No summary available.
የካቲት 5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ዓብደልቃድር መሐመድ ፀጋዬ አስማማው በላቸው አንሺሶ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 19/2ዐ አስተዲደር ጽ/ቤት - ነ/ፈጅ አቶ ወንደሰን በቀለ።
ተጠሪ፡- አቶ ያሲን ጀማል - ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነበር። መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ለሰበር የቀረበው አመልካች የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የይግባኝ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ሰኔ 1ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ስለጠየቀ ነው።
የክርክሩ ፍሬ ጉዲይ የአሁን ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዲ ዐ8 ቀበላ ዐ6 የቤት ቁጥር 636 በሆነ የይዞታ ማረጋገጫ የካርታ የሆነ የግል ይዞታ አለኝ። ስለሆነም ተጠሪ በዚህ ይዞታ ላይ ለሰራሁት የግል ቤቴ ኪራይ መክፈል አለብህ በማለት ቁጥሩ አ/አ/ከ/ቁ. 19/ዐዐ2/92 የሆነ ደብዲቤ ሰኔ 1ዐ ቀን 1995 የፃፈልኝ ስለሆነ፣ ደብዲቤው እንዱሰረዝልኝና ኪራይ መክፈል እንደማይገባኝ ይወስንልኘ በማለት አመልክተዋል። የአሁን አመልካች ከሥር በተከሳሽነት ቀርቦ ከሣሽ /ተጠሪ/ ከይዞታቸው ውጭ በመንግሥት ባድ ቦታ ላይ ያለ ፈቃድ በሕገ ወጥ መንገድ ቤት ሰርተው ተገኝተዋል። ይህንን በመግሥት ቦድ ቦታ ላይ የተሰራ ቤት ቁጥሩ 636/ሀ/ የሚል ቁጥር ከሰጠነው በኋላ ከሣሽ /ተጠሪ/ የንግድ ሥራ እንዱያከናውኑበት በመስማማት ተከሣሽ /ተጠሪ/ በመኖሩ በቀበላ ለመክፈል ተስማምተው የኪራይ ውል ፈርመው በገቡት የኪራይ ውል መሰረት ኪራይ እንዱከፍለ ከመጠየቃችን በስተቀር በሕጋዊ ይዞታቸው ላይ ለሰሩት ቤት ኪራይ እንዱከፍለ አልጠየቅንም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት አመልካች /ተከሣሽ/ ተጠሪ /ከሣሽ/ በባድ የመንግሥት መሬት ላይ ቤት ሰርተው ካገኘ ቤቱን እንዱፈርስ ከማድረግ በስተቀር ኪራይ የመጠየቅና የመሰብሰብ ስልጣን የለውም። ስለዚህ አመልካች /ተከሣሽ/ ከተጠሪ /ከሣሽ/ በሕገ ወጥ መንገድ ተሰርቷል ከሚለው ቤት ኪራይ መቀበለን እንዱያቋረጥ በማለት ወሰኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይግባኙ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። አመልካች ውሣኔው በሰበር እንዱታይ ለከተማ ነክ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎበታል።
አመልካች በየደረጃው ያለ የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት። ተጠሪ እየከፈልኩ ልጠቀምበት በማለት ጥያቄ በማቅረባቸው በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኪራይ ውል ተፈጽሟል። ተጠሪ ከጳጉሜ 2 ቀን 1988 ዓ.ም. እስከ 1995 ዓ.ም. የቤት ኪራይ ሲከፍለ ቆይተው 1995-1998 ያለውን ውዝፍ ኪራይ እንዱከፍለ ደብዲቤ ተጽፍላቸው። ከዚህ በኋላ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የላለውና የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ቤቱ የተሰራው በሕጋዊ ይዞታዬ ላይ ነው። የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የሰጡት ያለኝን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው። የኪራይ ውል አለን በማለት ያቀረቡት ክርክር በማስረጃ የተደገፈ አይደለም፣ ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በማጽናት እንዱያሰናብተኝ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። በሥር የተደረገው ክርክርና በሰበር አመልካችና ተጠሪ ያቀረቡት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን፣ እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው፣ የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካች ጥያቄ የክስ ምክንያት አለው ብለው መቀበላቸውና አመልካችንና ተጠሪን አከራክረው አመልካች ከተጠሪ የቤት ኪራይ መቀበለን፣ እንዱያቋርጥ በማለት መወሰናቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው ጥያቄ ይዘት አመልካች ተጠሪ በወረዲ 8 ቀበላ 6 ቁጥሩ 636/ሀ/ ለሆነው የድርጅት ቤት ያለበትን ውዝፍ ኪራይ እንድከፍል የፃፈው ደብዲቤ እንዱሰረዝልኝና ኪራይ እንዲልከፍል ይወስንልኝ የሚል ነው። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ፣ ከተጠሪ ጋር ጳጉሜ 2 ቀን 1988 ዓ.ም. በተደረገ የቤት ኪራይ ውል ተጠሪ የተከራየው መሆኑንና እስከ 1995 ድረስ ኪራይ ሲከፍል ቆይቶ፣ 1995 በኋላ ኪራይ መክፈለን ስላቆመ ማስጠንቀቂያ የተፃፈለት መሆኑን ነው። ከዚህም የምንረዲው የአመልካችና የተጠሪ ግንኙነት ጳጉሜ 2 ቀን 1988 በተደረገው የቤት ኪራይ ውል ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው። ተጠሪ፣ ከአመልካች ጋር የተደረገው የኪራይ ውል ሕጋዊ ውጤት ሉሰጠው የሚገባው አይደለም በፍርድ ታይቶ ፈራሽ መሆን አለበት የሚለበት፣ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1696 እስከ ፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 171ዐ ከተዘረዘሩት አንደ ወይም ላላ ውለ እንዲይረጋ የሚያደርግ ምክንያት አለኝ ብለው የሚያስቡ ከሆኑ ምክንያታቸውን በማስረጃ በማስደገፍ ከአመልካች ጋር ያደረጉት የኪራይ ውል እንዱፈርስ መጠየቅ ነበረባቸው ተጠሪ ይህንን አላደረጉም።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር ጳጉሜ 2 ቀን 1988 የፈፀሙት ውልን ፈራሽ ሣያደርጉ፣ አመልካች በዚህ ኪራይ ውል መሰረት ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዱከፍለ የፃፈው ደብዲቤ እንዱሰረዝላቸው የኪራይ ገንዘብ እንዲይከፍለ እንዱወስንላቸው ያቀረቡት ጥያቄ የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት ተጠሪ ከአመልካች የሚጠይቁትን መብትና ጥቅም በግልጽ የማያሣይና የክስ ምክንያት የላለው ነው። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረበውንና ይህንን የክስ ምክንያት የላለውን ጥያቄ ለአመልካች መጥሪያ ከመላኩ በፉት መርምሮ በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 231 ንዐስ አንቀጽ 1/ሀ/ መሰረት ውድቅ ማድረግ ነበረበት። የሥር ፍርድ ቤት ከላይ የተገለጹትን ድንጋጌዎች በሚጥስ አኳኋን፣ ተጠሪ ከአመልካች የሚጠየቀውን አመልካች የፃፈው ደብዲቤ ይሰረዝልኝ እና የቤት ኪራይ እንዲልከፍል አቤቱታ በመቀበል ማከራከሩንና ቤቱን በሕገ ወጥ መንገድ ተጠሪ በመግንስት ባድ ቦታ ላይ የሰራው ቢሆንም ቤቱ እንዱፈርስ ከማድረግ በስተቀር ተጠሪ ኪራይ እንዱከፍል ማድረግ አመልካች ስልጣን የለውም ከሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለውን የቤት ኪራይ ውል ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው።
የአዱስ አበባ ከተማ ነክ፣ የይግባኝና ሰበር ችልትም የሥር ፍርድ ቤት የክስ ምክንያት የላለውን የተጠሪን ጥያቄ አላግባብ በመቀበል የሰጠውን ውሣኔ ማጽናታቸው ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ተጠሪ የቤት ኪራይ ለአመልካች እንዲልከፍል ይወስንልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የክስ ምክንያት የላለው ሆኖ እያለ በየደረጃው ያለ የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች አመልካች ከተጠሪ የቤት ኪራይ ለአመልካች እንዲልከፍል ይወስንልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የክስ ምክንያት የላለው ሆኖ እያለ በየደረጃው፣ ያለ የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች አመልካች ከተጠሪ የቤት ኪራይ መቀበለን እንዱያቆም የሰጡት ውሣኔ፣ ከላይ የዘረዘርናቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር ዐ2157 መጋቢት 2ዐ ቀን 1998 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል። ይፃፍ።
የአዱስ አበባ አስተዲደር ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና በመዝገብ ቁጥር ዐ3331 ጥቅምት 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የአዱስ አበባ አስተዲደር ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዘገብ ቁጥር ዐ6ዐዐ1 መጋቢት 19 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.
የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል። ይፃፍ።
ተጠሪ አመልካች በቁጥር 19/ዐዐ2/95 ሰኔ 1ዐ ቀን 1995 ዓ.ም. የፃፈው ደብዲቤ ይሰረዝልኝ የቤት ኪራይ ገንዘብ እንዲልከፍል ይወስንልኝ በማለት፣ ያቀረበው ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻለ። ይህ ፍርድ ቤት በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የካቲት 5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በሙለ ድምጽ፣ ተሰጠ።
No topics extracted.