No summary available.
የካቲት 3 ቀን 2001 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ሐጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ በላቸው አንሺሶ ሱልጣን አባተማም አመልካች፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ጠበቃ ንጉሴ ገዛኸኝ ቀረበ።
ተጠሪዎች፡-
ስዩም ማሞ - ቀረበ።
በየነ አበራ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። ከሣሾች የነበሩት የአሁኖቹ ተጠሪዎች ናቸው። በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት ጥፊት ሳንፈጽም የገንዘብ ቅጣት/ከደመወዛችን ላይ እየተቀነሰ/ እንድንከፍል ተወስኖብናል። ማስጠንቀቂያም ተሰጥቶናል። ስለዚህ ቅጣቱና ማስጠንቀቂያው ይሰረዝልን ዘንድ ይወሰንልን በማለት ነው።
አመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሾች ግንቦት 6 ቀን 1999 ዓ.ም በማታው ፈረቃ የነበረውን የስራ ጫና ለማደላደል አለቃ በሚወስነው የአሰራር አፈጻጻም ስርአት መሰረት ከነበሩበት ቦታ ወደ ላላ ቦታ በመሄድ እንዱሰሩ አመራር ቢሰጣቸው አመራሩን ሳይቀበለ በመቅረታቸው ነው ቅጣቱ የተወሰነባቸው። ቅጣቱ የተወሰነው በሕብረት ስምምነቱ መሰረት በመሆኑ ሕጋዊ ነው። የሚሰረዝበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት ስለመከራከሩ ኀዲር 2 ቀን 2000 ዓ.ም ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ የስራ ክርክር ችልት ከፃፈው የመልስ ማመልከቻ ለመገንዘብ ችለናል። በዚህ መልክ ክርክር የቀረበለት የስራ ክርክር ችልትም ክርክሩን ከመረመረ በኋላ፣ በከሣሾች ላይ ቅጣቱ የተወሰነው በማታ ሽፍት አንሰራም ብለዋል በሚል እንጂ ከነበሩበት ቦታ ወደ ላላ ቦታ ተዛውረን አንሰራም ብለዋል በሚል አይደለም የሚል ምክንያት በመስጠት በአመልካች የተሰጠው ቅጣት እንዱሰረዝ ወስኖአል። በዚህ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የስራ ክርክር ችልትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም ብልአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውን በዚሁ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በአመልካች ተሰጥቶ የነበረውን የቅጣት ውሳኔ በፍ/ቤቶቹ በተሰጠው ውሳኔ የተሰረዘበትን አግባብ ለመመርመር ነው። በመሆኑም ይህን ነጥብ ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር፣አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ተጠሪዎች ቅጣት የተወሰነባቸው በአለቃቸው የተሰጣቸውን የስራ መመሪያ ለመቀበል ፍቃደኛ ሆነው አልተገኙም በሚል ነው። መስከረም 8 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት የክስ ማመልከቻ እንደሚታየው በአለቃቸው የተሰጣቸውን ትእዛዝ በመቀበል በስራ ቦታው እንደተገኙ ገልጸዋል። ይህም የሚያሳየው ለቅጣቱ መነሻ ሆኖአል የተባለው ጥፊት /የአለቃ መመሪያ አለመቀበል/ አለመፈጸማቸው በመግለጽ መከራከራቸውን ነው። አመልካችም ኀዲር 2 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው መልስ የበኩለን የመከላከያ ክርክር ያቀረበ ሲሆን፣ይዘቱም ከላይ የተመለከተው ነው።
እንግዱህ ከግራ ቀኝ ወገኖች የቀረበው የጽሐፍ ክርክር በግልጽ እንደሚያመለክተው አከራካሪው ጭብጥ ቁልጭ ብል መውጣቱን ነው። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 247/1/ እንደተደነገገው የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ላላው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ እንደሆነ ነው። በተያዘው ጉዲይ በአመልካች ለቅጣቱ መወሰን መሰረት ሆኖአል ያለው የፍሬ ነገር አግባብ በተጠሪዎቹ ተክድአል። በመሆኑም ይህ የፍሬ ነገር ጭብጥ እንደየሁኔታው ግራ ቀኝ ወገኖች ከሚያቀርቡት ማስረጃ አንፃር ታይቶ የሚነጥር ነው። በመቀጠልም በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ እውነታ ካለ አግባብ ካለው ሕግ አንፃር በመመርመር አግባብ ወዲለው ውሳኔ መድረስ ይችላል።
አቤቱታ በቀረበበት ውሳኔ እንደሚታየው ክርክሩ ከፍ ሲል በተመለከተው አኳኋን አልተመራም። የክርክሩ አመራር የክርክር አመራር ስርአት ወይም አግባብ ተከትል ካልተከናወነ ፍትሐዊ ውሳኔ ላይ መድረስ አይቻልም። አንድን ክርክር በመምራት ላይ ያለ ፍ/ቤት ሉያከናውናቸው ከሚገባቸው መሰረታዊ ነገሮች አንደና ዋነኛው የክርክሩን ጭብጥ ለይቶ ማውጣት ነው። በያዝነው ጉዲይ በስር ፍ/ቤቶች ሳይከናወን የቀረውም ይኸው ተግባር ነው። ትክክለኛው ጭብጥ ባለመያዙም የደረሰበት ድምዲሜ ትክክል ነው ልባል አይችልም። በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37409 ጥር 28 ቀን 2000 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 37391 መጋቢት 22 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ለተወሰነው ቅጣት መሰረት ሆኖአል የተባለውን ጥፊት ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም? የሚለውን የፍሬ ነገር ጭብጥ በግራ ቀኝ ወገኖች በሚቀርብለት ማስረጃ መሰረት እንዱያነጥር /እንዱያረጋግጥ/፤ በመቀጠልም በፍሬ ነገር ረገድ አጣርቶ የደረሰበትን ድምዲሜ አግባብ ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ ከመረመረ በኋላ የመሰለውን ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
ይፃፍ።
ት እ ዛ ዝ ከፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ የመጣው ቁ. 37409 የሆነው መዝገብ ወደ መጣበት ይመለስ።፡