት ለእያንዲንዲቸው የአንድ ወር ደመወዝ በ42% ተባዝቶ የ2 ዓመት ከስድስት ወር ተቆርጦ የተያዘባቸው የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መ/ደ/ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሉዝ ውለ መሰረት የፕራይቬታይዜሽንና የመ/ል/ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ወደ ክርክሩ እንዱገባ እንዱታዘዝለት የአገልግልት ክፍያ ጥያቄም ጊዜውን በተመለከተ ግልጽነት የላለው በመሆኑ የሥነ-ሥርዓት ጉድለት እንዲለበት በመዘርዘር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት የተከራከረ ሲሆን በፍሬ ነገር ረገድም ለክሱ ኃፉነት የላለበት መሆኑን ያሣያለ ያላቸውን መከራከሪያ ነጥቦችን አንስቶ ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ውድቅ አድርጏ ለክሱ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን በመግለጽ ተጠሪዎች እያንዲንዲቸው የአንድ ወር ደመወዝ 42% ለሁለት ዓመታት፣21% ደግሞ ለስድስት ወራት የአገልግልት ካሣ ክፍያ በአመልካች ሉከፈላቸው ይገባል ሲል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሐምል 23 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት 2/ሁለት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ጉዲይ በቀጥታ የሚመለከተው የፊብሪካው ባለቤትና አከራይ በክርክሩ ጣልቃ እንዲይገባ መደረጉ፣አመልካች ፊብሪካውን ከመከራየቱ በፉት ላለ እዲና ሐላፉነት ከፊይና አስከፊይ መደረጉ ከህጉና ከኪራይ ውለ ውጪ መሆኑንና ጉዲዩም ቀደም ሲል በተመሣሣይ ሁኔታ ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ነው በማለት ዘርዝረው የበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪዎች በወኪልቻቸው አማካኝነት ታህሣስ 09 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፊት 2/ሁለት/ ገጽ ማመልከቻ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመንቀፍና የበታች ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ተገቢነት በመግለጽ ውሣኔው ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው የካቲት 11 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የጽሐፍ ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጭብጥ በጉዲዩ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በክርክሩ እንዱገባ አመልካች ጠይቆ በበታች ፍ/ቤቶች ጥያቄው ውድቅ ተደርጏ ለክፍያው ኃላፉ መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች ለረዥም ዘመናት በተለያዩ የስራ ዘርፍች በፊብሪካው ተቀጥረው የሚሰሩ መሆኑን፣ ፊብሪካውን የሚያስተዲደረው የነበረው የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ መሆኑን፣ ፊብሪካውን የአሁኑ አመልካች ከአስተዲዲሪው አካል በኪራይ ከየካቲት ወር 1999 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ያህል መከራየቱን ነው። እንግዱህ አመልካች የፊብሪካው ተከራይ መሆኑ ከተረጋገጠ ከፊብሪካው ጋር ተያይዘው የሚነሱት መብትና ግዳታዎች የኪራይ ውለንና አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች በመመልከት ምላሽ የሚያገኙ ናቸው።
አመልካች ለተጠሪዎች ጥያቄ በተከራይነቱ ኃፉነት የላለበት መሆኑን፣የተከራዩ እና አከራዩ መብትና ግዳታም በውለ ላይ መዘርዘሩን ጠቅሶ አከራይ ወደ ክርክሩ እንዱገባ ይታዘዝለት ዘንድ አመልክቷል። የስር ፍ/ቤትም አመልካች በዋቢነት የጠቀሰውን የኪራይ ውለን አንቀጽ ሰራተኞች የክፍያ ጥያቄውን በቀጥታ ለአከራይ እንዱያቀርቡ የማያስገድድ፣አመልካችም በመዋቅሩ ምክንያት ከስራ ለሚያሰናብታቸው ሰራተኞች ተገቢውን ክፍያ ከፈፀመ በኋላ ወጪውን ከአከራይ እንዱጠይቅ የሚያስችል ነው በማለት የራሱን እምነት በመግለጽ ወደ ክርክሩ እንዱገባ የተጠየቀውን አካል ሳይጠራ አመልካችን ኃላፉ አድርጏ ወስኗል።
No topics extracted.
በመሰረቱ በአንድ ጉዲይ ላይ ክስ ላቀርብና የክሱም ምክንያት የብዙ ሰዎች መብትና ጥቅም የሚነካ ሆኖ ከእነሱ ውስጥ አንደ ወይም ከፉለ ክስ ባቀረቡ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጉዲዩ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ወይም ፍርድ የክርክሩ ተካፊይ ያልሆኑትን ወገኖችም መብትና ጥቅም የሚነካ ሲሆን በክሱ ውስጥ ተካፊይ ያልሆኑ ሰዎች የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ መስጠት የአለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 39/1/ እና 40/2/ ድንጋጌ ስር ተመልክቷል። እነዚህ ወገኖች ተካፊይ ሣይሆን የሚሰጠው ውሣኔ ወይም ፍርድ ውጤት የማይኖረው ስለመሆኑም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች መንፈስ ያስገነዝባል። በመሆኑም በክሱ ውስጥ መግባት ያለበት ተከሣሽ የሆነ እንደሆነ ፍ/ቤቱ የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆንና ለቀረበው ክስ መልስና መከላከያውን እንዱያቀርበው ሉያዘው የሚችል ስለመሆኑ ሥነሥርአት ህጉ አስቀምጧል። በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፊይ መሆን የሚገባቸው ወገኖች ማለት ክስ በቀረበበት ጉዲይ ላይ በሚሰጠው ውሣኔ ጥቅማቸው፣መብታቸው ወይም ግዳታቸው የሚነካ በክርክሩ ውስጥ ተካፊይ ያልሆኑ ሰዎች ስለመሆናቸውም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 40 ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች የፊብሪካው ተከራይ ሆኖ የኪራይ ውለ የሚቆይበት ዘመንም ሁለት ዓመት ስለመሆኑ የአከራይና ተከራይ ጥቅም፣መብት ወይም ግዳታዎች በኪራይ ውለ መዘርዘሩን አመልካች ያስረዲ ሲሆን ከኪራይ ውለ ይዘት አኳያ ሲታይም በጉዲዩ ላይ የሚሰጥ ውሣኔ የአከራይን ጥቅም፣መብት ወይም ግዳታ ሉነካ አይችልም ልባል የማይገባው ነው። በመሆኑም አከራይ በክርክሩ የግድ ተከፊይ መሆን የሚገባው ወገን /Indispensable party/ ሆኖ እያለ የስር ፍ/ቤት በኪራይ ውለ ላይ የተመለከተውን አንድ አንቀጽ ብቻ ነጥል በመውሰድ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ስነ-ስርአታዊ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22768 ሚያዝያ 21 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 03845 ሐምል 14 ቀን 2000 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፊብሪካው አከራይ የተባለው የፕራይዜታይቬሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፊይ መሆን የሚገባው ወገን በመሆኑ ለቀረበ ክስና መልስ መከላከያውን እንዱያቀርብ የስር ፍ/ቤት ትእዛዝ ሰጥቶ ጉዲዩን እንደገና በመመልከት ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መ/ቤት ይመልስ።